#ከራስ_ጋር_ንግግር ከራስህ ጋር መቼም ብዙ ጊዜ አዉርተሃል፡፡ በተለይ በከባድና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ዉስጥ ነገሩ ያይላል...ህሊናህ እንዲህ ሲልህ ትዝ ይልሃል? • ተረጋጋ! እራስህን እንደምንም ብለህ ተቆጣጠር፡፡ በፍፁም እንዳታለቅስ...ዛሬ ብቻ አደራህን! ነገሮች እንደዚህ ተበጥብጠዉ አንተም ተጨምረህበት ከቁጥጥር ዉጪ ይሆናል፡፡ • ኸረ ሰዉ ምን ይላል? ምን እያወራህ ነዉ...? እንዴ ኸረ ሚስጥርህን ሁሉ ለአደባይ ለፈፍከዉ! ይብቃህ ተቀመጥ! • እራስህን መሸወድ ይበቃሃል! • ዉሸታም...ዉሸታም! • ምን አድርጋኝ ነዉ አትበል! ጥፋት አጥፍተሃል • ከመቼዉ ጭቃ ዉስጥ ገባህ? • ወንድ!ሰዉ ማለት እንደዚህ ነዉ! • ተጣልተህ መኖሩ አልሰለቸህም? እስኪ ተስማምተህ ኑር! • ይሄ ሁሉ ሩጫ ለዚህ ነበር?? • ትሂድ ተዋት...እንዳትከተላት! • መልካም ማድረግህ ጥሩ ነዉ...እራስህን አትጉዳ! እንዴት አደራችሁ @hivzz 86 viewsedited 04:01