Get Mystery Box with random crypto!

❒ ሐበሻው ቢላል ኢብኑ ረባሕ ረዲየሏሁ ዐንሁ ┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈ | ኢስላማዊ እና ጠቅላላ እውቀት

❒ ሐበሻው ቢላል ኢብኑ ረባሕ ረዲየሏሁ ዐንሁ
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

ክፍል
❒❒ ❒❒

የአቡበክር (ረ.ዐ) ስም ሲነሳ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዲህ ይሉ ነበር፦

«አቡበክር ልዑላችን ነው። የኛን ልዑልም ነፃ አውጥቶልናል።»

ዑመር ረ.ዐ "ልዑላችን" ሲሉ ያሞካሹት ግለሰብ ታላቅ ሰው ነበር። እጅግ በጣም ዕድለኛ። ይህ ሰው እንዲህ አይነቱን የሙገሳ ቃል ሲሰማ ግንባሩን ደፋ፥ ዐይኑን ገርበብ በማድረግ "እኔ ትናንት ባርያ የነበርኩ የሀባሻ ሰው ነኝ" ይል ነበር። ለመሆኑ የትላንቱ የሀበሻ ባሪያ የዛሬው ልዑል ማን ይሆን ?

ቢላል ኢብኑ ረባሕ ነው። የኢስላም ሙአዚን እና የጣዖታት አሳፋሪ ሰው ነው። የእምነትና የእውነተኝነት (ኢማንና ሲድቅ) ወርቃማ ፍሬ ነው። በየትኛውም ጊዜና ቦታ ከሚገኙ ሙስሊሞች መካከል ቢያንስ ከአስር ሰባቱ ቢላልን ያውቁታል። ስሙን ዝናውን እና ሚናውን በሚገባ ያወሱታል።

•••✿❒ ❒✿•••

በሚሊዬን የሚቆጠሩ ሰወች አቡበክርንና ዑመርን (ረ.ዐ) እንደሚያውቁ ሁሉ የቢላልም ረ.ዐ ስም እንግዳ አይሆንባቸውም። ሕፃናትን ቢላል ማን ነው ብለህ ብትጠይቅ የረሱል ﷺ "ሙአዚን" ነው ይሉሀል። አሳዳሪው በ ጋለ ድንጋይ ላይ በማስተኛት ሲያሰቃየው ወደ ጥንት እምነቱ ከመመለስ ይልቅ "አሐድ...አሐድ... በማለት ፅናቱን የገለፀ ሰው ነበር የሚል ምላሽ ታገኛለህ።

•••✿❒ ❒✿•••

ይህ ሁሉ ታላቅ ዝናና እውቅናን ያተረፈው ቢላል ኢስላምን ከመቀበሉ በፊት በሕዝቡ ዘንድ ከእንስሳ ተለይቶ የማይታይ እና የተናቀ ባርያ መሆኑን ማስታወስ ያሻል። ቢላል ረ.ዐ ኢስላምን ባይቀበል ኖሮ የአሳዳሪውን ግመል ከመጠበቅ ሌላ የህይወት ሚና የሌለው፣ እንኳን ከሞተ በኋላ በሕይወት ዘመኑም አስታዋሽ የሌለው ሰው ሆኖ በቀረ ነበር።

ነገር ግን በእውነተኛ ኢማን በመታነፁ ፣ ታታሪና ቀና በመሆኑ የገባበትም ሀይማኖት እጅግ ታላቅ በመሆኑ ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ኢስላም ከሚያወሳቸው ድንቅ ሰወች መካከል በመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠቃሽ ለመሆን በቅቷል። እንዲሁም ከፍተኛ የታሪክ ሰወች የቢላልን ያህል ትውስታ አልተቸሩም።

•••✿❒ ❒✿•••

የቆዳው መጥቆር፥ የሙያውና የዘሩ እውቅ ያለመሆን፥ በሰወች ዘንድም ትናንት ነፃ የወጣ ባርያ መሆኑ ቢታወቅም ኢስላምን ከመረጠ በኋላም ወደ ከፍተኛ ደረጃና ማዕረግ ለመሸጋገር አላገደውም። እንደ ቢላል ዐረባዊ ያልሆነ ባርያ ዘመድና ኋይል የሌለው ሰው ለታላቅ እጣ ይበቃል ብሎ የሚገምት አልነበረም።

ከቁረይሽ ነገድ ውስጥ በታላቅነታቸው የሚታወቁና ኢስላምን የተቀበሉ ግለሰቦች ሲመኙት የነበረውን የረሱል ﷺ "ሙአዚን" የመሆን እድልም ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ማግኘቱ የሚደነቅ ነው።
ወደ ዋናው ታሪኩ እንግባ የቢላል እናት ጥቁር ሀበሻ ናት። የአላህ ውሳኔ ሆነና የበኒ ሹምህ ጎሣ አባል ለሆነ ሰው በባርነት ተመዘገበ። እናቱም የዚሁ ጎሳ ባርያ ነበረች።

