Get Mystery Box with random crypto!

#በልተህ_ስለጠገብክ_ብቻ_አፍህን_አትክፈት! አንድ ቀን አንድ በሬ የሚያምር አረንጓዴ ሳር አየና | ስኬታማ ህይወት

#በልተህ_ስለጠገብክ_ብቻ_አፍህን_አትክፈት!

አንድ ቀን አንድ በሬ የሚያምር አረንጓዴ ሳር አየና ያንን ተከትሎ ለመጋጥ ጥቅጥቅ ወዳለው የጫካው ክፍል ዘልቆ ገባ።

እዚያ ከኖረ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ያለምንም ሀሳብ ስለሚበላና ስራም ስለቀረለት ወፈረ፡፡ ከዚያ አድኖ ለመብላት አቅም ያጣና የተራበ አንድ ሽማግሌ አንበሳ ይህን የሰባ በሬ ተመለከተ። ሚዳቋን አባሮ ከመያዝ በሬን ማደንና ማረድ ይቀል የለ? ስለሆነም፥ ጊዜ ጠብቆ በሬውን ገደለና በላው።

ከዚያ በጣም ጠገበና ከፍ ባለ ድምጽ አገሳ፡፡

በዚያ በመንገድ የሚያልፉ ጥቂት አዳኞች ድምጹን ሰምተው አንበሳውን ተከታትለው በጥይት ገደሉት።

#የታሪኩ_ፍሬ_ነገር- በልተህ ስለጠገብክ ብቻ አፍህን አትክፈት! የሚል ነው፡፡

ሰዎች ምን እንደሆነ ሳያውቁ ብዙ ነገሮችን ስላነበቡ ብቻ ጽፈዋል፤ ስለሚናገሩት ነገር በቂ እውቀት ስለሌላቸው ብዙ ነገር ተናገረዋል፣ ብዙ የማይረባ ነገር ከመነገሩ የተነሳም ብዙ ግራ መጋባት ተፈጥሯል። ሰዎች ዝም ቢሉ ኖሮ የሰው ልጅ በማሰብ ችሎታው መገለጥን ማወቅ ይችል ነበር፡፡ ማንም ስለ መገለጥ የማያውቀውን ነገር ባይናገር ኖሮ ብዙ ሰዎች መንገዳቸውን ባገኙ ነበር።

ሁሉም ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ አፋቸውን ቢዘጉ፣ እያንዳንዱ የሰው ልጅ ለማወቅ መጓጓቱ በጣም ተፈጥሯዊ ነው። ሁሉንም ነገር መመርመር ለአንተ አእምሮ በጣም ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች የተዘጋጁ መፍትሄዎችንና የማይረቡ ነገሮች በማመን ያንን ያበላሻሉ።

#ከሕይወት_ኬሚስትሪ መጽሀፍ ላይ
አስተያየት ለመስጠት:
@kci21