Get Mystery Box with random crypto!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hu_main_campus_gibi_gubae — ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hu_main_campus_gibi_gubae — ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ
የሰርጥ አድራሻ: @hu_main_campus_gibi_gubae
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.35K
የሰርጥ መግለጫ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን ማህበረ ቅዱሳን ሀዋሳ ማዕከል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ግቢ ጉባኤ መደበኛ ቻናል
በዚህ ቻናል
👉 ትምህርታዊ ጽሑፎች
👉 የግቢ ጉባኤ መልዕክት
👉 የክፍላት ማስታወቂያ ይተላለፍበታል።
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ከታች ባለው አድራሻ ይላኩልን
👇👇👇
@ZHawassa_GGbot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-21 08:40:28 Channel photo updated
05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 08:35:31
605 views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 16:04:48
እነሆ በሀ/ዩ/ዋ/ግ/ግ ጉባዔ የጂሲ ኮሚቴ በየዓመቱ ከሚደረጉት መርሀግብራት ውስጥ የምናፍቀው መርሀግብር የሆነው " ፍኖተ አሀው ወአሀት " የወንድሞችና የእህቶች ጉዞ ሲሆን ግቢ ጉባዔው መርሀግብራትን አሰናድታ የእናንተን መምጣት ትጠባበቃለች።
ስለዚህ ሁላችንም ተመራቂ ተማሪዎች ወንድሞች ሱፋችሁን እንዲሁም እህቶች የሀበሻ ቀሚሳችሁን ለብሰን በአንድነት የምንካፈልበት መርሀግብር ስለሆነ ሁላችንም እንድትገኙ ስትል ግቢ ጉባኤ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

ማሳሰቢያ:- ባስ በሁለቱም ግቢ ይጠብቃችኋል።
መነሻ ሰዓት:- ቀን 7:00 ሰዓት
ቀን ነገ ማክሰኞ ማለትም 14/10/2014ዓም
የጉዞ ዋጋ:- የባስ እራትን ጨምሮ 350 ብር ብቻ
መድረሻ :- ከግቢ በሮች ተነስተን ቅድስት ሥላሴ ተሰባስበን ከዛም ወደ ሴንትራል ጉዞ ይደረጋል።

ትኬት የሚገኝበት አድራሻ
ዋናዉ ግቢ +251921343902
ቴክኖ ግቢ
+251975096298
+251936588004
+251929465363

ለጉዞ ትኬት የምታገኑት ከላይ ስልካቸው አለ እየደወላቹሁ ብር በመክፈል ትኬት ተቀበሉ
746 viewsedited  13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 07:12:56 የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በእግዚአብሔር ፍፁም የሰላምታ ቃል ሰላም እላችኋለሁ እንደምን አደራችሁ አሜን እስከዚህ ሰዓት የጠበቀን እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን ይሁን። የተደረገልን በጣም ብዙ ሲሆን እኛ ግን ለምን ለምስጋና ሰነፍን? ምነው እግዚአብሔርን በዝማሬ ማመስገን አቃተን?እውነት እውነት እላችኋለሁ ግቢ ጉባኤን የቻሉት ቀምሰዋታል በደንብ ተመግበዋታል እስኪ ደግሞ እስካሁን ያላወቅናት እንጠጋትና መልካም መዓዘዋ ይድረሰን የምታውቋት ደግሞ በደንብ እንድትቀምሷት ላሳስባችሁ ወደድኩ
እነሆ መመረቂያ ቀን ደረሰ
ስለዚህ ከወዲሁ ወረቡን ማጥናት ስላለብን ዛሬ ማለትም ሀሙስ ሰርክ ሰዓት 11:30 ስላሴ ተቀሳቅሰን እነድንገኝ

ማሳሰቢያ ማንም ተመራቂ ተማሪ መቅረት የለበትም ከአሁኑ አብረን እንድንጀምር ለመቀሳቀስ እነሞክር ከዚህ ቀደም አልጀመርንም አዲስ ነኝ በሚል ሰበብ መቅረት አይቻልም ሁላችንም ጀማሪ ነን ። ኑ እንቅረብ አብረን እናጥና ?


ወስብሀት ለእግዚአብሔር
852 views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 19:06:16 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ውድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሁሉም ነገር ተጠናቀቀ እንኳን ደስ አላችው እያልን ግቢ በ 18/10/2014/ዓም እንዳስመርቀን በ19/10/2014 ደግሞ ቤተክርስቲያን ታስመርቀናለች እናም ለዚች ቀን መዝሙር ማጥናት አለብን እና ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች መሳተፍ ስላለብን እየተቀሳቀስን መዝሙር እንድናጠና እንድሁም የበገና መዘመራን እህት ወንድሞቻችን በመቀሳቀስ መዝሙር እንድናጠና ይሁን ለበለጠ መርጃ 092 134 3902 ጌታቸው ብላችው ደውሉ የበገና ዘማርያን 0915257493 ደውሉ ሙሉ መርጃ ታገኛላችው ለዚች ቀን በሰላም ያድርሰን
805 viewsedited  16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 00:22:32 ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ pinned a photo
21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 22:34:44
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በሰላም ሒዱ/


ሁልጊዜም አንድ ልብ ሆነው በቤተመቅደስ ያገለግሉ ነበር ፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግኑ ነበር ፤በህዝቡም ሁሉ ዘንድ መወደድ ነበራቸው ፤ሐዋ 2፥46-47

ከቤተሰቦቻችን ተለይተን ከመጣንበት ከከባዱ የመጀመሪያ ዓመት እስከ አሁን ብዙ አሳልፈናል። በጊቢ ጉባኤ የእግዚአብሔርን ቃል ተመግበን የመንፈስ መጠጥ ቀድተን ጠጥተናል። በፍቅር ተረዳድተን በአገልግሎት እና በጸሎት ተሳስበናል፤ እግዚአብሔር
ይመስገን ይህንን የሕይወት ምዕራፍ ልናልፍ ቀናት ቀርተውናል። ልባችሁ ውስጥ የፃፋችሁትን ፍቅር ይዘናል ትዝታችሁም ተዋህዶናል።

በመንፈስ ባንራራቅም በአካል ልንለያይ ነውና ዳግም እስክንገናኝ ሰላም ሁኑ እንባባል። ቅዳሜ ሁላችንም ተመራቂዎች የእናንተን ስንብት ቃል እንሰማ ዘንድ ፤ እኛም ደግሞ በልባችሁ የሚኖርን የከበረ አደራ ለማስቀመጥ እንመጣለን!!

በዕለቱ፦መዝሙር በተመራቂ ተማሪዎች
ትምህርተ ወንጌል
የስንብት መዝሙር
እና ሌሎችም መርሐግብራት ይኖራሉ

መቅረት በፍፁም አይቻልም!!

ቦታ፦ ቅድስት ሥላሴ ትልቁ አዳራሽ ሰርክ (11:30) ጀምሮ
998 views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