Get Mystery Box with random crypto!

የገበሬው ደብዳቤ እጅግ በዕድሜ የገፋ ብቻውን የሚኖር ጣሊያናዊ ገበሬ አባት በእስር ቤት ለሚገኘ | 🇰 🇦 🇱 🇺 🇹 🇺 🇧 🇪

የገበሬው ደብዳቤ

እጅግ በዕድሜ የገፋ ብቻውን የሚኖር ጣሊያናዊ ገበሬ አባት በእስር ቤት ለሚገኘው ብቸኛ ልጁ ደብዳቤ ይፅፋል።
"ልጄ ያው በዚህ አመት ድንችና ቲማቲም መትከል አልችልም ምክንያቱም ማሳውን የማረስ አቅም ስለሌለኝ፣አንተ ግን እዚህ ሆነህ ቢሆን ኖሮ ልትረዳኝ እንደምትችል አውቃለሁ።" ሲል ፃፈለት

ልጅም ለአባቱ ሲመልስ:-"አባቴ ሆይ፥ማሳውን ለማረስ ፈፅሞ እዳታስብ ምክንያቱም የሰረቅኩትን ገንዘብ እዛ ስፍራ ቀብሬዋለሁና!" በማለት መለሰለት
ታድያ በነጋታው የእስርቤቱ አለቃና ፖሊሶች ልጅና አባት የሚመላለሱትን ደብዳቤ ቀድመው አንብበው ነበርና በጠዋት ተነስተው ወደ ስፍራው በማቅናት ገንዘቡን ለማግኝት ከዳር እስከ ዳር ማሳውን ቆፈሩት፣ነገር ግን ምንም አይነት ነገር ሊያገኙ አልቻሉም።
በቀጣይ ቀንም ልጅ ለአባቱ ደብዳቤ ፃፈ:-"አባቴ አሁን ድንችና ቲማቲሙን መትከል ትችላለህ፣እዚህ ሆኜ ላደርግልህ የምችለው ትልቁ ነገር ይህንን ነው።"
አባትም መለሰ:-"ልጄ ሆይ፣በርግጥም ብርቱ መሆንህን አውቃለሁ እስር ቤት ሆነህ እንኳን ለኔ ፖሊሶችን ታዛለህ፣የእስርቤቱ አለቃና ጀሌዎቹ አካፋና ዶማ ይዘው ማሳውን ሲቆፍሩ በማየቴ ተገርሜያለሁ የመህር ጊዜ ሲደርስ ምርቱን ለመሰብሰብ ስፈልግ ደሞ እፅፋልሀለሁ።"

ልብ በል

ሰዎችና ሁኔታዎች አካልህን ያስሩ ይሆናል፣ነገር ግን አዕምሮህን ፈፅሞ ሊያስሩ አይችሉም።
አእምሮህ ታስሮ ከሆነ ግን እንዲለቅህ ራስህን ጠይቀው፣ያለፈቃድህ አእምሮህን ማሰር የሚችል ኃይል የለምና።

ትልቁ ሀይልህ የሆነውን አእምሮህን ያለመሰሰት ሁልጊዜም ተጠቀምበት

@kalu_Funny
@kalu_Funny