Get Mystery Box with random crypto!

‹‹በዛ ጥርጣሬ አይግባዎት ጋሼ…ምን አልባት ጊዜ ሚያመጣውን ነገር ምን እናውቃለን..እኔም ልክ ንግ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

‹‹በዛ ጥርጣሬ አይግባዎት ጋሼ…ምን አልባት ጊዜ ሚያመጣውን ነገር ምን እናውቃለን..እኔም ልክ ንግስት እንደወሰነችው አይነት ውሳኔ ወስን ይሆናል››
ፀጥ አሉ…ይሄንን ከእሷ አንደበት ለዛውም እንዲህ በቅርብ እሰማለው ብላው አስበው አያውቁም ነበር
‹‹ጋሼ አሉ?››
‹‹አዎ.አለው፡፡ ልጄ እኔ የፈለግሽውን ውሳኔ ብትወስኚ ከጎንሽ ነኝ..….ከአባትሽ ገር የገባሽውን ውል አውቃለው…ልብሽን የሚያቀልጠውንፍቅርሽን እስክታገኚ ድርስ እኔ ጉያ ለፈለግሽው ያህል ጊዜ ልትሸሸጊ ትችያለሽ…››
እንባዋ መጣ‹‹አመሰግናለወው ጋሼ…ይሄንን በመስማቴ የእውነት ደስ ብሎኛል…በሉ ደህና ይቆዩልኝ. ማታ ደውልሎታለው››
‹‹እጠብቅሻለው‹‹አሏት ልክ በፍቅር ያቀለጠችውን ፍቅረኛውን እንደሚሰናበት ወጣት አፍቃሪ በለሰለሰ ድምፅ
///


ይቀጥላል....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj