Get Mystery Box with random crypto!

የራእይ ጉልበት! ታዋቂው ጸሐፊ ስቲቨን (Stephen Covey)  First Things First | የስብዕና ልህቀት

የራእይ ጉልበት!

ታዋቂው ጸሐፊ ስቲቨን (Stephen Covey)  First Things First በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ ስለአንድ ቪክቶር (Viktor Frankl) ስለሚባል የአውስትራያዊ የስነ-ልቦና ባለሞያ ታሪክ ይናገራል፡፡ ይህ የስነ-ልቦና ባለሞያ ከናዚ (ጀርመን) የሞት ካምፕ የተረፈ ሰው ነው፡፡ ቪክቶር በናዚ የሞት ካምፕ ውስጥ ታሽገው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በሞት ሲያልፉ አንዳንዶቹ ግን እንዴት ያንን ለሞት የሚዳርግ ሁኔታ አሸንፈው ሊወጡ እንደቻሉ በምርምር ደረሰበት፡፡

በጥናቱ ብዙ ነገሮችን ተመልክቷል - የጤንነታቸው ሁኔታ፣ የቤተሰባቸው ሁኔታ፣ ብልህነታቸው፣ ችግርን የመቋቋም ብቃት እና የመሳሰሉት፡፡ በመጨረሻ የደመደመው፣ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱም እንኳን ለእነዚህ ሰዎች በሕይወት መኖር ምክንያት እንደልሆነ ነበር፡፡ በዚያ ከባድ ሁኔታ ውስጥ በሕይወት የቆዩት ሰዎች አንድ የጋራ ነገር ነበራቸው፡፡ ይህ ነገር የወደፊት ራእይ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በሕይወት የመኖርን ነገር ጠንክረው እንዲይዙ ያደረጋቸው ብቸኛውና ጉልህ የሆነው ምክንያት በፊታቸው ገና ያላከናወኑት ራእይ እንዳላቸው የማመናቸው ሁኔታ ነበር፡፡

ጸሐፊው እንደ ቬትናም እና የመሳሰሉት ብዙ የጦር ምርኮኞች በስቃይ በሚታጎሩባቸው ካምፖችም ውስጥም ተመሳሳይ ሁኔታ እንደታየ ይናራል፡፡ አሳማኝ እና ወደፊት ላይ ያተኮረ ራዕይ ብዙዎቹን በህይወት እንዲኖሩ ያደረጋቸው ዋና ሃይል ነበር (ምንጭ፡- Stephen Covey, First Things First, p 103)፡፡

•  አንድ ሰው የሚሞተው ጤናው ሲጠፋ ብቻ አይደለም … ራእይ ሲጠፋም ጭምር ነው!

•  አንድ ሰው የሚከስረው ስራ ሲበላሽ ብቻ አይደለም … የራእዩ ሁኔታ ሲበላሽም ጭምር ነው!

•  አንድ ሰው ብቸኝነት የሚሰማው ሰው ሲርቀው ብቻ አይደለም … ራእይ ሲርቀውም ጭምር ነው!

•  አንድ ሰው ተስፋ የሚቆርጠው ሁኔታዎች አልታይ ሲሉት ብቻ አይደለም … ራእይ አልታይ ሲለውም ጭምር ነው!

•  አንድ ሰው ውዳቂ የሚሆነው ስለወደቀ ብቻ አይደለም … ራእዩን ሲጥል ጭምር ነው!

. . . እያለ እውነታው ይቀጥላል፡፡ ይህ እውነታ እንደሚያሳየን አንድ ሰው ምንም እንኳን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሲያልፍ የዚያን ሁኔታ ውጤት መቅመሱ ባይቀርም፣ የመጨረሻውን ውሳኔ ከሚያስተላልፉትና በብርታትና በደካማነት መካከል ከሚወስኑት ሁኔታዎች መካከል አንጋፋው ራእይ የመኖሩና ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፡፡

አሁን ከምታልፉበት አስቸጋሪና ተስ አስቆራጭ ነገር ባሻገር እንድትሄዱ ሊያደርጋችሁ የሚችል ዋነኛው የፈጣሪ ስጦታ ራእይ ይባላል፡፡ 

ራእያችሁን አግኙና እሱን በመኖር አሁን ያለውን ከባድ ዘመን አሳልፉት!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Human_intelligence
@Human_intelligence