Get Mystery Box with random crypto!

- የእግዚአብሔር ስጦታ ከጳውሎስ ወደ ደቀመዝሙሩ ጢሞቴዎስ መተላለፉ በግልጥ የሚታይ ነው፡፡ ጢሞቴዎ | JUSTIN APOLOGETICS]

- የእግዚአብሔር ስጦታ ከጳውሎስ ወደ ደቀመዝሙሩ ጢሞቴዎስ መተላለፉ በግልጥ የሚታይ ነው፡፡ ጢሞቴዎስም ይኸንን ስጦታ በአንብሮተ ዕድ አስተላልፏል›› (H.H.Pope Shenouda III, On Priesthood, 1997, p.48)
#ተሞክሮው፡- በአርመንና በሕንድ የማላንካራ አብያተ ክርስቲያናትም ተመሳሳይ ቀኖና አለ፡፡ ሐዋርያዊ ክትትል አጥብቀው ይሰብካሉ፡፡ ከሕን ተገንጥለው በተሐድሶነት ከወጡት ፕሮቴስታንታውያን በቀር ወደ ካቶሊክ የሄዱትና ራሳቸውን ‹‹ጃኮባይት›› የሚሉትም ሐዋርያዊ ክትትልን አያስተሐቅሩም፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጥል አካሄዱ ላይ የኢኦተቤክ ቅሬታ ቢኖራትም ሐዋርያዊ ክትትልን በመጠበቅ ረገድ ግን የኤርትራ አበው ንቁዎች ነበሩ፤ ሐዋርያዊ ክትትል ካላት የኮፕቲክ (የገብፅ) ቤተ ክርስቲያን ሂደው ተሹመዋል፡፡
#ያረጋልና ብርሃኑ፡- ያረጋል አበጋዝ በመድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2፣ ብርሃኑ አድማስ በብላታ መርስዔ ኀዘን ለተዘጋጀውና በልጃቸው በተሰናኘው ‹‹የመጀመሪያው /ኢትዮጵያዊ/ ፓትርያርክ›› በጻፈው ቀዳሚ ቃል የሐዋርያዊ ክትትል ጽንሰ ሐሳብ ተዳስሷል፡፡ በቃል አጠቃቀም ረገድ ያረጋል ‹‹ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ›› ሲል ብርሃኑ በበኩሉ ‹‹ሐዋርያዊ ክትትል›› ይላል፡፡ ይዘቱ አንድ ነው፡፡ የያረጋል ቅጽ 2 መድሎተ ጽድቅ ‹‹ክርስቶስ ብቻ›› የሚለው ርእስ በጥሞና ሊነበብ የሚገባው ውብ የነገረ ክህነት ምንባብ አለበት፡፡
ፕሮፌሰር #ጌታቸው፡- ኦርቶዶክሳዊነትን ከሐዋርያዊ ክትትል ጋራ በጥብቅ አቈራኝተው ያዩታል፡፡ በዚህ ሐዋርያዊ ክትትል ያልተጓዘ ሁሉ ኢኦርቶዶክሳዊ ነው ይላሉ (አዲሱ የደቂቀ እስጢፋኖስ መግቢያ፣ በአንዳፍታ ላውጋችሁ 2ኛ ዕትም ተካትቶ የሚቀርብ)፡፡
--
ሲመተ ፕትርክና ወጵጵስና በጨረፍታ
--
(1) #ቅድመ_ሲመት፡- ይኸኛው ደረጃ የመምረጥና የመለየት/የመቀደስ/ ነው፡፡ ከምሰክሮችም መካከል በየሐዋ.ሥራ 13፡2-3 ‹‹የእግዚአብሔርን ሥራ ሲሠሩ ሲጾሙም መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን እኔ ለፈለግኋቸው ሥራ ለዩልኝ አላቸው›› የሚለው ቃልና በሐዋ.6፡6 ‹‹… ከእናንተ ወገን በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ምረጡ፤ ለዚህም ሥራ እንሾማቸዋለን፡፡›› በሚል የሰፈሩት ምንባባት ይጠቀሳሉ፡፡ አካላዊና አእምሮአዊ ጤንነት በተለይም ከሚጥል ሕመምና ከተላላፊ በሽታ የፀዳ መሆን፣ ቀድሶ ለማቁረብ የሚያስል አካላዊ ደኅንነት፣ የሃይማኖት ርትዐት፣ የአስተዳደር ችሎታ፣ ቤተ ክርስቲያንን ከመናፍቃን መጠበቅ የሚያስችል የትምህርት ዝግጅትና ምስጉን ጠባይን ከጥበብ አቀናጅቶ መገኘት በአጠቃላይ 8 የሚደርሱ መመዘኛዎችን ማሟላት ይጠይቃል፡፡ የግእዙና ከዐረብኛው ቅጅ በእንግሊዝኛ የደረሰን ፍትሐ ነገሥት እነዚህንና የመሳሰሉትን ቅድመ ሲመት መማሏት አላቸው የሚላቸውን፣ ከጵጵስና የሚያስቀሩና የማያስቀሩ መመዘኛዎች በአንቀጽ 4 እና 5 በዝርዝር ያኖራል፡፡ ምርጫው ከምዕመን እስከ ሊቀ ጳጳስ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን አካላት ድምፅ ያካትታል፡፡ በምርጫው ተቀራራቢነት ያላቸው ተወዳዳሪዎች የቀረቡ እንደሆነ እንደ ዘመኑ ይወሰናል፡፡ ውሳኔው በድምፅ ብልጫም ሊወሰን እንደሚችል ፍትሐ ነገሥቱ ደንግጓል (አንቀጽ 4፡57)፡፡ ድምፁ እኩል ከሆነ በታቦት ላይ ዕጣ መጣልም ሌላኛው አማራጭ ነው (አንቀጽ 4፡69)፡፡ በመመዘኛ ረገድ ግን ዘመኑ መናፍቃን የበዙበት ከሆነ በስብከቱ የተሻለውን፣ አስተዳደሩ የተጓደለ እንደሆነ በአስተዳደር የተመሰገነውን ማድረግ ይገባል፡፡ “ ይረስይዎ ኖላዌ ለዘይፈቅዶ ፍትሐ ዝኩ ዘመን …ጊዜ የሚፈቅደውን ይሹሙት … the needs of the time should be considered.” ዘመንን የዋጀ ምርጫን ሁሉም ቋንቋዎች ይተባበሩበታል፡፡ ለጵጵስና የሆነ እንደሆነ የሊቀ ጳጳሱንና የሕዝቡን ይሁንታ እንዲሁም ፈቃደ መንፈስ ቅዱስን ማግኘት ግድ ነው (ፍት.ነ.አንቀጽ 5፡90)፡፡ ይኸንን ድንጋጌ መተላለፍ ውጤቴ ግዝት መሆኑን የዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 91 ድንጋጌ ይናገራል፡፡
(2) #ጊዜ_ሲመት፡- በሲመቱ ጊዜ የሚኖርን ሥርዓት የሚመሩት ጳጳሳት ናቸው፡፡ ቢያንስ 2 ወይም 3 ጳጳሳት መገኘት አለባቸው “ … his becoming a bishop is in the presence of two or three bishops.” ቀኖና ሐዋርያት /Apostolic Constitution/ ነው ፡፡ ሕዝቡም ተገኝቶ ሥርዓቱን በይፋ በገሐድ ይከታተላል፡፡ ጳጳሳቱ እጃቸውን ታጥበው ‹‹እኛ በዚህ በተመረጠ የእግዚአብሔር ባሪያ ላይ እጃችንን እንጭናለን - We lay our hands on this servant selected for God›› ብለው በአንብሮተ ዕድ እየባረኩት የሲመት ቅድምና ያለው እጁን በተለጫው እጩ ጳጳስ ላይ ጭኖ ለሲመቱ የተገባውን ጸሎት ሲያደርስ ሕዝቡ በልዑል ዜማና በንባብ ‹‹ይገባዋል-ይደልዎ/አኪዎስ/›› ይላሉ (ፍት፣ነ.አንቀጽ 5፡101)፡፡ አብነቱ ከቅዱስ መጽሐፍም በ2ኛ ጢሞ.1፡6፡- ‹‹… #እጄን_በአንተ_ላይ_በመጫኔ ያገኘኸው የእግዚአብሔር ጸጋ›› በሚል እንዲሁም በ1ኛ ጢሞ.4፡14 ‹‹… #በጳጳሳት_እጅ_መጫን_የተሰጠህን በአንተ ላይ ያለውን ጸጋ አታቃልል›› የሚል ምስክር አለው፡፡ ሐዋርያት የተመረጡትን በአንብሮተ ዕድ መሾማቸው ‹‹በሐዋርያትም ፊት አቆሟቸው ጸልየውም እጃቸውን በራሳቸው ላይ ጫኑ›› ከሚለው የሐዋ.ሥራ.6፡6 በግልጥ የሚነበብ ነው፡፡ አንብሮተ ዕድ ግድ ነው! ቅዱስ ጳውሎስ እንኳ በጌታ ቢጠራም ክህነቱ ግን ከሐዋርት በአንብሮተ ዕድ ነበረ የተገኘ (የሐዋ.ሥራ 13፡2)! ወደ ንዑስ ርእሳችን ስንመለስ፡- ጸሎቱ ሲጠናቀቅ ተሰያሚውን ጳጳስ እጅ ይነሡታል፡፡ ልብሰ ተክህኖና መስቀል ይሰጠዋል፡፡ ቀድሶ ቆርቦ ያቆርባል፡፡
(3) #ድኅረ ሲመት፡- ጳጳስ አምስት ተልእኮዎች እንዳሉት ፍትሐ ነገሥታችን ይጠቅሳል፡፡ ከዐረብኛው ቅጂ ወደ እንግሊዝኛ ከተተረጐመው ባጭሩ ብንወስድ፡- ሃይማኖተ አበውን ባገናዘበ መልኩ መንጋውን ከመናፍቃን በትምህርት በምዕዳን መጠበቅና ማጽናት /duty to protect or sustain/፣ በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ በሚነሣ ክርክር በሥልጣኑ ልክ ፍርድ መስጠት /judgment/፣ ነዳያንን መፍቀድ /determine the needs of the needy/፣ ለሚገባቸው ሥልጣንን መስጠት/ to give positions of leadership/፣ ለሁሉም ጊዜ አለውና ከጸሎትና አስተዳደር ባሻገር ምዕመናን በግልም በማኅበርም ማነጋገርና ማጽናናት እንዲሁም ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት /Mnage public affairs/ ይጠቀሳሉ (Magmou al-Safawy Ibn al- Assal, p.8 ). የተልእኮው መዝጊያ ቃል፡- ‹‹አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› የሚለው የሐዋ.ሥራ 20፡28 መሆን ይችላል፡፡ ከሲመት በኋላ ከመንጋው ርቆ ‹‹ጸሎት ላይ ነኝ›› እያሉ መንጋው እንዲናውዝ መተው የሚገባ አይደለም! ሲመቱ፡- ቅድመ ሲመትም፣ ጊዜ ሲመትም፣ ድኅረ ሲመትም የሚገባውን መስመር ሊጠበቅ ግድ ይሆናል፡፡