Get Mystery Box with random crypto!

ኤፒክቲተስ- 2 ክስቶችን እንደ አፈጣጠራቸው ይቀበሏቸው ነገሮች የእርስዎን መሻትና ፍላጎት ብቻ | የስብዕና ልህቀት

ኤፒክቲተስ- 2

ክስቶችን እንደ አፈጣጠራቸው ይቀበሏቸው

ነገሮች የእርስዎን መሻትና ፍላጎት ብቻ ተከትለው እንዲከናወኑ አይጠብቁ፤  ነገሮችን እንደ አፈጣጠራቸው ይቀበሏቸው፡፡ በዚህ መንገድ ብቻ ሰላም የሚቻል ይሆናል፡፡

ሁኔታዎች የእኛን ምኞትና ጥባቆት ለማሟላት ብቻ አይከናወኑም፡፡ ክስተቶች የሚከናወኑት በራሳቸው ተፈጥሯዊ መንገድ ነው፡፡ ሰዎች የሚያደርጉትን የሚያደርጉት በራሳቸው መንገድ፣ ጸባይ ነው፡፡
የሚያገኙትን ነገር ይቀበሉ፡፡

ከሐሳዊ ስቃይ ለመዳን ዓይንዎን ይክፈቱ፤ ነገሮችን በተፈጥሯዊ ማንነታቸው ብቻ ይገንዘቧቸው፡፡ የሚያስደስቱዎትን፤ ጥገኛ የሆኑባቸውን ነገሮች፤ የሚያደንቋቸውን ሰዎች ልብ ብለው ያንሰላስሏቸው እስቲ፡፡ የነገሮቹ ተፈጥሮአዊ ስሪትና ክንውን እርስዎ ለነገሮቹ ካለዎት ግምት ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡

@Human_Intelligence