Get Mystery Box with random crypto!

ለፈገግታ ሚስት ባልዋ ከስራ ወደ ቤት ሲመጣ ትንሽ ልታናድደው ታስብና እጥር ም | BOON TECH


ለፈገግታ


ሚስት ባልዋ ከስራ ወደ ቤት ሲመጣ ትንሽ ልታናድደው ታስብና እጥር ምጥን ያለች ደብዳቤ ፅፋለት አልጋ ላይ አስቀምጣለት አልጋው ስር ትደበቃለች።
ባል በስራ የደከመ ሰውነቱን እየጎተተ ወደ ቤቱ ገብቶ ሚስቱን ሲጠራት አቤት የሚለው በማጣቱ ተኝታ ይሆናል ብሎ ወደ መኝታ ቤት ሲገባ ሚስቱ የፃፈችለትን ደብዳቤ ያገኛል።
ደብዳቤው እንዲ ይላል፦ " ሌላ ሰው ስለወደድኩ ካሁን በዋላ ካንተ ጋር መኖር ስለማልፈልግ ቤቱን ትቼልህ ሄጃለው" ይላል።ባል ሆዬ ወዲያው ፈገግ ይልና ስልኩን አውጥቶ ደወለ:–
"ሀይ የኔ ቆንጆ እንደነገርኩሽ ያቺ ጅል ሚስቴ በራሱዋ ጊዜ ትታኝ ሄደች ደስ አይልም? መጣው ጠብቂኝ" ብሎ ስልኩን ዘግቶ ከቤት
ይወጣል።
ይሄን ጊዜ ሚስት ብሽቅ ብላ እያነባች ከተደበቀችበት ስትወጣ አልጋው ላይ ሌላ ደብዳቤ ታገኛለች፤እንዲ ይላል:-
"የኔ ማር አልጋ ስር እንደተደበቅሽ አውቂያለው ፤ አሁን ወተት ገዝቼ እስክመጣ ቆንጆ ራት ሰርተሽ ጠብቂኝ እወድሻለው የኔ ቆንጆ" ይላል።
አላህ እንደዚህ አይነቱን ትዳር ይስጠን!