Get Mystery Box with random crypto!

ሐበሻው ቢላል ኢብኑ ረበሕ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈ | ኢስላማዊ እና ጠቅላላ እውቀት

ሐበሻው ቢላል ኢብኑ ረበሕ
(ረዲየሏሁ ዐንሁ)
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

ክፍል
❒❒ ❒❒


ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ግን ለኢስላም ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር የሚያኮራአቋም ከመውሰድ ወደ ኋላ አላለም። አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ የአንድ ሰው የቆዳ ቀለሙ መጥቆር ከፍተኛውን የኢማን ደረጃ ከማግኘት የሚያግድ እንደማይሆን በቢላል ረ.ዐ ተምሳሌት አስተምሯል። ቢላል ለዘመኑ ሰወችና ከእርሱ በኋላ ለመጣው ትውልድ እንዲሁ ም እምነት ለሚያጋሩትም ይሁን ለማያጋሩት ወገኖች ያስተማረው ትምህርት ቢኖር የህሊና ነፃነትና ሉዐላዊነት ምድርን የሞላ ንዋይም ሆነ አሰቃቂ ቅጣት ሊበግረው እንደማይችል ነው።

ቢላር ረዲየሏሁ ዐንሁ እርቃኑን በትኩስና አሸዋማ መሬት ላይ እንዲተኛና ቋጥኝ ድንጋይ ደረቱ ላይም እንዲጫን ተደርጓል። ግን እምነቱን ሊቀይር አልፈቀደም። በተከታታይ እና በተደጋጋሚ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ተፈፅሞበታል። የቁረይሽ ሹማምንት አንድን ባርያ ሊያ ሳምኑና ወደ ቀድሞው እምነቱ ሊመልሱት ባለመቻላቸው ቁጭትና ሀፍረት ስለ ተሰማቸው ክብራቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ቢላል ቢያንስ ቢያንስ ስለ አማልክቶቹ ጥቂት በጎ ነገር እንዲናገር ጠይቀውት አሻፈረኝ አለ።.

•••✿❒ ❒✿•••

ህይወቱን ቀስቃይ ምናልባትም ከሞት ለማዳን አማልክታቸውን ከልቡ እንኳ ባይሆን ማመስገን በቂ ነበር።ታላቁ ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ግን ከስጋዊ ህመም መንፈሳዊ የበላይነትን በመምረጡ ለጠላቶቹ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። ይልቁንም በተደጋጋሚ፦ "አሐድ....አሐድ..." በማለት የመለኮትን አንድነት ያውጅ ነበር።

"ላት" እና "ዑዝዛ" የተሰኙ ጣዖታትን እንዲያወሳ ያለ መታከት ይጠይቁታል። መልሱ ግን "አሐድ....አሐድ" ነበር። እኛ የምንለውን ደግመህ በል በማለት ይገርፉታል። በምፀታዊ ቃልም፦ እናንተ የምትሉትን ለመናገር ምላሴ አይችልም... ይላቸዋል። "ላት" እና "ዑዝዛ" ጌታዎች ናቸው ካልክ አንተንም እምነትህንም እንተዋችኋለን፣ በእርግጥ እኛ ራሳችን ስቃይ ተቀባዪች የሆንን ይመስል አንተን በማሰቃየት ደክመናል።" ፅንቅላቱን በመነቅነቅ "አሐድ...አሐድ" የሚል ምላሽ ከመስጠት ባሻገር እጅ አልሰጠም ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ።

•••✿❒ ❒✿•••

ቁረይሾች ተስፋ አልቆረጡም እናሰቃየው፥ እርሱ የኛ ወገን ነው። እናቱም የኛ አገልጋይ ነች። በመስለሙ እኛን የቁረይሽ መዛበቻ አያደርገንም። ቢላል ግን ለተንኮላቸው አልተንበረከከም ፦አሐድ.....አሐድ....." በማለት የ አላህን አሐዳዊነት ገለፀላቸው። ቁረይሾች ቢላል ነብሱን እስኪስት ድረስ ደበደቡት።

አቡበክር ረዲየሏሁ ዐንሁ ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ከሚሰቃይበት ቦታ ደረሱ ደብዳቢወችንም ወቀሷቸው፦"አንድ ሰው አምላኬ አላህ ነው! በማለቱ ብቻ ልትገድሉት ትሻላችሁን? ከዚያም ኡመያ ኢብን ኸለፍን፦ ቢላልን ከገዛህበት ዋጋ ጨምሬ እከፍልሀለው። ልቀቀው አሉት።

