Get Mystery Box with random crypto!

የብሔር ማንነት ቅዠት -3 በአንድ ሀገር ውስጥ የ'ብሔር” ጭቆና ሊፈጽም ያሰበ መንግስት በመጀመሪ | የስብዕና ልህቀት

የብሔር ማንነት ቅዠት -3

በአንድ ሀገር ውስጥ የ"ብሔር” ጭቆና ሊፈጽም ያሰበ መንግስት በመጀመሪያ ራሱን በ”ብሔር” ማንነቱ መደራጀት መሠረታዊ ነው፡፡ ከመሠረቱ በ”ብሔር” ማንነት ለመደረጃት የሚያስብ ሥነልቦና በእርግጠኝነት የአናሳነት ስሜት የመፈጠር ውጤት ነው፡፡ ይህም በሰውነት ጭብጥ ከማንም ሰው ጋር እኩል መሆኑን ከማሰብ ይልቅ በሌሎች በጊዜና በቦታ ሊቀየሩ በሚችሉ ጉዳዮችን መመዘኛ በማድረጉ ነው፡፡ በተቃራኒው በብሔር” ማንነት የማይደራጅ አገዛዝ የ”ብሔር” ጭቆና የሚባለውን ሊያደርስ አይችልም፡፡ የ”ብሔር” ጭቆና እንደ ችግር ከታወቀ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት እንደገና በብሔር” ማንነት በመደራጀትና ሌላ የብሔር” ጨቋኝ ገዢ መፍጠሩ መፍትሄ ሳይሆን ሌላ ባለተራ ጨቋኝ “ብሔር” መፍጠር ይሆናል፡፡ ከዚህ በመነሳት የ”ብሔር ጭቆና” ተብሎ የተሰጠውን የችግር ግንዘቤና ትርጉም በተመሳሳይ በ”ብሔር” ማንነት ላይ በመደራጀት ለመፍታት መሞከር እርስ በእርሱ የሚቃረን በመሆኑ ምንኛ ጥልቅ የድንቁርና ቅዠት ውስጥ መግባት መሆኑን በቀላሉ መገንዘብ አስቸጋሪ  አይሆንም፡፡


ስለዚህ ስአንድ ሀገር ውስጥ ”የብሔር” ጭቆናን ችግር ለመፍታት በ”ብሔር” ማንነት በመከፋፈልና በመደራጀት አይደለም፡፡ ነገር ግን የ"ብሔር” ጭቆና የተባለው ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚፈታው ሕዝብ በሀገር አንድነትና
ሎአላዊነት ልዩነትን ማስወገድ ሲችል ነው።

ስለዚህ ለአንድ ሀገር የ”ብሔር” ጭቆና ስጋት ከሆነበት ዘላቂ መፍትሄው "በብሔር” ማንነት አደረጃጀትንና አገዛዝን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሕዝበ ውሳኔ ሕገ መንግስታዊ በማድረግ በመገደብ አማራጭ የሌለው ዘለቄታዊ መፍትሄ ነው፡፡


በአንድ ሀገር ውስጥ ብዙሃን ይሁን አናሳ ቁጥር ባለው “በብሔር” ማንነት
ላይ የተመሠረተ ማንኛውም አገዛዝ የሳይንሳዊ ፖለቲካዊ ስርአት ሳይሆን
በአዕምሮ ቅዠት ህመም የተጠቃ፣ አምባገነን፣ ኢሰብአዊ፣
ስርአተ አልበኛ፣  ገዢ ቡድን ነው፡፡ በአጠቃላይ “የብሔርተኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ በፖለቲካ ሳይንስ የተቃኘ ሕዝባዊ አስተዳደር ሳይሆን፣ ከአዕምሮ ቅዠት ህመም የመነጨ የድንቁርና አገዛዝ ነው::
በአሁኑ ዓለም የመልካም አስተዳደር ሳይንሳዊ ፖለቲካ ማለት፣ የአንድ ሀገርን ብዙሃን ሕዝብ አዕምሮ ከፖለቲካዊ ጥላቻና በቀል ነጻ በማድረግ በኑሮ ደረጃዉ እያሳደገ የማስቀጠል ብቃት ነው፡፡

ብሔርተኛ አገዛዝ የስልጣኑን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የከፋፍለህ ግዛው መሰረታዊ ፖሊሲው ነው፡፡ ፋሽስታዊ “ብሔርተኛ” ሴራውን ለማስፈጸምና የአገዛዙን እድሜ ያስቀጥልልኛል ብሎ ስለሚያስብ ብቻ “የብሔር” “ብሔረሰቦች” መብት “የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከመገንጠል ድረስ” የሚል ጊዜው ያለፈበትን የማርክሳዊ ኮሚኒዝም ፍልስፍና ሊያራምድ ይችላል፡፡ ይኸውም በፌደራላዊ መዋቅር ስም ሀገርን “የብሔር” ማንነትን በቋንቋ ላይ ብቻ መሠረት በማድረግ ለአገዛዙ ፌደራላዊ ግዛቶችን ወይም “መንግሥታትን” የሚፈጥረው በቀጠናው አገዛዜን ኢኮኖሚና በመከላከያ የበላይነቴን ለዘለቄታው ያስቀጥልልኛል በማለት የቅርብና የሩቅ እቅዱን ሴራ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡


ይኸውም ሕዝብ ሁልጊዜ ከነገ ዛሬ ምን ይመጣብን ይሆን? እያለ በፍርሃት ውስጥ በማስገባት ሕዝቡ ሳይወድ በግድ ላለው  “ብሔርተኛ አገዛዝ በቀጣይነት ምርኮኛ ሆኖ እንዲገዛ የታለመ ሴራ ነው፡፡

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence