Get Mystery Box with random crypto!

መልካም ነገሮች የሚኖሩት ክስተቶች ላይ ሳይሆን በልባችን ውስጥ ነው። መልካም ዐይን ሲኖረን በሁሉም | የትም ብትሆን አላህን ፍራ

መልካም ነገሮች የሚኖሩት ክስተቶች ላይ ሳይሆን በልባችን ውስጥ ነው። መልካም ዐይን ሲኖረን በሁሉም ነገር ላይ ያለውን ውበት እናያለን።
ሰይድ አቡበክርና አቡጀህል በእኩል አንድን ክስተት አይተዋል፤ ሰይዳችን ሙሐመድን [ﷺ]።
ዐይናቸውና ልባቸው ግን ተለያይቷል። አቡበክር በንፁህ ልብ ውበትን ለማየት በታደለ ዐይን አዩ። አቡጀህል በቆሻሻ ልብ ውበትን ማየት በማይችል ዐይን አየ።
ውሳኔያቸውም ተለያየ!
መልካሙን እይ። ክፉን ሸፍን።
ከፈለጉ ሞኝ ነው ይበሉህ፤ አንተ ግን በጎ አስብ!
:
『መልካም ጁምዓ』
@iteqillahk