2022-07-30 15:05:09
ወንጌል ከመስማትና ከማንበብ ምን አዘገየን ምንስ አደከመን
እግዚአብሔር ደሙን አፍስሶ ነጻ አወጣን
ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ በቀላሉ ልናየው የማይገባ እጅግ ትልቅ ነገር ነው ታዲያ ክርስቶስ ይህን በዋጋ የማይተመን እና በዋጋ የማይገለጽ እጅጉን ከባድ ውለታ ሰጥቶናል፡፡
እኛስ ምን ያክል
ተገንዝበናል
ጌታችን በምንም አይደለም የገዛን በደሙ ነው!
ከሲኦል ነጻ ወጥተናል ከባርነት ነጻ ወጥተናል እንደ ሀጢያተኛ ስንቆጠር የነበረበት ዘመን አልፏል መጋረጃው የጥል ግድግዳ በእርግጥ ፈርሷል ታዲያ እኛ በዘመነ ሐዋርያት ጊዜ አባቶቻችን ሐዋርያት የጻፉልን ወንጌል ይህንን ነገር በጉልህ ያስረዳናል ነገር ግን እግዚአብሔር ለብሉይ ኪዳን ሰወች ኦሪቱን በነቢያቱ እጅ አጽፍ በዘመነ ሐዲስ ደሞ ትምህርተ ወንጌልን ካስተማረ ቡሃላ ሐዋርያት ትምህርተ ወንጌልን ሰብከው አስተምረው ወንጌልን ጽፈዋል
እኛ ክርስቶስን የምንረዳበት የድህነታችን(የመዳናችን) ዜና የሆነውን ወንጌል ቅዱስ ወንጌል ጌታችን እጃቸው ውስጥ አስገብቷል ጽፈውታልም፡ማር(16:8).
እኛ ይህነን ወንጌል አንብበን የምናገኘው በረከት በራሱ ብጹዓን ያስብለናል ራዕይ(1:3).
ሌላው አይደለም የሚያነበው ብቻ እራሱ ብጹዕ ይባላል በማለት ቅዱስ ዮሐንስ ይነግረናል፡
ወንጌልን በማንበብ እራሳችን በዋጋ የተገዛን መሆናችንን በጥሞና እንረዳ ነገር ግን እኛ ወንጌልን ከመማር ይልቅ ወንጌልን ከማንበብ ይልቅ የልብ ወለድ እና የፈጠራ ተራ ወሬና ተረት አዘል መጽሐፍ በየ ገበያው በየሱቁ በየትራንስፖርቱ እየገዛን ቅንጭላታችንን ስንበርዝ እንውላለን የሚገርመው እነዚህ መጽሐፍቶች ከነ ደራሲው ሳይቀር የከሌ መጽሐፍ ሁለተኛው አልያም ሶስተኛው ህትመት አልወጣምወይ በማለት ይጠይቃል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሰው የሐዋርያት ስራ የሚባለውን መጽሐፍ ማን ጻፈው ብሎ አያቅም አንዳንዴም የሐዋርያት ስራ የሚባል መጽሐፍ መኖሩንም ከነ አካቴው አያውቅም፡፡
ነገር ግን የአለም ፈላስፋ የጻፉትን ተረት አንዳንዴም ከሐይማኖት የሚያስወጡትን እርኩሳን መጽሐፍ ለማንበብ አይታክትም የህይወት መሪ የሆነውን ቅዱስ ወንጌል ለማንበብ ይታክታል ወይ ከነ ጭራሹ ፍላጎቱ የተዘጋም አይጠፋም፡፡
ይሕ ነገር የሚመነጨው ከስንፍና እና እያወኩ ሐጢያት ከማደርግ ሳላውቅ ይሻለኛል በማለት የራሱን የቅድመ ሁኔታ እና ሐሳብ ያራምዳል፡፡
በነገራችን ላይ ለማወቅ(ለማንበብ) ፍቃደኛ ባለመሆን እራሱ ሐጢአታችን መሆኑ ተቀምጧል ሮሜ( 1:28).
የህይወት መጽሐፍ ቅዱስ ወንጌልን መማር ማንበብ በረከት እንጅ አለማንበብ እና ለማወቅ ባለመውደድ የሚገኝ ጥቅም የለም፡፡
ቅዱስ ወንጌል የህይወት ቃል እንጅ ሌላ አላማ የለውም ባለማወቅም የሚደረግ ስህተት ከስህተት ይቆጠራልጂ ከስህተት ሐጢአት እና ከመከሰስ አያድንም እንደውም ለማወቅ ባልወደዱት ላይ ቅጣት አለው ሮሜ1:28
አላዋቂነትም ከተጠያቂነት አያስመልጥም ምሳ1:22
ስለዚህ የእግዚአብሔር ወንጌል ሕይወት የሚያድን መንፈስ የሚየድስ ከእግዚአብሔር ሕብረት የሚመጣ ሰይጣንን የሚያቃጥል ጠላት የሚያሳፍር ከክህደትም የሚያስመልጥ የተበላሸ ሕይወትን ወደ ንስሃ የሚያደርስ አንደበተ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል እስትንፋሰ መንፈስ ቅዱስ የሆነ ቅዱስ ወንጌል ነው ስለዚህ ይህንን ወንጌል በማንበብ ሕይወትን ከተያዝንበት ነገር ነጻ እናውጣ ምክንያቱም ሰው ለተሸነፈበት ነገር ባሪያ ነውና (ቅዱስ ጴጥሮስ(2ኛጴጥ(2:19))).
ያሸነፈን ሱስ ከሆነ የሱስ ባሪያ ነን
ያሸነፈን ዝሙት ከሆነ የዝሙት ባሪያ
ያሸነፈን ክህደት ከሆነ የክህደት ባሪያ
.
.
.
ስለዚህ ለሐጢያት ባሪያ ከምንሆን ለክርስቶስ ልጆች ብንሆንስ?
ልጆች ከሆንን ደሞ ልጅ ያባቱን ይወርሳል (ቅዱስ ጳውሎስ(ሮሜ(8:17))).
https://t.me/Tmhrte_Tewahdo
253 views12:05