•••✿❒ ❒✿•••

የቢላል ረ.ዐ እናት ጥቁር ሀበሻ ናት። የአላህ ውሳኔ ሆነና የበኒ ሹምህ ጎሣ አባል ለሆነ ሰው በባርነት ተመዘገበ። እናቱም የዚሁ ጎሳ ባርያ ነበረች። ዛሬ አንዳች መብት የሌለውና ለነገም አንዳች ተስፋ ያሌለው ተራ ባርያ ነበር-ቢላል ረ.ዐ ።

የሙሀመድ ﷺ ዜና ከቢላል ጆሮ መግባት ጀመረ። የመካ ሰወች በትኩስ ወሬነት የሚነጋገሩት ሙሀመድ ﷺ ነብይ ነኝ ብሎ የመነሳቱን ጉዳይ ነበር። አሳዳሪውና እንግዶቹም በዚሁ ርዕስ ጉዳይ ላይ ሲወያዩ ይሰማል። በተለይ ኡመያ ኢብኑ ኸልፍ የተባለው አሳዳሪው ተንኮል የተሞላበት ውይይትና ምክክር ከጥቂት ሰወችና ከበርካታ እንግዶች ጋር ሲነጋገር አድምጦታል።

•••✿❒ ❒✿•••

የቢላል ጆሮ ተሰብሳቢወቹ ከሚናገሩት የጥላቻ ንግግር ውስጥ ሙሀመድ ﷺ ስለተነሱበት አላማና ምን እያሉም እንደሚያስተምሩ ሊቀነጭብ ቻለ ። አዲስ የመጣው ዲን ለአካባቢው እንግዳና ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ያለመ ሙሀመድም ﷺ ምንም እንኳ ነብይ ነኝ ብለው በመናገራቸው ተቃውሞ የገጠማቸው ቢሆንም ታማኝ፥ እውነተኛና በጥሩ ሥነ-ምግባር የታነፁ መሆናቸውን ከጠላቶቻቸው ቁንጮወች አንደበት አድምጧል።

ሙሀመድ አንድም ቀን ዋሽቶ አያውቅም። ዝምተኛም ሆነ እብድ አልነበረም።...ዛሬ ግን እኛ እርሱን በነኝህ ነገሮች መጥራት ይኖርብናል-ወደርሱ የሚጎርፉትን ሰወች መግታት የምንችለው በዚህ መንገድ ነው" በማለት ሲዶልቱ ሰምቷቸዋል። ሙሀመድን ﷺ የሚቃወሙት በቅድሚያ የአባቶቻቸውን ዲን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲሆን። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የቁረይሽን የበላይነት የሚያከስም መሆኑ ስለ ተሰማቸው ነው።

•••✿❒ ❒✿•••

ቁረይሽ በመላው ዐረብ ለጣዖታዊው እምነት ማዕከል በሆነችው መካ የሚገኝ ነገድ በመሆኑ ተፈሪነቱና ከበሬታው የላቀ ነበር። በሶስተኛ ደረጃ በኒ ሀሺም ተብሎ በሚታወቀው የነብዩ ሙሀመድ ﷺ የዘር ሀረግ ቤተሰብ ላይ ያሳደሩት ቅናትና ምቀኝነት ነበር። ከበኒ ሐሺም ቤተሰብ ነብይና መልእክተኛ መምጣቱን እንደ ሽንፈት ቆጥረውታል። ሁሉም ቤተሰብና ጎሳ ነቢይ ከራሱ ወገን እንዲመጣ ይሻ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን ቢላል ኢብኑ ረባሕ ረዲየሏሁ ዐንሁ የኢማን ብርሀን ፈነጠቀበት። ምርጭልውን ይፋ ማድረግ እንዳለበት ወሰነ። ወደ ረሱል ﷺ በመሄድም ለኢስላም እጁን መስጠቱን ይፋ አደረገ። የቢላል መስለም በመካ ምድር ተሰማ። የበኒ ጀመህ መሪወች በቁጣ ተወጣጠሩ። በተለይ አሳዳሪው የኢስላም ጠላት ኡመያ ኢብን ኸለፍ ሀበሻዊው ባሪያው መስለሙ እንደታላቅ ነውርና ንቀት ቆጥሮታል።

ከዛም እንዲህ አለ "ይህ ኮብላይ ባሪያ በመስለሙ ፀሀይ ተመልሳ የምትጠልቅ አይመስለኝም.." ሲል ቁጭቱን ገለፀ። ቢላል ረዲየሏሁ ዐንሁ ግን ለኢስላም ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር የሚያኮራአቋም ከመውሰድ ወደ ኋላ አላለም። አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ የአንድ ሰው የቆዳ ቀለሙ መጥቆር ሳይሆን የሚመለከተው የልብን ንፅና ነው።

#ኢንሻአላህ #ይቀጥላል

•••✿❒ ❒✿•••

የተለያዩ ጣፋጭ አስተማሪና ኢስላማዊ
ታሪኮች የሚቀርቡበት ምርጥ ቻናል ነው።

•════••• •••════•
ሼር JoiN & Share
https://t.me/AAASELEFYA
https://t.me/AAASELEFYA