Get Mystery Box with random crypto!

#እኔ ማመን የምፈልገውንና ማወቅ ያለብኝን የማስታውሰው ፣ ስደክም የምበራታውና ዝወዛወዝ የምረጋጋው | ሃይማኖት አንድ ናት

#እኔ ማመን የምፈልገውንና ማወቅ ያለብኝን የማስታውሰው ፣ ስደክም የምበራታውና ዝወዛወዝ የምረጋጋው ፣ ስጨነቅ ለራሴ ፋታ የምሰጠውና ወደ ወደቡ የምደርሰው የኖህን መርከብ በማስታወስ ነው።
" ለአንተ ለወዳጄም እልሃለሁ፦ በመጀመሪያ ደረጃ መርከቡ እንዳያመልጥህ፣ ሁላችንም የመርከቡ ተሳፋሪ መንገደኞች መሆናችንን እወቅ። ነቅተህ ጠብቅ ፣ ወደ መርከቢቷም ግባ። ነገ እንደሚመጣ እመን ፣ እርግጥኛ ሁን የኖህ መርከብ የተገነባችው ዝናብ እየዘነበና መጥለቅለቅ ስለነበረ ሳይሆን ወደፊቱ ለሚመጣው የጥፋት ውሃ ነበር። በጤንነትና በጥንካሬ ኑር፤በምድር ላይ ጥፋት በሆነ ጊዜ ኖህ የ600 ዓመት ነበር ። አንተ 60 ዓመት ሆኖህም ቢሆን ለጠንካራ ሃላፊነት ልትታጭ ትችላለህና አትድከም ፣ ጠንክር ተበረታታ። የማይገቡ አሽሙሮችንና በስራህ ላይ የሚደረጉ ቀልዶችን አታድምጣቸው። ዝም ብለህ ስራ ፣ገንባ። የወደፊት ተስፋህንና ህይወትህን በከፍታ ላይ አስቀምጥ። የጥፋት ውሃ ወደ ተራሮች እንደወጣ ሁሉ አንተ ደግሞ ጥፋት ከማይደርስበት የመንፈስ ከፍታ ተቀመጥ።
ለሰላምና ለጤንነትህ ሲባል ጥንድ ሁን። ውደድ ፣ ውሰድ አጥብቀህ ያዝ።(ከንጹሕ እንስሳት ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹህ እንስሳም ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕስትና እንስት .... ተወስዶ እንደተረፈ ሁሉ ለማንኛውም ዘርህ ይተርፍ ዘንድ ጥንድ ሁን ።) ፍጥነት ሁል ጊዜ ይጠቅማል ብለህ አትንቀዥቀዥ። አስታውስ ቀንድ አውጣም ይሁን አቦሸማኔ መርከቧ ላይ ወጥተዋል። ተንኮል ብቻ ያዋጣኛል አትበል!
ፍየልም ይሁን በግ በዚያው ነበሩ፣ ውበት ያድነኛል አትበል ጃርትም ይሁን እባብ ፣ አዞን ይሁን ጉማሬ ፣ ፒኮክም ይሁን ርግብ በዚያው ነበሩ። ስትጨነቅ ገለል ብለህ ተንሳፈፍ፣ እየቀዘፍክ አስብ፣ ተረጋግተህ ውረድ። ልብ በል የኖህ ምክር የተሰራችው በፕሮፌሽናል ገንቢዎች አልነበረም፣ እንዲያም ሆኖ ከዚያ ሁሉ መአት ተረፈች፤ ታይታኒክ ደግሞ የተሰራችው በድንቅ ማሃንዲሶች ነበር፤ እንዲያም ሆኖ በዚያች ኢምንት አደጋ ወደቀች።
ምንም አይነት ዶፋ ቢወርድ፣ ምንም አይነት ወጀብ ቢመጣ፣ ምንም አይነት ጎርፍ ቢጎርፍ #እግዚአብሔር ካንተ ጋር ከሆነ የሚጠብቅህ መሰባበርና መስመጥ ሳይሆን ቀስተ ዳመና ነው። ተስፋ አድርግ ፤ እመን** ወዳጄ (ኦሪት ዘፍጥረትን ከምዕራፍ 7 ጀምሮ ለምን አታነብም!)
አባት ሆይ የኖህን ታዛዥነትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና በመርከቡ ገብተን እንድንሄድ የተጠራንና የተዘጋጀን ያድርገን!!!!
@haymanotanednat
@haymanotanednat