Get Mystery Box with random crypto!

#በዚህችም_ቀኑብኝ!? ----------------------------- ህይወትን ልመራት ባለኝ ተደስ | BOON TECH

#በዚህችም_ቀኑብኝ!?
-----------------------------
ህይወትን ልመራት ባለኝ ተደስቼ
አንድ ሁለት ስል ለማወቅ ጓግቼ
ለእዉነት ብዬ የጠመመዉን ትቼ
እራሴን ሰብስቤ ገና ቀና እንዳልኩ
ጣታቸዉ ዞረብኝ ብዙ ብዙ ተባልኩ

ያወኩ መስለዋቸዉ በዝህችም ቀኑብኝ
ግን አልተቀየምኩም ገና ስላልተረዱኝ

እስኪ ተመልከቱ ምን ማድረግ አለብኝ
እንዳያይ ነው ብለው አፈር በተኑብኝ
አጅብ የሰው ነገር በዚህችም ቀኑብኝ

ገና ቆሜ ሳልሄድ በዳዴ ስራመድ
ቆርጠዉ ተነሱኮ ልያስሩኝ በገመድ

@abdi_ik