Get Mystery Box with random crypto!

                      ማርስ MARS                        ======== | IKEZ

                      ማርስ MARS
                       =========
ጎረቤት ማርስ ቅዝቃዜዋ ለጉድ ነው፡፡ በዚያ ላይ ከባቢ አየሯ ከምድር ከባቢ ጋር ሲነጻጸር በመቶ ጊዜ የሳሳ ነው፡፡ በመጠኗ የመሬትን ግማሽ ብታክል ነው፡፡ ከፀሐይ ከኛ ፕላኔት በግማሽ ርቃ ነው የምትገኘው፡፡ ለዚህም ይሆናል የሚበርደው፡፡ ለዚህም ይሆናል ፀሐይን ለመዞር ከኛ ዘለግ ያለ ጊዜ የሚወስድባት፡፡

ለመሆኑ ማርስ ከመሬት በምን ያህል ኪሎ ሜትር ትርቃለች?እውነት ለመናገር የዚህ ምላሽ ቋሚ አይደለም፡፡ እንደ ወቅቱ ይለያያል፡፡ መሬትና ማርስ ፀሐይን ሲዞሩ በተለያየ ፍጥነትና በተለያየ ርቀት ነው ታዲያ፡፡ ይህም በመሀላቸው ያለው ርቀት ተለዋዋጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

አንዳንዴ ማርስ ከኛ 400 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ነው የምትርቀው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ስንቀራረብ ጎረቤት ማርስ በ56 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ትሸሸናለች፡፡ለዚህ ነው ‹ጽናት› በራሪ ሮቦት ከፍሎሪዳ ማርስ ለመድረስ 7 ወራት የሚወስድባት፡፡

ከዚህ በኋላ ማርስ መሬትን በእዚህ ቅርበት የምትጠጋት መቼ ይመስላችኋል? እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2287 ዓ. ም፡፡ያን ጊዜ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊም ሆነ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ግብአተ መሬታቸው ተፈጽሟል፡፡
ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይጫኑ ።
Telegram
https://t.me/Ikez_KAKROS
YouTube



Tik Tok
https://vm.tiktok.com/ZMNyWY6SA/