Get Mystery Box with random crypto!

ስለመፅሐፍ የተነገሩ አባባሎች! ወዳጆች ዛሬ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ሊያነሳሱን የሚችሉ ስለ | የስብዕና ልህቀት

ስለመፅሐፍ የተነገሩ አባባሎች!


ወዳጆች ዛሬ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ሊያነሳሱን የሚችሉ ስለመፃሕፍት የተነገሩ የተለያዩ ሠዎችን አባባል ዛሬ ልንዘክር ብዕራችንን ከወረቀቱ አገናኝተናል፡፡
መፅሐፍ የሚሠጡት ጥቅም የታወቀ ቢሆንም በማንበብ ብቻ ግን አዋቂ መሆን አይቻልም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡
ለማንኛውም አባባሎቹን እነሆ እላለሁ..! ሃሳብና አስተያየታችሁ የተጠበቀ ነው፡፡ መልካም ንባብ!

‹‹መፅሐፍ አንድ ቁምነገር አለው፡፡ ይሄም እግርህን ከቤትህ ሳታነሳ ዓለምን እንድትዞር ያደርግሃል›› (ጁምባ ራሂሪ)

‹‹አንባቢ ከመሞቱ በፊት አንድ ሺ ኑሮ ይኖራል፡፡›› (ጆርጅ ማርቲን)

‹‹መፅሐፍት ተንቀሳቃሽ አስማቶች ናቸው›› (ስቴፈን ኪንግ)

‹‹እንደመፅሐፍ ያለ ታማኝ ጓደኛ የለም፡፡›› (ኸርነስት ኸርሚንግወይ)

‹‹ አንድ ነገር አንርሳ! አንድ መፅሐፍ፣ አንድ እስኪብርቶ፣ አንድ ሕፃን፣ አንድ መምህር ዓለምን መለወጥ ይችላሉ፡፡›› (ማላላ ዮሶፍዜ)

‹‹ዓለም መፅሐፍ ናት፡፡ ዓለምን ተጉዘው ያላዩ መፅሐፍ ይግለጡ፡፡›› (ቅዱስ አውግስጦስ)

‹‹መፅሐፍ በየዕለቱ የሚያጋጥመንን የህይወት ጉድፍ የሚያስወግድልን የነፍሳችን ማጠቢያ ነው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)

‹‹ማንበብ ለአዕምሮ ሲሆን አዕምሮም አካላችን ምን ማድረግ እንዳለበት ያቀናጃል›› (ያልታወቀ ሠው)

‹‹መፅሐፍ ከባድ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ዓለሙ ሁሉ በእርሱ ታጭቋልና፡፡›› (ኮሜሊያ ፈንክ)

‹‹ዛሬ አንባቢ የሆነ ነገ መሪ ይሆናል፡፡›› (ማርጋሬት ፉለር)

‹‹ዛሬ ልታነበው የምትችለውን መፅሐፍ ለነገ አታቆየው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)

‹‹ካነበብኩ መላው ዓለም ለእኔ ክፍት ነው፡፡›› (ሜሪ ማክሎድ ቤቱን)

‹‹አንዳንድ መፅሐፍት ነፃ ይተዉናል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ነፃ አድርገው ይሠሩናል፡፡›› (ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን)

‹‹መፅሐፍ ወደፊት ልንሆን የምንፈልገውን የያዘ ህልማችን ነው፡፡›› (ኔል ጌማን)

‹‹ቤተ-መፃሕፍቶች ልክ እንደጥሩ ትዝታ መዓዛቸው ያውደኛል፡፡›› (ጃኩሊን ውድሰን)

‹‹መፅሀፍ አስተሳሰባችንን የሚያቀጣጥል መሣሪያ ነው፡፡›› (አላን ቤኔት)

‹‹እኔ በቀላሉ የመፅሐፍ ጠጪ ነኝ›› (ኤል ኤም ሞንቶጎሞሪ)

‹‹ሌላ ሠው ያነበበውን ብቻ እያነበብክ ከሆነ ሌላ ሠው የሚያስበውን ብቻ ነው እያሠብክ ያለኸው፡፡›› (ሐሩኪ ሙራካሚ)

‹‹ቤት ያለመፅሐፍት ማለት አካል ያለነፍስ ማለት ነው፡፡›› (ሲስሮ)

‹‹ተራ ሠዎች ትላልቅ ቲቪ አላቸው፡፡ ብልህ ሠዎች ግን ቤተመፃሕፍት ናቸው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)