Get Mystery Box with random crypto!

💎ስለ ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን✍

የሰርጥ አድራሻ: @join_maryam_amalajinet_telegram
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.40K
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ቻናል አላማ ስለ ድንግል ማርያም,ፃድቃን,መላእክት እና ሰማእይታት አማላጅነትና ገድል ተአምራታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን መመስከር ነው። ለህይወታችን ለሚገጥሙን ፈተናዎች አስተማሪና ጠቃሚ የሆኑ መልእክቶች ይገኙበታል።

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-06 09:55:53
ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡
ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡
6.1K views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 06:01:14
#ቅዳሜ_ስዑር
ከስቅለት በኋላ ያለው ይህ ቅዳሜ በተለያየ ስያሜ ይጠራል፡፡ ይኽውም ‹‹ቀዳም ስዑር›› ዐቢይ ሰንበት ቅዱስ ቅዳሜ እየተባለ ነው፡፡
1. ቀዳም ስዑር ይባላል፡፡ ይህ ስያሜ ሰንበት በአይሁድ መሻሩን ያመለክታል፡፡
2. ዐቢይ ሰንበት ይባላል፡፡ ሰንበት ዕረፍት ማለት ስለሆነ ይህም ቀን ጌታችን ሁሉንም ሥራ ፈጽሞ በመቃብር አርፎበታልና ትልቁ ሰንበት ለማለት ዐቢይ ሰንበት ተብሏል፡፡
3. ቅዱ ቅዳሜ ይሉታል፡፡ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታን በመቃብር ያኖሩት በማዘጋጀቱ ቀን ዓርብ
.ማታ ሰንበት ሲጀምር ሲል ነበር፡፡ ቅዳሜም ከገባ በኋላ እንደ ትዕዛዛቱ ሰንበት ስለሆነ አረፉ፡፡ (ሉቃ.23÷56)
.ሐዋርያት ጌታችን ከተያዘ ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ድረስ እህል አልበሉም በዚሀም መሰረት በቤተክርስቲያናችን ከዓርብ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ድረስ እህል አይበላም፡፡ ይህም አክፍሎት ተብሎ ይጠራል፡፡ ሕዝቡ ከጾመው ምግብ በካህኑ በኩል ለድሆች ማካፈል እንደሚገባው ያመለክታል፡፡ ጌታችን ‹‹ሙሽራው የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ›› ብሎ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ (ማቴ9÷15)
በዚህ ዕለት ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን የምናስብበት ብርሃነ ትንሣኤውን የምንናፍቅበት ቀን መሆኑን አንዘንጋ፡፡
ክርስቲያኖች ቅዳሜ ጠዋት በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው ጸሎቱ ሲፈጸም “ገብረ ሰላመ
በመስቀሉ- ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ፤ ሰላምን ፈጠረ፤ የምሥራች” ይባባላሉ፡፡
ለተሰበሰበ ሁሉ የምሥራች ምልክት የሚሆን ቄጤማ ይታደላል፡፡ ምእመናንም ይህን
እየሰነጠቁ በራሳቸው ያስሩታል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ላልመጡት ደግሞ ካህናት
በየበኩላቸው ልብሰ ተክኅኗቸውን ለብሰው መስቀልና ቃጭል ይዘው ቄጤማውን
“የምሥራች” እያሉ ይሰጣሉ፡፡
6.3K views03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 15:37:43
ተፈፀመ
" ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 19:30)
6.1K views12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 14:54:34
ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
6.3K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 07:00:52
ጌታዬ ሆይ! ልዑል አምላክ ስትሆን ዝቅ ብለህ የእኔን የባርያህን እግር ልታጥብ ፈቀድክን? እንግዲያውስ እጄንና ራሴን ጭምር እንጂ እግሬን ብቻ አትጠብ። አባቴ ሆይ የቆሸሸው ልቤን፥ ያደፈችው ነፍሴን መላ አካላቴን እጠበኝ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም።
6.2K views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 20:12:17
በህማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይስ ለምን አናማትብም ?
የመስቀል ክብር እና ሐይል የታወቀው ጌታ በመስቀል ከተሰቀለ በሗላ ነው፡፡ በሰሞነ ህማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የአመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው፡፡በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ህማማት በቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ ማማተብ ስርዓት አይደለም፡፡
  በሰሞነ ህማማት ለምን አንሳሳምም?
ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷል እኛ ግን እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማስረዳት ከዚህም በተጨማሪ ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰምነ ህማማት እስከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም፡፡

በሰሞነ ህማማት የማይደረጉ ሌሎች ነገሮች ምን ምን ናቸው? ማንኛውንም ለስጋ የሚያደሉ ተግባራትን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜያችንን የጌታን ህማም መከራ በማሰብ በፆም በፀሎት በስግደት ማሳለፍ ፤ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ አለብን
8.7K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 10:51:48
ሆሳዕና ከባእለ ትንሳኤ አንድ ሳምንት ቀድሞ በሚውለው እሁድ ይከበራል
ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
8.9K views07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 19:13:05
የዓብይ ፆም 7ኛ ሳምንት ኒቆዲሞስ
በዚህ ሳምንት እንደ ኒቆዲሞስ ያሉ
ዓለማዊ የመሠሉ ጠንካራ  ክርስቲያኖች ይዘከራሉ።
ኒቆዲሞስ ምሁር ነው፤ ባለሥልጣን ነው፤ ሀብታም ነው።
የፈሪሳዊ ዘር ሆኖ ክፋት አላሸነፈውም።
ቀን ዓለማዊ ሥራውን እየሰራ ሌሊት ወደ ክርስቶስ እየሄደ ሃይማኖትን ይማራል። 
እውቀቱ፣ ሥልጣኑ፣ ሀብቱ ... ለሃይማኖቱ እንቅፋት አልሆኑትም።
ሥልጣን ሲይዝ የሚመራውን ሕዝብ ራሱ  የፈጠረ የሚመስለው፣
በገንዘቡ ሰውን ሁሉ የሚገዛ የሚመስለው፣ በእውቀቱ ፈጣሪን ያወቀ የሚመስለው ፣
በበዛበት ዓለም ክርስቲያን ሆኖ መገኘት መታደል ነው።
13.6K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 08:15:04
የአለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድን ነው?
የአብይ ፆም አምስተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት
መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ስለ ዳግም ምፅአት ያስተማረበት
...............................
የአለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድን ነው?
ይህን ሁሉ ታያላችሁን እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።
እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።
ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤
እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
፤ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
፤ በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤
፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤
፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።
፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።
፤ ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 24 ቁ1-14
12.9K views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 19:53:54 የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡
«ዘወረደ» ማለት «የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡

ዮሐ.3-13፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ”ገላ 4፥4 እንዳለ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ። ይህ ጾም የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡ ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው።እኛም በዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀር እንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ።በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ በሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም በመፆም ልዑል እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።
ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡
13.0K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