Get Mystery Box with random crypto!

ይህን መልእክቴን ለእህቶቼ አድርሱል # ብርቱ ሴት ውብናት .... ብርቱ ሴት ዋጋዋን ጠንቅቃ ታ | #Fire🔥 Embassy Girum Révíväll🇪🇹🔥🔥

ይህን መልእክቴን ለእህቶቼ አድርሱል
# ብርቱ ሴት ውብናት ....
ብርቱ ሴት ዋጋዋን ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ ራሷን በቁስ አትተምንም፡፡ እልፍ ግዜ ወድቃ ደግማ... ደጋግማ የተነሳች ናት፡፡ በመሰናክል አትበገርም፣ፅኑ ናት፡፡ ከመንገዷ የሚገታት አንዳች ሀይል የለም፡፡ ክህደት ፣ አሉባልታ፣ ትችት አያዝሏትም፡፡ ህልመኛ ናትና ህልሟን ለመኖር ሰርክ ትተጋለች፡፡ ከእውነት ጋር ትጓዛለች እንጂ በነፈሰበት አትነፍስም፡፡
ከብዙ ስህተቶቿ ብዙ የተማረች ፣ በፈተና የተሞረደች ናት....ብርቱ ሴት፡፡
ብዙ ያነባች ብትሆንም... ፈገግታ ጌጧ ነው፡፡ እርሷ ላመነችበት ቆራጥ ፣ ለወዳጆቿ ሟች ናት፡፡
# ብርቱ ሴት ውብናት ....
@jesussssssssssssss