Get Mystery Box with random crypto!

[ተስፋ በመቁረጥ ተስፋ መቀጠል] እንዳለ ገጣሚው መዘክር ግርማ...! -/ ተስፋ በተስፋ ይተካል: | የስብዕና ልህቀት

[ተስፋ በመቁረጥ ተስፋ መቀጠል] እንዳለ ገጣሚው መዘክር ግርማ...!

-/ ተስፋ በተስፋ ይተካል:: በማይቀየር  እና ከቁጥጥራችን ውጭ በሆነ ነገር ላይ ተስፋ መቁረጥ... ሊቀየር በሚችልና በቁጥጥራችን ውስጥ በሆነ ጉዳይ ተስፋ ለመቀጠል/ለማድረግ ያግዛል:: [ አዲስ ተስፋ ለመቀጠል በአሮጌው ተስፋ መቁረጥ ያስፈልጋል::]... ትውልድ ያለ ዕዳው እየተቀጣ ነው:: አባቶቹ ባለራዕይና ንቁ አልነበሩም:: ለሃያላን ስሁት ህልም የተገበረ የመስዋእት በግ ሆኑዋል:: ይህን ለመቀየር ረፍድዋልና ተስፋ መቁረጥ አለበት... ይህን የሚነግሩት ደፋር ብእርና አንደበት ያላቸው ቀንዲሎችም ያስፈልጉታል:: አዎ! ተስፋ መቁረጥ ከባድ ነው: ዙሪያን ጨለማ: መንገድን ግራ ያስመስላል ያኔ ግን የራስ ህልም ይወለዳል: አዲስ ተስፋ ይቀጠላል:: መጀመሪያ ተስፋ እንቁረጥ! አባቶቻችን አያቶቻችንን አይመስሉም:: ቅዠት እንጂ ህልም አልነበራቸውም::


[ናትናኤል ዳኛው]
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence