Get Mystery Box with random crypto!

IKEZ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ikez_kakros — IKEZ I
የቴሌግራም ቻናል አርማ ikez_kakros — IKEZ
የሰርጥ አድራሻ: @ikez_kakros
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 448
የሰርጥ መግለጫ

#መረጃን በቀላሉ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
#አስተማሪ ታሪኮች
#ሁሉም መረጃሆች በቀላሉ ወደናንተ በፍጥነት ይደርሶታል።
#join &share በማድረግ ተጠቃሚ ይሁኑ::
TELEGRAM 👇
@Ikez_123
@Ikez_123

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-10 15:40:02
                      ማርስ MARS
                       =========
ጎረቤት ማርስ ቅዝቃዜዋ ለጉድ ነው፡፡ በዚያ ላይ ከባቢ አየሯ ከምድር ከባቢ ጋር ሲነጻጸር በመቶ ጊዜ የሳሳ ነው፡፡ በመጠኗ የመሬትን ግማሽ ብታክል ነው፡፡ ከፀሐይ ከኛ ፕላኔት በግማሽ ርቃ ነው የምትገኘው፡፡ ለዚህም ይሆናል የሚበርደው፡፡ ለዚህም ይሆናል ፀሐይን ለመዞር ከኛ ዘለግ ያለ ጊዜ የሚወስድባት፡፡

ለመሆኑ ማርስ ከመሬት በምን ያህል ኪሎ ሜትር ትርቃለች?እውነት ለመናገር የዚህ ምላሽ ቋሚ አይደለም፡፡ እንደ ወቅቱ ይለያያል፡፡ መሬትና ማርስ ፀሐይን ሲዞሩ በተለያየ ፍጥነትና በተለያየ ርቀት ነው ታዲያ፡፡ ይህም በመሀላቸው ያለው ርቀት ተለዋዋጭ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

አንዳንዴ ማርስ ከኛ 400 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ነው የምትርቀው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ስንቀራረብ ጎረቤት ማርስ በ56 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ትሸሸናለች፡፡ለዚህ ነው ‹ጽናት› በራሪ ሮቦት ከፍሎሪዳ ማርስ ለመድረስ 7 ወራት የሚወስድባት፡፡

ከዚህ በኋላ ማርስ መሬትን በእዚህ ቅርበት የምትጠጋት መቼ ይመስላችኋል? እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2287 ዓ. ም፡፡ያን ጊዜ የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊም ሆነ የዚህ ጽሑፍ አንባቢ ግብአተ መሬታቸው ተፈጽሟል፡፡
ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይጫኑ ።
Telegram
https://t.me/Ikez_KAKROS
YouTube



Tik Tok
https://vm.tiktok.com/ZMNyWY6SA/
53 viewsĬĶÊŽ, 12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 14:08:51
ወታደራዊ ሮቦቲክ ውሻዎች (Vision 60)   
==========================

ውሻ ናቸው፡፡ አራት እግሮች ያሏቸው ውሻዎች፡፡ ነገር ግን እጅግ በጣም የረቀቁ መሳሪያዎችን የታጠቁ ወታራዊ ሮቦቲክ ውሻዎች፡፡ ቪዥን-60 የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ፊለደልፊያ የሚገኘው ጎስት ሮቦቲክ የተባለው የቴክኖሎጂ ተቋም እነዚህን የሰው ሰራሽ ልህቀት የሆኑትን ውሻዎች በማምረት ወደ ስራ ያስገባቸው ሲሆን፡፡ የአሜሪካ አየር ኃይል 325ኛ የጸጥታ ሃይሎች ክፍለ ጦር በመደበኛነት ለጥበቃ ይጠቀማቸዋል ተብሏል፡፡

14 የማነፍነፊያ ስርዓቶች ያካተቱት እነዚህ የኢንፍራሬድ ቪዲዮ የሚጠቀሙት ወታደራዊ ሮቦቶች በሁሉም አቅጣጫ አንዳችም እክል ሳያጋጥማቸው እየተንቀሳቀሱ ጥበቃቸውን በንቃት የማከናወን ብቃትን ተላብሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በአንድ ጊዜ ሙሉ ቻርጅ ለሶስት ሰዓታት መሳሪያቸውን እንደታጠቁ ወዲህ ወዲያ እያሉ ጥበቃቸውን ማቀላጠፍ አልያም በጦር ሜዳ ተሰልፈው መፋለም እንደሚችሉ ሁሉ ይነገራል፡፡

ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይጫኑ ።
Telegram
https://t.me/Ikez_KAKROS
YouTube



Tik Tok
https://vm.tiktok.com/ZMNyWY6SA/
55 viewsĬĶÊŽ, 11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 13:58:08
ኤምኪው-9 ሪፐር /MQ-9-REAPER/ ድሮን
-----------------------------------------------

የዚህ ድሮን ክንፍ 20.1 ሜትሮች የሚረዝም ሲሆን እስከ 15,240 ሜትሮች ከፍታ ድረስ ወገቤን ያዙኝ ምርኳዜን አቀብሉኝ ሳይል የመብረር ብቃት አለው፡፡ ኤምኪው-9 ሪፐር 1,701 ኪ.ግ ያክል ተመሸከሞ 370.2 ኪሎ ሜትሮችን በሰዓት የመክነፍንም አቅም የተላበሰ እጅግ አስገራሚ ሰው አልባ የውጊያ አውሮፕላን ነው፡፡  ሌላው የዚህ ድሮን ጀብድ ደግሞ በአንድ ጊዜ ሙሉ ነዳጅ 1,850.7 ኪ.ሜ አካሎ መመለስ መቻሉ ነው፡፡

ታዲያ በማንኛውም የጥቃት ተልዕኮ ላይ ድሮኑ ቦምብም ሚሳኤልም ሊታጠቅ ይችላል፡፡ በአብዛኛው የሚታጠቀው ኤጂኤም-114 /AGM-114/ የተባለ በሌዘር የሚመራ ሚሳኤል ነው፡፡ አንዳንዴ የገሀነም እሳትም እየተባለ ይጠራል፡፡ ቅጽል ስሙ ኢላማቸውን በቅጽበት ወደ አመድነት ለመቀየር የተነደፉ ፍጹም ትክክለኛ የሚባሉ ሚሳኤሎች ቤተሰብ አባል ለመሆኑ መገለጫ ነው፡፡
ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይጫኑ ።
Telegram
https://t.me/Ikez_KAKROS
YouTube



Tik Tok
https://vm.tiktok.com/ZMNyWY6SA/
49 viewsĬĶÊŽ, edited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