Get Mystery Box with random crypto!

ቢታነፅ ቢወቀር! (በእውቀቱ ስዩም) እኔም አንድ ሰሞን ልክ እንደ ሰለሞን 'ሁሉም ከንቱ ከንቱ ን | የስብዕና ልህቀት

ቢታነፅ ቢወቀር!
(በእውቀቱ ስዩም)

እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰለሞን
"ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል
ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል"
እያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር!

ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ

ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ
"ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ!

ለካስ...

ጠቢብ ቢያስተምረው
መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!

#share
Join: @Human_Intelligence