Get Mystery Box with random crypto!

በደንብ አንብብናና ለሙስሊም ጓደኞችህ አካፍላቸው!!! የዚህን ትርጉም ለሁሉም ግልፅ እንዲሆንና | Un–rey&una–reiner official👑👑

በደንብ አንብብናና ለሙስሊም ጓደኞችህ አካፍላቸው!!!
የዚህን ትርጉም ለሁሉም ግልፅ እንዲሆንና ሙስሊሞች ሁሉ ከዚህ ሙሲባ ሸር እንዲርቁ ብዙ ሙስሊም ወገኖቻችን ተገናኝተው ሲለያዩ አሰላሙ አለይኩም ከማለት ፋንታ የሚጠቀሙትን (buy) ባይ የምትለዋ ቃል ትርጉሟንና አደገኝነቷ ታውቃለህን? እኛ ሙስሊሞች ሳናውቅ አውሮፓዊያኖችን እየተከተልን አደጋ ላይ ስንወድቅ ተመልከቱ ነቢያችን صلى الله عليه وسلم ሀዲሳቸው ላይ እንዲህ ይላሉ (( የሰው ልጅ አንዲት ንግግርን ይናገራል ምንም ቦታና ትኩረት ሳይሰጣት ነገር ግን የሰባ አመትን ያክል የጀሀነም እሳት ውስጥ ይዛው ትወርዳለች )) አሉ። እና ይቺ ባይ የምትለዋ ቃል ትርጉሟ ካየን ፦ ጳጳሱ (ቄሱ) ጥበቃቸው ስር ያርጉህ ብሎ ዱአ ማድርግን ነው ፣እኛ ሙስሊሞች ጠባቂያችን الله ብቻ ነው ከሱ ውጪ ጥበቃን መፈለግ ሽርክ ነው እያልን ነገር ግን በዚች ቃል ብቻ ሳናውቅ ጠባቂያችን በሆነው በጌታች በ الله አሻርከናል አጋርተናል ማለት ነው። ስለዚህ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ልናረግለትና ሙስሊሞችን በሙሉ ልናስጠነቅቃቸው ግድ የሚሆንብን ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው ፣ ነፍሶችን ለማዳን ለቻልከው ሁሉ አስተላልፍ አድርስ አንተም ይቺን ቃል ዳግመኛ እንዳትጠቀማት ተጠንቀቅ ፣ አስበው ይህንን እያስተላለፍክ በ الله ፍቃድ ስንት ሚሊየን ሙስሊሞችን ለማዳን ሰበብ መሆን እንደምትችል፡ وفق الله الجميع