2022-07-13 21:27:20
#ለውጥ
.
.
transformation (መለወጥ/መሻሻል), barter (ለወጠ), change (ተለወጠ/ለወጠ), reverse(መለወጥ), reform,... የሚለት የኢንግልዘኛ ቃላቶችን ይይዛል።
ለዚህ አለም ከሚያስፈልገው ነገር ውስጥ ቀዳሚውና ዋናው “ለውጥ” ነው። ፍጥረተ አለሙ በአጠቃላይ በግልጽም ይሁን በይፋ ለውጥን ያራምዳል።
ሀሉንም ነገር የምታደርገው፣ የምትሰራው፣ የምትደግፈው፣ የማትደፈው፣ የምትጠላው፣ የምትወደው... መነሻቸው ሀሳብ ነው። ካሰብክመና ካሰላሰልክ በኋላ ወዳዘነበልክበት ትወስናለህ።
በወሰንከዉ ነገር ላይም ለመፅናት ትጥራለህ፡፡ ለማሳካትም ትለፋለህ ትተጋለህ፡፡
ስለዚህ የነገራቶች መነሻ ሀሳብ ነው ያላሰብከውን አትናገርም አትሰራምም፡፡
'ለውጥ የሚጀምረው ከሀሳብ ነው።
በፊት ከነበረህ የተሳሳተ እይታ(አመለካከት) አስወግደህ ራስህን፣ ቤቴሰብህን፣ ማህበረስብህን፣ ሀገርህን… የሚጠቅም ሃሳብ ስታስብ የአስተሳሰብ ለውጥ አስመዘገብክ ማለት ነው፡፡
አንተ የምታስበው፣ የምታደርገው፣ ምታልመው፣ የምታምነው ነገር ለውጥን ያመጣል። ጥሩ የለውጥ ሀሳብ ካመነጨነህ ተስፈኛ ነህ። የለውጥ ሀሳብ ደግሞ ብሩህ ተስፋን፣ መልካም ህልውናን ይሰጣል። ቆራጥ ማንነትን እንድንገነባ ይረዳል፣ ፅናትን ትለምዳለህ፣ ተስፋህ እውን ሆኖ ለማየት ትጓጓለህ ትታትራለህም።
ማስተዋል ያለብህ ነገር ጥሩ የለውጥ ሀሳብ ብቻውን ለውጥ አይሆንም፤ አስተሳሰብህ ከተለወጠ በቂ ነው ማለት አይደለም፤ ሃሳብህ መሬት ላይ መውረድ አለበት ልትተገብረው ግድ ይላል፡፡ ለውጥ ተግጋባር ይፈልጋልና።
በለውጥ ወቅት በተስፋ እና በተግባር መካከል ግጭት ሊፈጠር ይችላል። በዚህ ጊዜ ታጋሽና መሆንና በቶሎ እጅ መስጠት የለብህም። ለውጥ የጨለማ ጉዞ መሆን የለበትም፤ በተቻለ መጠን በጥሞና የታሰበበት፣ በእጋት የታቀደበት መርሀ ግብር ሊኖረው ይገባል፡፡
በለውጥ ወቅት ትንሽ ስህተት ለብዙ ነገር ይዳርዳርጋል ስለሆነም ጥንቃቄን ያሻል። ለውጥ ማፍረስን በማይጠቅሙ ነገራቶች ላይ ደግሞ ማመጽን ይጠይቃል። ለውጥን ለማየት ብዙ ጊዜ ይፈልጋል፤ መስዋትም ያስከፍላል።
የጽንፈ አለምም ሆነ የሰው ልጆች መኖር ይህ ነው ሚባል አላማ ከሌለህ፤ የምትኖርለት ነገር ካጣህ በህይወትህ ምናልባትም ዘር ከመተካት ያለፈ አላማ አይኖርህም ማለት ነው፤ ከንቱ ሰው ሆነህ ከንቱ ቤተሰብን ትገነባለህ፣ ስትሞት ደግሞ ከንቱ ነህና ለዘላለም ከህልውናህ ውጭ ትሆናለህ።
የማሰብ የማዛዘንና ስለ ሕይወት አላማ የማሰላሰል ችሎታ ያለው አንጎልህ ይህን ችሎታ ያገኘው እንዲሁ በአጋጣሚ ይሆናል ማለት ነው። እራስህን በመፈተሸ ምንም ሳትፈራ ቆርጠህ በመነሳት ለመለወጥ መዘጋጀት፤ በለውጥ ሰአት የሚያጋጥሙ ዕንቅፋቶችንም ለማለፍ እራስህን ማዘጋጀት አትዘንጋ፡፡
በመጨረሻም ጥያቄ አዘል ምሳሌን ላስነብባችሁ፦
በአንድ ጫካ ውስጥ እየተዘዋቀርክ ሳለህ አንድ የሚያምር የእንጨት ቤት አየህ እንበል፤ ታዲያ በዚህ ጊዜ 'እንዴት ያምራል! ዛፎቹ እንዴት በትክክል ተገንድሰው ቢወድቁ ነው ይህን ቤት ያስገኙት!' ብለህ ታስባለህ?
እንዲህ እንደማታስብ የታወቀ ነው! እንዲህ ብሎ ማሰብ ምክንያታዊነት አይደለም።
ታዲያ ለምን ብለን ነው በጽንፈ አለማችን ውስጥ ያሉት ነገሮች ሙሉ እንዲሁ ተገኙ ብለን የምናምነው?
.
.
https://t.me/kamil_official
https://t.me/kamil_official
415 viewsAkmel, 18:27