Get Mystery Box with random crypto!

#አትፍረድ ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) Part ➋➌ ሄለው፡ ሄለው አብዲ እንዴት አደ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#አትፍረድ

ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➋➌

ሄለው፡
ሄለው አብዲ እንዴት አደርክ
ደህና አልሃምዱሊላህ፡ አንተስ?
ደህና ነኝ፡ አብዲዬ እኔ ምልህ እ.. አብርሽ አርፏል።
ማለት? ስል የተናገረው ነገር ቀልድ ይሁን ቁምነገር ለማረጋገጥ በድጋሚ፡፡
አርፏል ማለት?።
አብዲ እኔም እንዳንተ ነበር ሲነገረኝ ለማመን ያቃተኝ።
ኦው በእናትህ፡ እኔ ለማመን እየከበደኝ ነው።
ብታምን እመን ባታምን ስራ ያውጣህ ለማለት የፈለገ በሚመስል መልኩ፡ በቃ ቢሮ ስትደርስ ደውልልኝ ብሎ ስልኩን ዘጋወ። ከእሱ ውጭ ለሌሎች ከጓደኞቻችን ደወልኩ ሁሉም እያዘኑ ነገሩ እውነት እንደሆነ ነገሩኝ።

አብርሃም በጣም ያሳዝናል በመጠጥ ውስጥ እራሱን ደብቆ ህይወቱን ገና ለጋ ወጣት ሳለ ቀጠፋት አልኩ፡ ድጋሚ ሆስፒታል የገባ ጊዜ አንድም ቀን ሄጄ ባለመጠየቄ እየተቆጨው።

የአበርሽን መሞት ያመጣውን ሀዘን ከቤተሰቡ ጋር በመጋራትና በማፅናናት ቀናቶች አለፉ።

ሰአዳ የት እንደገባች አላውቅም ስልኳ አይሰራም፡ በአካልም ከዛች አንድ ቀን ውጭ፡ እኛ ሰፈር ውስጥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ካየዋት በኋላ ተመልክቻት አላውቅም ፡እሱ ነገር ለኔ ምላሽ ያጣ ጥያቄ ነው፡ናዲያን ሳስታውስ ሰአዳ የዛኔ ሀኒም ሱቅ ለምን መጣች እላለሁ።

ሀኒም ያገባኛል ብላ በጉጉት ቀናቶችን ትጠብቃለች፡ እኔም በአፌ ቀባቀባ እያደረኩ ልቧ ላይ ነግሻለሁ።

ዛሬ እሁድ እንደመሆኑ፡ እረፍቴን ከእናቴ ጋር ነበር ያሳለፍኩት፡ ከሀኒም ጭቅጭቅ ለማምለጥ እና ወንድሟን የእጁን እንዲያገኝ ከማሰብ የተነሳ፡ ከእናቴ ጋር በመነጋገር ፡ዳግም ከውልደት ጀምሮ ወዳደኩበት ቤት በስራ ምክንያት ልመለስ እንደምፈልግ ነገርኳት። እናቴ ደስታዋ አስደናቂ ነበር፡በዚህ ደስታዋ ውስጥ፡ በፊትም ከጎኗ ስለይ ደስተኛ እንዳልነበረች ተረዳሁ።

አሁን የሚቀረኝ ነገር ሀኒም ሱቅ የማትገኝበትን ቀን ተገን በማድረግ እቃዬን ይዤ ቤቱን ለአከራዬ አስረክቤ ውልቅ ማለት ነው። ግን ነገሩ አድካሚ ነው።

ከ ቢሮዬ ሆኜ ስለ እቤት መቀየሩ ሀሳብ ውስጥ ባለሁበት ሰአት አንድ መላ መጣልኝ። ሀኒምን እሁድ ቀን ለሽርሽር በሚል ከአዲስ አበባ ይዞ መውጣት።

ማምሻውን ከሀኒም ጋር በስልክ ማውራት ጀመርኩ ያሰብኩትን እቅድ በመሃል ፃፍኩላት፡ መልሷ ለአንድ ቀን ችግር የለውም፡ ሱቅም ቢሆን እዘጋለሁ፣ ወንድሜም ሰሞኑን ስለሌለ፣ ማሜ እሺ ካለኝ እሱ እንዲገባ አደርጋለሁ፡ ካልሆነ ግን እዘጋለሁ ግን በጊዜ ነው የምንመለሰው? አለች።

ዛሬ ከቢሮዬ አጠገብ ካሉት ምርጥ ጓደኞቼ መሃል ከቴዲ ጋር እቤት ልቀይር እንደሆነና፡ የዛን ጊዜ እኔ ስለማልኖር እሱ ሃላፊነቱን ወስዶ እቃውን በጠቅላላ መኪና ተከራይቶ ከእናቴ ቤት እንዲያደርስልኝ በንግግራችን መሃል ጠየኩት፡የኔ መኖር መልካም መሆኑን ከገለፀልኝ በኋላ፡ ካልተመቸህ ግን፡ ሲል ያለምንም ንትርክና ማቅማማት ተስማማ።

ከሀኒም ጋር ከከተማ የምንወጣበት ቀን በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ሲቀሩ፡ለአከራዬና ለጊቢው ኮሚቴ ነገሩን አሳወኩኝ።

