Get Mystery Box with random crypto!

#መቼ ነው* እውነተኛ ክርስቲያኖች የምንሆነው? #መቼ ነው* እግዚአብሔር በፈጠራቸው ነግሮች የምን | ሃይማኖት አንድ ናት

#መቼ ነው* እውነተኛ ክርስቲያኖች የምንሆነው?
#መቼ ነው* እግዚአብሔር በፈጠራቸው ነግሮች የምንማረከው?
#መቼ ነው* እግዚአብሔር ለምን እንደፈጠርን የምንረዳው?
#መቼ ነው* እግዚአብሔር እንደሚፈልገው መኖር የምንጀምረው?
#መቼ ነው* ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልብ እምንናገረው?
#መቼ ነው* እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?

#መቼ ነው* ለመልካም ስራ ምሳሌ የምንሆነው?
#መቼ ነው* በስግደታችን በፆማችን የምንጠቀመው?
#መቼ ነው* ጾለታችን ተሰሚነት የሚያገኝው?

#መቼ ነው* ውሎና አዳራችን በቅዱስ ቃሉ ሚሆነው?
#መቼ ነው* ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ የምንመካው?
#መቼ ነው* ያአለምን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?
#መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ ያለው የተበላሸ ሂዎት የሚስተካከለው?
#መቼ ነው* ቤታችን ውስጥ መጸሐፍ ቅዱስ ውዳሴ ማሪያም የሚወራው?
#መቼ ነው* ውሽት እምናቆመው?
#መቼ ነው* የእግዚያአብሔርን ውሳኔ መቃውም እምናቆመው?
#መቼ ነው* እኔ እኔ ማለት ትተን ውንደሜ እህቴ ማለት እምንጀምረው?
#መቼ ነው* ለሰዎች ከክርስቶስ ውጪ ጌታ እንደሌለ እምንናገረው?
#መቼ ነው* ጥሩና ለጋሽ መልካም ሰው የምንሆነው?
#መቼ ነው። ክርስቲያንነታችንን የምናስተዋውቀው?
#መቼ ነው* ለድሃ እምናዝነው?.
#መቼ ነው* ትዳራችን ስላም ሚያገኝው?
#መቼ ነው* የጋብቻን ጥቅም ተገንዝበት ለትዳር የምንቻኮለው?

#መቼ ነው* ከሀሜት; ስውን ከመበድል; ከማስቀየምና ከማማት እምንላቀቀው?
#መቼ ነው* ወላጆቻችንን እምናስደስተውና እምንታዝዝው?
#መቼ ነው* ያልተጣራ ውሬ ካማውራት እምንቆጠበው?
#መቼ ነው* እምንዋደደው?
#መቼ ነው* እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?
#መቼ ነው* ስግደት ፆም ፆለት የምንላመደው?
#መቼ ነው* የበድለንን ይቅር የመንለው?
#መቼ ነው* ከራስ ወዳድነት እምንላቀቀው?
#መቼ ነው* ከሞት ቡኃላ ላለው ሂወት ስንቅ እምናዘጋጀው?
#መቼ ነው* አባቶችን እምናከብረው?
#መቼ ነው* ለእውቅት ጊዜ የምንሰጠው?
#መቼ ነው* ባወቅነው የምንሰራው?
#መቼ ነው* የ ምንሞትበትን ቀንም ይሁን ስፍራ እንደማናውቅ ተገንዝበን በተጠንቀቅ የምንቆመው?
#መቼ እረ መቼ ነው* ክርስትናን የምንኖረው?
#መቼ ነው* ለእነዚህ ተግባራዊ መልስ የምንመልሰው
እግዚአብሔር ይርዳን

ተራራውን ደልድለህ፣ ሸለቆውን ሞልተህ፣ መንገዴን ያቀናህልኝ፡፡ የማለዳው ድምቀት፣ የቀኑ ውበት፣ ክብሬ ብርሃን ክርስቶስ ምን እላለሁ ብቻ ተመስገን፡፡ በሕይወቴ ስንት አለፈ፡፡ ሞት ለሚገባኝ ምሕረት የሰጠኸኝ ጌታ እባክህ እንዳለፈው ዘመን ጊዜዬ አይለፍብኝ፡፡ ፍጻሜዬ በቤትህ ይሁንልኝ፡፡ የእነዚያን ባርያዎችህን ፍጻሜ እኔም ተመኘሁ፡፡ አምኜህ መሞትን ናፈቅሁ፡፡ ያላንተ ወርቅ ከምደርብ ከመስቀልህ ሥር እርቃኔን ልቀመጥ፡፡ አንተ የሕይወት ተስፋ ያላንተ እንደማይሆንልኝ እንኳን መራራው ጣፋጩ እንደማይጣፍጠኝ ታውቃለህና ዘመኔን በፍቅርህ ፈጽመው፡፡ በተወጋው ጎንህ አሜን፡፡ @haymanotanednat