2022-07-09 19:01:36
እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?
ለስራ መስክ በወጣሁበት አንድ አጋጣሚ ከአንድ ልጅ ጋር ተዋውቀን
በጊዜ ሂደት ተግባባን፤ ውሎ ሲያድርም መግባባቱ ተቀይሮ አፈቀርኳትና የፍቅር ጥያቄ አቀረብኩላት፡፡
ይሁን እንጅ እርሷ እንዲህ አይነት ግንኙነት እንዲኖራት እንደማትፈልግ ገልፃ ለጥያቄየ ይሁንታን ነፈገችኝ
እኔም ተስፋ ሳልቆርጥ እሷን የእኔ ለማድረግ ለወራት በጥያቄየ ገፋሁ፤ ይሁን እንጅ አሁንም በእምቢታዋ ጸናች።
ቀድሞ የነበራት ህይወት ያሳደረባት ተፅእኖ እና የልጅ እናት መሆኗ ደግሞ የእኔን የፍቅር ጥያቄ ላለመቀበሏ ምክንያት ነበር።
ልጅ እንዳላት በነገረችኝ ወቅት ለጊዜው ባመነታም ባል ስለሌላት ተደስቼ ችግር እንደሌለው በመግለጽ ይሁን አልኳት።
በተደጋጋሚ እንዳስብበት ብትነግረኝም ስለማፈቅራት አብረን መሆን እደምንችልና ልጁንም በጋራ እንደምናሳድግ ነገሬያት ተስማማን።
የምንኖርበት ቦታ ርቀት ቢኖረውም ርቀቱ ፍቅራችንን ሳይገድበው መተሳሰባችን ሳይላላ ከአመት በላይ ቆየን፤
ጋብቻ አሰብንና ልንጋባ ሽማግሌ ለመላክ ተስማማን።
ለቤተሰቤ ላሳውቅ ብዬ ሽማግሌ ከመላኬ በፊት ላገባ መሆኔን ነገርኳቸው
ጥያቄየን ቢወዱትም ለትዳር የመረጥኳት ፍቅረኛየ ልጅ እንዳላት ስነግራቸው አምርረው ተቃወሙኝ፡፡
በፍፁም ልጅ ያላት ሴት ማግባት የለብህም በማለት ሃሳቤን እንድሰርዝ ነገሩኝ
እሷን ካገባህ ልጃችን አይደለህም መቃብራችን ላይም እንዳትቆም በማለት እሷን ወይም እኛን ምረጥ በማለት መስቀለኛ ጥያቄ አቀረቡልኝ።
በዚህ መሃል እኔ አጣብቂኝ ውስጥ ገባሁ።
ፍቅሬ ላይ ፈርጄ ቤተሰቦቼን እንዳልመርጥ ሳትፈልግ ገፋፍቼ የገባሁላትን ቃል ማፍረስ ከበደኝ
በዛ ላይ እወዳታለሁ ከእርሷ ጋር መጋባትም እፈልጋለሁ፡፡
ልቤን ተከትዬ የቤተሰቦቼን ቃል ትቼ ፍቅሬን እንዳልመርጥ ደግሞ በችግር አሳድገው ለዚህ ያበቁኝንና ጧሪ ቀባሪ ይሆነናል ብለው ተስፋ ያደረጉብኝ ቤተሰቦቼ ጋር እናዳልቆራረጥ
ሰጋሁ
መንታ መንገድ ላይ ቆሜ ተቸገርኩ።
ምን ባደርግ ይሻለኛል? እርስዎ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?@hivzz
235 viewsedited 16:01