Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅርና ተቀባይነት! አንድ ሰው እንዲህ ሲል የተናገረው ትዝ አለኝ፣ “በሕይወታችን የምናደርጋቸው | የስብዕና ልህቀት

ፍቅርና ተቀባይነት!

አንድ ሰው እንዲህ ሲል የተናገረው ትዝ አለኝ፣ “በሕይወታችን የምናደርጋቸው አብዛኛዎቹ ነገሮች ፍቅርንና ተቀባይነትን ለማግኘት ነው ወይም ላጣነው ፍቅርና ተቀባይነት ማካካሻ ፍለጋ ነው”፡፡ የሚገርም ምልከታ!

ከዚህ በፊት በጣም የተጎዳችሁበትን ሁኔታ አስታውሱት፡፡ ከዚህ በፊት ከእናነት በራቁ ቁጥር የተከታተላችኋቸው ሰዎች አስቧቸው፡፡ በአሁን ወቅት ስሜታችሁን የረበሸውን ነገር አስቡት፡፡ በአሁን ወቅት ከአእምሯችሁ አልወጣ ስላለው ሰው አስቡት፡፡ በአሁን ወቅት የተነሳሳችሁለትን ድንገተኛ ውሳኔ አስቡት፡፡ አብዛኛውን ነገር ከፍቅርና ከተቀባይነት ፍለጋ ጋር ተያይዞ ታገኙታላችሁ፡፡

ሰው የሚረጋጋው ፍቅርንና ተቀባይነትን የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋትን የሚያጣው ፍቅርና ተቀባይነትን ማግኘት ከማይችልበት ሰውና ስፍራ ያንን በመፈለግ ሲንገላታ ነው፡፡

ሰው የሚረጋጋው መወደድንና ተቀባይነትን የሚያስገኝ ባህሪይ ካዳበረ በኋላ ሰዎች የራሳቸው ምርጫ እንዳላቸው አምኖ ሲቀበል የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋትን የሚያጣው ከሰዎች የሚጠባበቀውን ሁኔታ ሚዛናዊ አድርጎ ካልያዘው ነው፡፡  

ሰው የሚረጋጋው ከማንም ሰውና ሁኔታ ውጪ መኖር እንደሚችል ውስጡን ሲያሳምነው የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋት የሚያጣው የሸሸውንና ተቀባይነት የነፈገውን ሰው ሁሉ ሲከታተል ውሎ ሲያድር ነው፡፡

ሰው የሚረጋጋው ከምን አይነት ሰው ምን አይነት ፍቅርና ተቀባይነት እንደሚያገኝ ለይቶ ሲያውቅ የመሆኑን ያህል፣ ሰው መረጋጋትን የሚያጣው ከአንዱ ያጣውን ፍቅርና ተቀባይነት ከሌላ ሰው ለማግኘት ሲጦዝና ደረጃውን ዝቅ ሲያደርግ ነው፡፡

መልካም ቀን!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@Human_intelligence