Get Mystery Box with random crypto!

የዙልሂጃ አስር ቀናት ትሩፋት እና በነዚህ ቀናት መተግበር የሚወደዱ ስራዎች * አላህ እንዲህ በማ | ኢስላማዊ እና ጠቅላላ እውቀት

የዙልሂጃ አስር ቀናት ትሩፋት እና በነዚህ ቀናት መተግበር የሚወደዱ ስራዎች

* አላህ እንዲህ በማለት ምሎባቸዋል። [ وَالْفَجْرِ وَلَيَالٍ عَشْرٍ] (በጎህ እምላለው በአስሩ ለሊቶችም) (አል ፈጅር)
* የታወቁ ቀናቶች ናቸው። አላህ እንዲህ ብሏል [وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ] (በታወቁ ቀኖችም ውስጥ የአላህን ስም ሊያወሱ) (አል ሀጅ)
* ከነዚህ ቀናቶች ውስጥ አንዷ የእርድ ቀን ናት። ይህም በአመት ውስጥ ከሚገኙ ቀናቶች ሁሉ ታላቅ ቀን ነው።
[أعظم الأيام عند الله يوم النحر ثم يوم القر]
رواه ابو داود والنسائي
(አላህ ዘንድ ታላቅ ቀን የእርድ ቀን ነው በመቀጠል የውመል ቀር ነው) አቡዳውድ እና ነሳኢይ ዘግበውታል ። የውመል ቀር ማለት የዙል ሂጃ 11ኛ ቀን ነው።
* በእነዚህ ቀናቶች የአምልኮዎች ሁሉ ቁንጮ የተባሉ ተሰብስበው ይፈፀማሉ። ከነሱም መሀል (ሶላት ፣ ፆም ፣ ሀጅ ፣ ሶደቃ)

@islamawe99
@islamawe99