•••✿❒ ❒✿•••

ኡመያ በቢላል (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ተስፋ ስለቆረጠ ከሚገድለው ገንዘብ ቢያገኝበት የተሻለ መሆኑ ተሰማው፣ በአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ጥያቄ ከልብ ተደስቷል። አቡበክር ረዲየሏሁ ዐንሁ ቢላልን ከገዙት በኋላ ነፃነቱን አወጁለት። አቡበክር ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁን ተረክበው ሊሆዱ ሲሉ ኡመይያ እንዲህ በማለት ተሳለቀ፦ "በላትና ዑዝዛ ምላለሁ በአንድ ወቄት ወርቅ ካልሆነ አልገዛህም ብትለኝ እንኳን እሸጥልህ ነበር!" አቡበክርም (ረዲየሏሁ ዐንሁ)፦ "በአላህ ስም እምላለሁ! በመቶ ወቄት ወርቅ ካልሆነ አልሸጥልህም ብትለኝ ኖሮ የጠየቅከውን እክፍልህ ነበር።" አሉት።

አቡበክር ቢላልን (ረዲየሏሁ ዐንሁም) ወደ መልእክተኛው ﷺ በመውሰድ ነፃ መውጣቱን አበሰሩዋቸው ትልቅ ደስታ ሆነ። ነብዩ ሙሀመድ ﷺ ወደ መዲና ከተሰደዱ በኋላ "አዛን" ማሰማት አስፈላጊ ሆኖ በተገኘበት ወቅት ይህን ተግባር እንዲፈፅም አንድ ሰው መምረጥ ግድ ሆነ። የዘር አድሎ የማያውቀው ኢስላም ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ን በ "ሙአዚን"ነት መረጠ።

•••✿❒ ❒✿•••

በሙስሊሞች እና በቁረይሾች የነበርው ቅራኔ ወደ ወታደራዊ ፍጥጫ ተቀየረ። የቁረይሽ ሰራዊት ወደ መዲና ተመመ። በርካታ የቁረይሽ ሹማምንትም በጦርነቱ ተሳታፊ ለመሆን በሙሉ ልብ ተነስተዋል። ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሲፈፅም የነበረው ኡመያ ኢብን ኸለፍ ግን ከሀገሩ ለመውጣት ባለመፈለጉ ምክንያት ፈጥሮ ለመቅረት አስቦ ነበር።

ጓደኛውና በቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ላይ እኩይ ድርጊት እንዲፈፅም ሲያበረታታው የነበርው ዑቅበት ኢብን አቢ ሙዓይጥ የኡመያን በጦርነቱ ተሳታፊ ያለመሆን ሰማ። ሴቶች ጭስ የሚሞቁበት ሸክላ በመውሰድም ወዳጆቹ በተሰበሰቡበት እንዲህ አለው፦ "የዐሊይ አባት ሆይ! በዚህ ሸክላ ጪስ ሙቅበት፥ አንተ ሴት ነህ አለው።

ኡመያ የሀፍረት ማቅ መልበሱ ስለተሰማው፦ አንተንም ሆነ ይዘህ የመጣኸውን ነገር ፈጣሪ ያጥፋችሁ..." በማለት ብስጭቱን ከገለፀ በኋላ ወደ ጦር ሜዳ ለመዝመት ዝግጅት ጀመረ። ክስተቱ አስገራሚ ነው። ዑቅበት ኢብን አቢ ሙአይጥ በቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ እና ወገን ዘመድ በሌላቸው ሙስሊሞች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም የሚያበረታታ ሰው ነበር። ዛሬ ኡመያ ኢብን ኸለፍን ወደ በድር ጦርነት እንዲሄድ አስገድዶታል።

•••✿❒ ❒✿•••

ምንአልባትም የሁለቱም የህይወት ፍፃሜ ቀርቦ ይሆናል።
ውጊያው ተጀመረ። ሙስሊሞች "አሏሁ አክበር....አሐድ....አሐድ..." ሲሉ ይሰማል ኡመያ ይህን ቃል በሚገባ ያስታውሰዋል. ትናንት የቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ የጣር ድምፅ ነበር። አሁን ደግሞ የአዲሱ ትውልድ መፈክር ሁኗል። ልቡ ተሸበረ

•••✿❒ ❒✿•••

የተለያዩ ጣፋጭ አስተማሪና ኢስላማዊ
ታሪኮች የሚቀርቡበት ምርጥ ቻናል ነው።

•════••• •••════•
ሼር JoiN & Share
https://t.me/AAASELEFYA
https://t.me/AAASELEFYA