ቅዳሜ ምሽት ላይ የቤቴን ቁልፍ ለቴዲ ሰጥቼው ሁሉንም እቃዎች አዘገጃጅቼለት አደርኩ።

እሁድን ከሀኒም ጋር እዚሁ ከአዲስ አበባ ብዙም ሳንርቅ ደብረዘይት አካባቢ ለማሳለፍ በጠዋት ጉዞ ጀመርን። መኪና ውስጥ እንዳለን

ግን እኮ አብዲ መፍጠን አለብን አርግዣለሁ እኮ። አለች በጫወታ መሃል
ችግር የለውም የኔ ውድ ይህው በዚህ ሳምንት የሚያልቅ ጉዳይ ይሆናል አታስቢ። አልኳት እያወራን የነበረው ወደ ቤተሰቦቿ ዘንድ ወደ ሚላኩት ሽማግሌዎች ነበር።
እሽ የኔ ውድ አለች ፈገግ ብላ። ያለቅጥ የጥቆረውን ፀጉሯን ግንባሯ ላይ በከፊሉም ቢሆን እያሳየች።

ደስ የሚል ጊዜ በደብረዘይት ላይ አሳልፈን ወደ አዲስ አበባ አመሻሹ ላይ መመለስ ጀመርን።

እንዴት ነበር ውሎ። ስል ጠየኳት። ከፊት ለፊቴ አይኔ ላይ ልጠልቅ ያለችው ጀንበር ነፀብራቋን ለመከላከል መኪናው ውስጥ ያለውን የፀሃይ መከላከያ እንደጦር ከሚዋጋው ጨረር ለማምለጥ እያስተካከልኩ።
በጣም ደስ ይላል ከሰርጋችን በኋላ እንደምንደግመው አልጠራጠርም።
እንዴ እረ ብዙ ቦታ አለ። አልኳት የውሸት ሳቅ እየሳኩላት።

እንዲህ እየተጨዋወትን አዲስ አበባ ገባን ሀኒምን የቤታቸው ደጃፍ ላይ አድርሻት ወደ ቤቴ ተመለስኩ በአንድ እጄ መሪ በአንደኛው እጄ ስልኬን በጆሮዬ ላይ አስደግፌ ከቴዲ ጋር አወራ ጀመር።

ከአንድ ፍራሽ በስተቀር ምንም አይነት እቃ ሳያስቀር እንደነገርኩት ከእቃ ጫኝና አውራጆች ጋር በመሆን ወደ እናቴ ጋር እንዳደረሰልኝ ነገረኝ። አመስግኜ ነገ እንገናኛለን በቃ ስል፡ ስልኩን ዘጋሁት።

ሰኞ ነው። ሰአቱ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ይላል አከራዬ ወደ እኔ ቤት መጣ በመውጣቴ ቅር የተሰኘ ቢሆንም የእኔ እግር ቤቱን ለቆ ሳይወጣ ሌላ ተከራይ ከደላላ ጋር ከተፍ አለ። እኔ እሱን ተሰናብቼ የነበረችኝን አንዲት ትንሽዬ ፍራሽ ጠቅልዬ ይዤ ከቤቱ ወጣሁ፡

ከመኪናዬ ጋር እንደደረስኩ ከውሃላ ኪስ ውስጥ ፍራሹን ከትቼ ወደሀኒም ሱቅ ሄድኩ። ይሄ የመጨረሻ የምንተያይበት ቀን ነው።
ወደ ሱቁ እንደገባሁ ሀኒም ደስ በሚል ፈገግታ ተቀበለችኘና
አብዲዬ ስራ አይረፍድብህም እንዴ?
እ ተኝቼ እኮ ነው ባክሽ ትላንትናም ትንሽ መንገዱም አድክሞኝ ነበር።
አይዞህ በቅርቡ የምትቀሰቅስህ ሚስት ትኖርሃለች እና አሁን ልትሄድ ነው።
አዎ።
በቃ ማታ ስለትላንትናው ውሎ እናወራለን እንዳታረፍድ።
ሀኒም ይሄ የመጨረሻችን መሆኑን ብታውቅና ደስ በተሰኘው አልኩ በሆዴ።

ስራ ገብቼ እንደወጣሁ ወደ ጀሞ ሳይሆን ወደ እናቴ ቤት ሄድኩ። አዲስ የስልክ መስመር አውጥቼ የበፊቱን አዘጋሁት፡ አሁን የሀኒም ስቃይ "ሀ" ብሎ ይጀምራል።

ከእናቴ ጋር መኖር ከጀመርኩ ወራቶች ተቆጠሩ፡ አልፎ አልፎ ወደ በፊት ሰፈሬ እየተጓስኩ ሀኒምን ተደብቄ ለማየት እሞክራለሁ ግን አንድም ቀን አጋጥማኝ አታውቅም። የት ሄዳ ይሆን እንደ ናዲያ ሆና ይሆን እንዴ?። እያልኩ እራሴን በጥያቄ አጨናንቃለሁ። የእህት ነገር እና የወንድሟ በሀሪ አናዳጅ ሆኖ እንጂ ከሷ መለየት ፍላጎቴ ሆኖ አይደለም፡ ህይወቴን እንደዚህ የማስጨንቀው።

እሁድም ስለሆነ ብዙም ከቤት ለመውጣት አላሰኘኝም። እናቴ በጠዋት እድር ለመክፈል ወጥታለች፡ ከበረንዳው ላይ ሆኜ ጊቢውን በዝምታ እየቃኘሁ ሳለ የጊቢው በር ይንኳኳ ጀመር ከሰራተኛዋ ቀደም ብዬ ወደ በሩ በመሄድ የተዘጋውን በር ያለምንም ንግግር ከፈትኩት ሀኒምና ሰአዳ....

Part ➋➍ ይቀጥላል !

any comments
@kaludi_bot


@kalidoyeumi
join telegram