Get Mystery Box with random crypto!

ሠላም እንደምን አላችሁ የሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር አባላትና ወዳጆች... በዛሬው ዕለት ማህበሩ | Henon Charity Org.

ሠላም እንደምን አላችሁ የሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር አባላትና ወዳጆች...

በዛሬው ዕለት ማህበሩ የተመሰረተበትን #6ኛ (ስድስተኛ) ዓመት ምክኒያት በማድረግ የማህበሩ አባላት የጋራ ጊዜ እንዲህ በሚያምር መልኩ አሳልፈናል።

በዕለቱ ከተከናወኑ መርሃ-ግብሮች መካከል ማህበሩ ባለፉት ስድስት አመታት ያከናወናቸው በርካታ የበጎ አድራጎት ሥራዎች የተዳሰሱ ሲሆን፤ በቀጣይም ማህበሩ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ለአባላቱ ገለጻ ተደርጎ በተነሳው ሀሳብ ላይም ከአባላቱ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። እንዲሁም የተለያዩ አዝናኝ ስፖርታዊ ጨዋታዎች እና ሌሎች ክንውኖች የመርሃ-ግብሩ አካል ነበሩ።

መልካምነት ለራስ ነው።
በቀጣይ ማህበሩን በመቀላቀል አብራችሁን መሥራት የምትፈልጉ በ0900615876 ደውሉልን።

እንዲሁም ማህበራችንን በገንዘብ መደገፍ ለምትፈልጉ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- 1000373276409
- ሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር

በጎነትን በፍቅር!
ሄኖን በጎ አድራጎት ማህበር

ሰኔ 13/2014 ዓ/ም ዱራሜ
ዘገባው የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ነው።

@henon_charity_association