Get Mystery Box with random crypto!

#እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ራሱ ሲከብርበት እንዴት ያምራል። እንደዛ ሳይሆን ሲቀር አግባብ አለመሆ | #Fire🔥 Embassy Girum Révíväll🇪🇹🔥🔥

#እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ራሱ ሲከብርበት እንዴት ያምራል። እንደዛ ሳይሆን ሲቀር አግባብ አለመሆኑ ፣ ማሳፈሩ ፣ ማስቀየሙ እንደተጠበቀ ሆኖ በውጤቱም ማስጠየቁ እና ውርደት ማስከተሉ አይቀርም!!!! ጌታ እንዲህ ባለው ጉዳይ ደስ አይሰኝማ!!!!!!

ይኸውልህ ዘጸአት 32 ላይ ሙሴ በተራራ ቆየብን ብለው አሮን አምላክ (ጥጃ) እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ እኮ ያመጡት ወርቅ እና ጉትቻ ከየትም አይደለም፤ እግዚአብሔር አስበዝብዟቸው እንጂ!!! ተመልከት እንግዲህ እርሱ ከግብጻውያን  ባስበዘበዛቸው (ባሰጣቸው) መልሰው ሊያስከፉት ጥጃ ሲሰሩበት።

ደግሞ ልጨምር አንድ  " 2ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 11 ላይ ቤርሳቤህን ያስጠራት ዳዊት ሳይሆን ስልጣኑ ነው። እረኛ እያለ ቢያስጠራት ትመጣ ነበር?! የማስጠራት አቅምስ ነበረው???? "። እውነት እኮ ነው .... ጌታ በሰጠው ስልጣን እኮ ነው ያጠፋው። ለዛስ ሳይሆን ይቀራል መዝሙር 51 ላይ ነሰሃ ሲገባ " ..... አንተን ብቻ በደልኩ ያለው"

መልእክቴ ይህ ነው ....  እርሱ በሰጠን ነገር እርሱ ይክበርበት። ከተሳሳትንበት መንገድ ይመልሰን። ምንስ ከእርሱ ያልተቀበልነው አለና!!!!!

እኔ በዚህ አቅጣጫ አምላኬን እያወራሁም፤ ጸጋም እየጠየቅኩ ፤ ይቅርታህንም እያልኩ ነው።

ምንአልባት አንድን ሰው ከቀሰቀሰ ብዬ ወዲህ አምጥቸዋለሁ።

ይሁንልን!!!!!! እወዳ ቹሀለው
ሼር
Fire Embassy
join_us_Now
                Join us
@jesussssssssssssss
@jesussssssssssssss
@jesussssssssssssss
              ይ ላ ሉን