Get Mystery Box with random crypto!

ሕይወት ምንድን ናት? ስንቶቻችን ይህንን ለራሳችን ጠይቀን እናውቅ ይሆን? ምናልባት ሐብታም መሆን፣ | የስብዕና ልህቀት

ሕይወት ምንድን ናት? ስንቶቻችን ይህንን ለራሳችን ጠይቀን እናውቅ ይሆን? ምናልባት ሐብታም መሆን፣ ተምሮ ዶክተር መሆን፣ አልያም ሌላ ነገር ልትሉኝ ትችላላችሁ ። እኔ ግን ህይወት እነዚህን ሁሉ እንዳልሆነች እነግራችሗለው። እና ታዲያ ምንድነው አላችሁኝ መሰለኝ? ሕይወት እኛ እንደምናስባት የተወሳሰበች አይደለችም። ሕይወት አሁን ነች። አሁን ምን እያደረጋችሁ ነው? ምናልባት ይሄን ፅሁፍ እያነበባችሁ፣ ቤት እያስተካከላችሁ ወይም ከልጃችሁ ጋር እየተጫወታችሁ በቃ ሕይወት ማለት እሱ ነው። ሌላ ትንታኔ የለውም። እኛ ግን ብዙ ቅጥያ ፈጥረን ሕይወትን አክብደናታል። ትዝ ይላችሗል ልጅ እያለን 1ኛ ክፍል ሆነን ሁለተኛ ክፍል ስንገባ ደስተኛ ምንሆን ይመስለን ነበር። ከዛ አመቱ ያልቅና መግባታችን አይቀር እንገባለን። ግን ያሰብነው ደስታ የለም። አሁን ደግሞ ሶስተኛ ክፍል ስንገባ ደስተኛ እንደምንሆን እናስባለን። ከዛ እንዲህ እንዲህ እያልን ዩኒቨርሲቲ እንገባለን። ከዛ ከተመረቅን በሗላ ደስተኞች እንደምንሆን ማሰብ እንጀምራን። ከተመረቅን በሗላ ግን ስራ ፍለጋ መንከራተት እንጂ ደስታ የለም። ሁሌ ደስታን የሌለንን ከማሳደድ እንጂ ያለንን ከማጣጣም ለማግኘት አንሞክርም። እኛ እንዲኖረን ከምንፈልጋቸው ነገሮች በላይ መተንፈስ መቻላችን ብቻ ደስተኛ ሊያደርገን እንደሚገባ አስባችሁት ታውቃላችሁ። እባካችሁ ደስታን በቁሳቁስ ለመሸመት አትሞክሩ። በህይወታችን ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እነደ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም በፍፁም በቁስ ልንሸምታቸው አንችልም። ምናልባት ገንዘብ ጊዜያዊ ፈንጠዝያ ውስጥ ከቶ ሊያደነዝዘን ይችል ይሆናል እንጂ የደስታችን ምንጭ ሊሆን አይችልም። ይህ ማለት ግን አትስሩ፣ ገንዘብ አታግኙ፣ አትማሩ ማለት አይደለም። እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርጉ ተማሩ ከዛ ሰርታችሁ ሀብታም ሁኑ ነገር ግን ደስታችሁን በገንዘባችሁ ለማግኘት አትሞክሩ። ደሀ ስታዩ ከሱ አንደምትሻሉ አታስቡ። ምክንያቱም ገንዘብ ለሰው ተፈጠረ እንጂ ሰው ለገንዘብ አልተፈጠረም። ያላችሁን ገንዘብም ሆነ የትምህርት ደረጃ እነደ ተራ ቁጠሩት። ለራሳችሁ ቅድሚያ ስጡ። እራሳችሁን አፍቅሩ። ለራሳችሁ ጥሩ ስሜት እንዲሰማችሁ የግድ ጥሩ ፍቅረኛ እስክቲዙ፣ ሀብታም እስክቶኑ አትጠብቁ። ምንም ነገር ባይኖራችሁም ውብ ናችሁ። ከቁሳቁስ የእናንተ ሰብአዊነት ይበልጣል። ለራሳችሁ ያላችሁን ክብር በምንም ምክንያት አትጣሉት። ገንዘብ፣ ንብረት ወይም ሌላ ነገር ለራሳችሁ የምትሰጡትን ክብር እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ። በገንዘብ ሊገዛችሁ የሚፈልግ ሰው እሱ እራሱ በገንዘብ የተገዛ ሰው መሆን አለበት። አለበለዚያ እንደዚያ ማድረግ ለምን አስፈለገው? ብዙዎቻችን ሳይታወቀን ገንዘብ እየገዛን ነው። ከሰው በላይ ለገንዘብ ትልቅ ቦታ እንሰጣለን። ግን ይህ ለምን የሆነ ይመስላችሗል። ለሌሎች ሰዎች ቦታ የማንሰጠው ለራሳችን ቦታ ስለማንሰጥ ነው ወይም ሌሎችን የማናፈቅረው እራሳችንን ስለማናፈቅር ነው። እራሳችንን ምናፈቅር ከሆነ ግን ሌሎችም ልክ እንደ እኛ መፈቀር እንዳለባቸው ስለምናስብ ለማፍቀር አንቸገርም። እንደውም ብዙ ጊዜ የበታችነት የሚሰማቸው ሰዎች ሌሎችን ማፍቀር አይችሉም። ምክንያቱም የበታችነት ስሜት እራስን ብቁ አይደለሁም ብሎ ከማሰብ የሚመጣ ስሜት ነው። ሌላው ደግሞ የበላይነት ስሜት ነው። ይህ ስሜት ከበታችነት ስሜትም የከፋ ነው። ብዙዎቻችን የሚመስለን ይህ ስሜት እራስን አብዝቶ ከመውደድ የሚመጣ ከድርገን ነው የምናስበው። ነገር ግን ይህ ስሜት መነሻው ስጋት ነው። በሌላው የመበለጥ ስጋት የወለደው ስሜት አለበለዚያ ይህ ስሜት ለምን ይሰማዋል? አንድ በበላይነት ስሜት የተጠቃ ሰው ሁሌም ሌሎች ሰዎች ያሉበት ደረጃ ያሳስበዋል ምክንያቱም መበለጥ አይፈልግም። እንደውም የበላይነት ስሜት ትክክለኛ መነሻው የበታችነት ስሜት ነው። አንድ ለረዥም ጊዜ የበታችነት ስሜት ሲሰማው የነበረ ሰው የሚያስበው እንዴት የበላይ መሆን እንደሚችል ነው። የበላይነት ስሜት ውስጥ የታመቀ የበታችነት ስሜት አለ። እናንተ ግን በበላይነትም ሆነ በበታችነት ስሜት ውስጥ አትሁኑ። እንዲሁ እራሳችሁን አፍቅሩ። እራሳችሁን ለማፍቀር ምክንያት መደርደራችሁን አቁሙ። ለራሳችሁ ክብር ይኑራችሁ ገንዘባችሁን ከራሳችሁ አስበልጣሁ አትዩት። ገንዘብ አለማግኘታችሁ ደስታችሁን እንዲቀማችሁ አትፍቀዱ። ከዛ ሌሎችን ማፍቀረ ቀላል ይሆንላችሗል። ሌሎችን ለመውደድም ምክንያት አትደርድሩ። ዝም ብላችሁ ሰዎችን እና ይህችን አለም ውደዱ። ከዛ የህይወት ትርጉም ይገለጥላችሗል።

ምንጭ፦ እኔ እራሴ

@Zephilosophy
@Zephilosophy