Get Mystery Box with random crypto!

አብደላህ ኢብን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ክፍል > (ረሱል ﷺ) •• | ኢስላማዊ እና ጠቅላላ እውቀት

አብደላህ ኢብን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ክፍል

<< ቁርኣንን በወረደበት ዓይነት ለመቅራት የፈለገ ሰው እንደ ኢብን ኡም አብድ ይቅራ >> (ረሱል ﷺ)

•••✿❒ ❒✿•••

~ ገና ወጣት እያለ የጉርምስና ዕድሜውን ሳይጨርስ ዑቅባ ኢብን ሙዐይጥ የተባለውን የቁረይሽ ሹም የከብት መንጋወች በመጠበቅ በመካ የተራራ ሰርጦች ላይ ብቻውን መመላለስ ልማዱ ነበር። ሰወች "ኢብን ዑም አብድ" (የባሪያ እናት ልጅ) ብለው ይጠሩት ነበር። እውነተኛ ስሙ ዐብደላህ ሲሆን የአባቱ ስም መስዑድ ነበር። ወጣቱ በወገኖቹ መካከል ስለታዩት ነቢይ ወሬወችን ሰምቶ የነበረ ቢሆንም በዕድሜውና ከመካ ህብረተሰብ በመራቁ ምክንያት አንዳችም ትኩረት አልሰጣቸውም ነበር።የዑቅባህን የከብት መንጋ ይዞ ገና ማለዳው ላይ መውጣት ልማዱ የነበረ ሲሆን ካልመሸ ደግሞ አይመለስም።

•••✿❒ ❒✿•••

~ አንድ ቀን መንጋዎቹን እየጠበቀ ሳለ ሁለት መካከለኛ ዕድሜና ግርማ ሞገስ የተላበሱ ሰወች ወደ እሱ ሲመጡ ከርቀት አየ። እንደ ደከማቸው ያስታውቁ ነበር። ከመጠማታቸውም የተነሳ ከንፈሮቻቸው ክው ብለው ደርቀዋል። ወደ እሱ ቀርበው ሰላምታ ከሰጡት በኋላ "አንተ ወጣት፥ የውሀ ጥማታችንን ለመቁረጥና ጉልበት ለማግኘት ብንችል እስኪ እባክህ ከነዚህ በጎች መካከል አንዷን እለብልን አሉት። ወጣቱም "አልችልም! በጎቹ የኔ አደሉም። የኔ ሥራ መጠበቅ ብቻ ነው ሲል መለሰላቸው። ሁለቱ ሰወች አልተከራከሩትም። ምንም እንኳ በውሃ ጥም እጅግ ተሰቃይተው የነበሩ ቢሆንም ቀና በሆነ መልሱ እጅግ ተደሰቱ።

•••✿❒ ❒✿•••

ደስታቸው በፊታቸው ላይ ይታይ ነበር። በእርግጥ ሁለቱ ሰወች የተባረኩት ነቢይና ﷺ ጓደኛቸው አቡበክር ሲዲቅ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ነበሩ። የዚያን ቀን ወደ መካ ተራራወች የወጡት ከቁረይሽ ግፍና መከራ ለማምለጥ ነበር። ወጣቱም በተራው በነቢዩ ﷺ እና በጓደኛቸው ተደንቆ ወዲያውኑ ከእነሱ ጋር ተወዳጀ።አብደላህ ኢብን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ሙስሊም ሆኖ ለነብዩ ግልጋሎት ለመስጠት ፈቃደኝነቱን ሲገልፅ ብዙም አልቆየም። ረሱል ﷺ በነገሩ ተስማሙበትና ከዚያ ቀን ወዲህ እድለኛው አብደላህ የበግ እረኝነቱን ተወ። በምትኩም የተባረኩትና የተወዳጁ ነብይ ﷺ የቅርብ አገልጋይነት ዋና ስራው ሆነ።

አብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ ከነብዩ ﷺ ጋር የቅርብ ወዳጃቸው እንደሆነ ቆየ። በቤታቸው ውስጥና ውጭ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ያሟላ ነበር። መንገድ ሲሄዱና ዘመቻ ሲወጡ ያጅባቸዋል። ሲተኙ ይቀሰቅሳቸዋል። ሲታጠቡ ግርዶሽ ይሰራላቸዋል። ዕቃቸውንና የጥርስ መፋቂያቸውን ይይዝ ነበር። ሌሎች በግል የሚያስፈልጉ ዋቸውን ነገሮችም ያቀርብ ነበር። አብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) በነብዩ ﷺ ቤተሰብ ውስጥ ልዩ ስልጠና (ተርቢያ) ተቀበለ። በረሱል ሶለሏሁ ዐልይሂ ወሰለም አመራር ስር ነበር።

•••✿❒ ❒✿•••

"በፀባይ ረሱልን ﷺ እጅግ በጣም የሚመስል ነበር።" እስከሚባል ድረስ እያንዳንዱን የእርሳቸውን ባህሪ ተላበሰ። አብደላህ በነብዩ ﷺ "ትምህርት ቤት" ውስጥ ነበር የተማረው። ከሶሐቦች መካከል ቁርኣንን በመሸምደድ በላጩ እሱ ነበር።ከሁሉም በተሻለ ሁኔታ ተረድቶትም ነበር። ስለዚህ በኢስላማዊ ሕገ-መንግስት (ሸሪዓ) ላይ ከሁሉም የላቀ ከፍተኛ እውቀት ነበረው። ይህንን ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ በአረፋ ሜዳ ላይ ቆመው ሳሉ ወደ እሳቸው ከመጣውና እንደሚከተለው ከነገራቸው ሰው ታሪክ የተሻለ የሚያብራራ የለም፦ "የምእመናን መሪ ሆይ! ከኩፋ ነው የመጣሁት። የቁርኣኑን ቅጅወች ከአእምሮው እያፈለቀ የሚሞላ ሰው አጋጥሞኛል።" አላቸው። ዑመር እጅግ በጣም ተናደው በግመላቸው አጠገብ ይንጎባለሉ ጀመር። "እሱ ማነው?" ሲሉ ጠየቁት። "አብደላህ ኢብን መስዑድ ሲል መለሰ። የዑመር ቁጣ ወዲያው በረደ። ተረጋጉ። "በአላህ ስም እምላለሁ! በዚህ ጉዳይ ላይ ከእሱ የበለጠ አዋቂ ሌላ ሰው መኖሩን አላውቅም።

•••✿❒ ❒✿•••

ስለዚሁ አንድ ነገር ላጫውትህ" አሉ። ቀጠሉና "አንድ ቀን ማታ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከአቡበክር ጋር ሆነው ስለሙስሊሞች ይነጋገሩ ነበር። እኔም ከእነሱ ጋር ነበርኩ። ከጨረስን በኋላ ነብዩ ﷺ ሄዱ። እኛም ተከትለናቸው መስጊዱን አቋርጠን ስንሄድ እኛ ከሩቅ ያልለየነው በስግደት ላይ የቆመ ሰው ነበር። ነብዩ ﷺ ቆመው ሰውየው የሚለውን ከሰሙ በኋላ ወደእኛ ዞረው " ቁርኣንን በወረደበት ዓይነት ለመቅራት የፈለገ ሰው እንደ ኢብን ኡሙ አብድ ያንብብ" አሉ። አብደላህ ስግደቱን ጨርሶ ተቀምጦ ዱዓ እያደረገ ሳለ የአላህ መልእክተኛ ﷺ "ጠይቅ! ይሰጥሀል" አሉ።

ዑመር ንግግራቸውን ቀጠሉ..."ወደ አብደላህ ኢብን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ። በቀጥታ ሄጀ ፀሎቶቹ ሁሉ ተቀባይነት ስለማግኝታቸው ነብዩ ﷺ የ ተናገሩትን የምስራች እነግረዋለሁ ብየ ወሰንኩ። ነገርኩትም። ነገር ግን ከእኔ በፊት አቡበክር ሄዶ የምስራቹን ነግሮት እንደነበር ተረዳሁ። በአላህ ስም እምላለሁ! አቡበክርን ጥሩ ነገር በመስራት ፈፅሞ ቀድሜው አላውቅም።" አብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ አይነት ከፍተኛ የቁርኣን ዕውቀት ከማግኘቱ የተነሳ። "ከእሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ በሆነው እምላለሁ! እያ ንዳንዱ የቁርኣን አንቀፅ የት እንደወረደና የአወራረዱን ሁኔታ (ታሪካዊ አመጣጡን) እኔ ሳላውቅ አንዲትም የቁርኣን አንቀፅ አልወረደም።

•••✿❒ ❒✿•••

በአላህ ስም እምላለሁ! የአላህን መፅሐፍ የበለጠ የሚያውቅ ሰው መኖሩን ካወቅኩ ከእሱ ጋር ለመሆን የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ" ይል ነበር። አብደላህ ረዲየሏሁ ዐንሁ ስለራሱ የተናገረው እያጋነነ አልነበረም። ዑመር ኢብን ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ ኸሊፋ በነበሩበት ወቅት ካደረጉዋቸው ረጅም ጉዞወች መካከል በአንደኛው አንድ "ካራቫን" (ሲራራ ነጋዴ) ያጋጥማቸዋል። ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ ስለነበር የንግድ ቅፍለቱ በወጉ አይታይም ነበር። ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ አንድ ሰው ቅፍለቱን እን ዲያናግር አዘዘ። "ከየት ነው የምትመጡት?" ሲሉ ዑመር ጠየቁ፤ "ከፈጀል-ዐሚቅ" (ከጥልቅ ሸለቆ) የሚል መልስ ተሰማ።

•••✿❒ ❒✿•••

ፈጀል-አሚቅ የሚለው አገላለፅ ቁርኣናዊ ነው። "እና ወዴት እየሄዳችሁ ነው?" ሲሉ ዑመር ጠየቁ፤ "ወደ አል- በይተል-ዓቲቅ (ወዳ ጥንታዊው ቤት) የሚል መልስ መጣ። (አልበይት አልአቲቅ የሚለው አገላለፅም ቁርኣናዊ ነው።) በዚህ ጊዜ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ "ከነሱ መካከል የተማረ ሰው (ዓሊም) አለ።" ካሉ በኋላ ተጨማሪ ጥያቄ እንዲጠየቅ አዘዙ። " ከቁርኣን ውስጥ ታላቁ ክፍል የቱ ነው?"፦ የሚከተለውን የቁርአን አያት አነበበላቸው.....

#ኢንሻአላህ #ይቀጥላል

የተለያዩ ጣፋጭ አስተማሪና ኢስላማዊ
ታሪኮች የሚቀርቡበት ምርጥ ቻናል ነው።

•════••• •••════•
ሼር JoiN & Share
https://t.me/AAASELEFYA
https://t.me/AAASELEFYA