Get Mystery Box with random crypto!

የታላላቅ ሰዎች ምርጥ አባባሎች ❖“ሰው የሚማረው አንድም በፊደል፣ አንድም በመከራ ነው፣ አንድም | የስብዕና ልህቀት

የታላላቅ ሰዎች ምርጥ አባባሎች

❖“ሰው የሚማረው አንድም በፊደል፣ አንድም በመከራ ነው፣ አንድም በሳር “ሀ” ብሎ፣ አንድም በኣሳር “ዋ” ብሎ።”
ፀጋዬ ገ/መድህን

❖ ‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ
አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን

❖ "የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።"
-ዊሊያም ሼክስፒር

❖ እምነት ባለዩት ነገር ማመን ሲሆን ሽልማቱም ያመንቱን ነገር ማየት ነው።"
-ጳጳስ ኦገስቲን

❖"ማለም የፈጠራ መነሻ ነው ፤ የምትፈልገውን ታልማለህ ፣ ያለምከውን ትመኛለህ ፤ በመጨረሻም የተመኘኸውን ትፈጥራለህ።"
-ጆርጅ በርናንድ ሾው

❖ ለመጀመር ስኬታማ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
-ዚግ ዚግላር

❖"በብርሃን ስትሆን ሁሉ ነገር ይከተልሃል:: ጨለማ ውስጥ ከሆንክ ግን ጥላህ እንኳን አይከተልህም።"
- ሂትለር

❖"ሳንቲም ብዙ ድምፅ ያሰማል:: ገንዘብ ግን ምንም አያሰማም:: ስለዚህ ዋጋህ ሲጨምር ወሬህን እየቀነስክ ና!"
- ዊሊያም ሼክስፒር

❖"ደሀ ሆነህ ብትወለድ ጥፋቱ ያንተ አይደለም ደሀ ሆነህ ብትሞት ግን ጥፋቱ ያንተ ነው።"
- ቢል ጌትስ

❖“ደካሞች ይቅር ማለት አይቻላቸውም። ይቅር ባይነት የጠንካሮች ብቻ ባህርይ ነው።”
-መሀተመ ጋንዲ

❖"በምድር ላይ የማያለወጠው ነገር ቢኖር ራሱ ለውጥ ነው።"
-መሀተመ ጋንዲ

❖‹‹ ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ
ብርሃን ነው፡፡ ››
ካህሊል ጂብራን

❖"በዓለም አንተ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ራስህ ኹነው።አለም ላይ ሰላም ፍቅር እንዲኖር ከፈለክ አፍቃሪ እና ሰላማዊ በመሆን ከራስህ ጀምር"
-መሀተመ ጋንዲ

❖"ሁለት የሞኝነት መንገድ አለ ። አንደኛው እውነት ያልሆነውን ማመን ሲሆን ሌላኛው እውነት የሆነውን አለማመን ነው ።"
ሶረን

#ሼር ይደረግ

Join
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence