Get Mystery Box with random crypto!

የገደል ማሚቶዎን ይምረጡ አንድ ሰው ልጁን በአቅራቢያው ባለ ጫካ ውስጥ ለእግር ጉዞ ይዞት ይወጣል | ሁለንተናዊ ስኬት

የገደል ማሚቶዎን ይምረጡ

አንድ ሰው ልጁን በአቅራቢያው ባለ ጫካ ውስጥ ለእግር ጉዞ ይዞት ይወጣል።
ድንገት ልጁ ተደናቅፎ ይወድቅ እና ህመም ሲሰማው፣
"አህህህ!" ብሎ ይጮሃል
በሰማው ነገር ተገረመ፤
“አህህህ!” የሚል ድምፅ ከተራራው ሲመጣ ይሰማል፣

የገደል ማሚቶ ሲሰማ የመጀመሪያ ልምዱ ስለሆነ በጣም ተደነቀ፡፡

በጉጉት ተሞልቶ “አንተ ማን ነህ?” እያለ ይጮሃል ፣ ግን የተቀበለው ብቸኛ መልስ “አንተ ማን ነህ?” የሚል ነበር ፡፡

በትክክል መልስ ስላልሰጠው ተናዶ “አንተ ፈሪ ነህ!” ብሎ ጮኸ፡፡
የገደል ማሚቶው ይመልሳል "አንተ ፈሪ ነህ!"

ወደ አባቱን እየተመለከተ “አባባ ምን እየሆነ ነው?” ሲል ጠየቀ ፡፡
"ወደ እኔ መልሶ የሚናገረው በማን ነው?"
“ልጄ” ሰውየው ይመልሳል ፣" ትኩረት አድርግና ፣ አንድ ጥሩ ነገር በል።
ከዚያም ልጁ ይጮሃል ፣ “እወድሃለሁ!”
ድምፁ ይመልሳል ፣ “እወድሃለሁ!”

የልጁን ግራ መጋባት በመገንዘብ ሰውየው ውይይቱን ከተፈጥሮ ጋር ተረክቦ ይጮሃል።
"አንተ በጣም ድንቅ ነህ!"
ድምፁም መልሶ “አንተ ድንቅ ነህ!”
ልጁ በጣም ተደስቷል ግን ምን እየተካሄደ እንዳለ ሊረዳ አልቻለም ፡፡

አባትየው ያስረዳዋል ፣ “ልጄ ፣ ሰዎች ይህንን የገደል ማሚቶ (echo) ብለው ይጠሩታል ፣ ግን በእውነት ይህ ሕይወት ነው”።
ሕይወት ሁል ጊዜም የሰጡትን ይመልሳል ፡፡
ሕይወት የድርጊቶችህ መስታወት ናት ፡፡

ብዙ ፍቅር ከፈለክ የበለጠ ፍቅር ስጥ፡፡
ተጨማሪ ደግነትን ከፈለክ ብዙ ደግነትን ስጥ።
መረዳት እና አክብሮት ከፈለጉ
ክ ማስተዋል እና አክብሮት ይኑርህ።
አንተ ሰዎች እንዲታገሱህ ከፈለግህ ከዚያ ታገሳቸው።

ይህ የተፈጥሮ ደንብ ለሁሉም የሕይወታችን ገጽታ ይሠራል ፡፡
የገደል ማሚቶች እኛ እንዲያደርጉልን የምንፈልገውን በሌሎች ላይ እንድናደርግ እና እኛ ለራሳችን የምንመኘውን ለሌሎች እንድንመኝ የሚያስተምረን የተፈጥሮ መንገድ ነው።
ሕይወት ምንጊዜም የሰጧትን ትመልሳለች ...
ሕይወትህ አጋጣሚ አይደለም ፣ ግን የራስህ ተግባራት መስታወት ነው።

የእርስዎን ማሚቶ ዛሬ ይምረጡ!