Get Mystery Box with random crypto!

ትጋት.....!!! ሰውነት ባዳ ነው ቀን ጠብቆ ይከዳል:: ሠውነትክን ማጠንከሪያ አዕምሮ ነውና | ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪

ትጋት.....!!!

ሰውነት ባዳ ነው ቀን ጠብቆ ይከዳል:: ሠውነትክን ማጠንከሪያ አዕምሮ ነውና ትጋትን አስተምረው! ሁሉም ነገር ጥረት እና ትጋት ሳይኖረው እጅ በእጅ የተደላደለ ነገር አይኖረውም! ነገ ታላቅ ለመሆን ዛሬን ሳትሰለች መፍጋት አለብክ!!! ነገን ለማረፍ ዛሬ መስራት የግድ ነው!!! ነገን የተስተካከለ ለማድረግ ዛሬ መጣር አለብክ!!! ትጋት ፅናት እና ትግዕስት የበሳል ሰው አካሄድ ነው:: ልብክንም አዕምሮክንም ለለውጥ አዘጋጅተክ የደከመውን ሰውነት ብርታትን ስጠው!!! ደከመኝ ሰለቸኝ አትበል!!! ምክንያቱም የተፈጠርከውም ጥረክ ግረክ ልትበላ ነው!!! እናት አባትክ ያስቀመጡልክ የእኔ ነው አትበል!!! ያንተ የሆነው አንተ ፈግተክ ያኖርከው ብቻ ነው!!! የኔ ነው የምትለው ታሪክ እንዲኖርክ ከፈለክ ከተኛክበት ተነስተክ ሩጥ.... ሩጥ....ጀግን.....በርታ የምትፈልገውን እስክታገኝ ፈግተክ ስራ በብልጭልጭ እና በስሜትክ እንዳትረታ!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal