Get Mystery Box with random crypto!

ዮሐንስ ባለ ራዕይ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hawaryawyohanis — ዮሐንስ ባለ ራዕይ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hawaryawyohanis — ዮሐንስ ባለ ራዕይ
የሰርጥ አድራሻ: @hawaryawyohanis
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 635

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-01-23 01:12:32
205 views22:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 01:12:32 We stand with his holiness!!!
185 views22:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 05:36:53

38 views02:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 15:53:24

73 views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 22:31:55 ጌታችን መች ተጠመቀ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር። ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19፡ በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር። (ሉቃ 3፥23)።
ጌታችን ስለምን በ30 ዓመቱ ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓት እና ልማድ፤ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልዕኮ እና መንፈሳዊ አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር።፡እጅግ አስፈላጊ እንኳን ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም። የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፤ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ፡ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው። (ዘፀ4፥3፤1 ዜና መዋ.23፥24፤1ጢሞ.3፥6-­‐10)።
ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዘመኑ ነበር። ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው። ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን የተሰጠውን ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው።
ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ፈልጎ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስቅዱስ ለማስመስከር፤ ውኃውን ለመቀደስ፤ የአዳምን ልጆች የዕዳ ደብዳቤ ለመደምሰስ እና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው። ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲያርፍ የባሕርይ አባቱ አብ በደመና “ይህ የምወደው ልጄ ነው” ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ በጉልህ ተረጋግጧል። (ማቴ 3፥16) ጌታችን በዮሐንስ እጅ ለምን ተጠመቀ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትኅትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው። ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ብሎት ቢሆን ዛሬ ነገሥታቱና መኳንንቱ፤ ካህናቱን ያለንበት መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር። ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው። ጌታችን “ጌታ ስሆን በባሪያዬ እጅ ካለበት ድረስ ሂጄ እንደ ተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ” ሲል።ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነት የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ እና ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ እከብር ብሎ አይደለም። ምክኒያቱም እርሱ እከብር አይል ክቡር፤ እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና። ጌታችን ጥምቀቱን ለምን በዮርዳኖስ አደረገው? በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች፤ ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው። ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው። “ባሕር አየች ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ” (መዝ 113፥3)። ከዚህም ሌላ ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ (በመገረዝ እና ባለመገረዝ) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው። እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምድረ ርስት ገብተዋል።
ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ። ሌላው በዮርዳኖስ ተደብቆ የነበረውን አዳምና ሔዋን የዲያብሎስ ባርያ ተብሎ የተፃፈው የዕዳ ደብዳቤ ይደመሰስልን ዘንድ ነው። (ቆላ.2፥14)። ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን በማን ስም አጠመቀው? ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ “ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለው አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው፤ በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ፤ በመንፈስቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?” ብሎ ቢጠይቀው ጌታም “እንደ መልከ ጼዴቅ ባለ ሹመት ተሹህ የዓለም ካህን አንተ ነህ ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለን እያልህ አጥምቀኝ” አለው። በዚህም ቃል አጥምቆታል።
ዮሐንስ ጌታን ሲያጠምቀው እጁን ለምን አልጫነበትም? ቅዱስ ዮሐንስ ጥምቀት ከበረው (ልዕልና ሰጠው) እንዳይባል፤ አንድም መለኮትን በእጅ መንካት አይቻልምና። ጌታችን ለምን በሌሊት ተጠመቀ? በኃጢአት ጨለማ ለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና፤ በጨለማ በሚመሰል ኦሪት ይኖር ለነበረ ሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ (ኢሳ.9፥2)። አንድም ጌታ ልደቱ፤ ጥምቀቱ፤ ትንሣኤው እንዲሁም ዳግም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን፤ ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው። አንድም መንፈስቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር። በሌሊት ርግብ ዓይኗ ማየት ስለማይችል መብረር አይሆንላትም። ስለዚህ መንፈስቅዱስ እንደሆነ በዚህ ይታወቅ ዘንድ ነው። መንፈስቅዱስ ለምን ጌታ ከውኃ ከወጣ በኋላ ወረደ? ዮሐንስን ያከብሩት ነበርና መንፈስቅዱስ የወረደው ለዮሐንስ እንጂ ለጌታ አይደለም ይሉ ነበርና። ምክንያቱም ጌታ ውኃ ውስጥ እያለ ከዮሐንስ አልተለየምና። አንድም ውሃን የሚባርክ መልአክ እንዳለ ያውቁ ነበርና ውኃውን ለመባረክ እንጂ ለጌታ አይደለም እንዳይባል። አንድም ማረፊያ ያጣች ርግብ በባሕር ስትበር አረፈችበት ባሉ ነበርና፡፡ ሐሳባቸውን በሙሉ ያጠፋ ዘንድ ከውኃ ውስጥ ከወጣ በኋላ መንፈስቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ።
ዛሬም ታቦታቱ በዋዜማው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ መውረዳቸው ጌታ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳሶ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ሲሄድ ብቻውን ነበር ዛሬም ታቦቱ ሲወርድ የዕለተ ጥምቀቱን ያህል ሕዝብ አይገኝም፡፡ በማግሥቱ በዙ ሕዝብ ጥምቀቱን እንደ ሚያከብር ጌታችንም ከተጠመቀ በኋላ ብዙ ሕዝብ የሚከተለው ሁኗል፡፡ ይህንን በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሚታ በሚዳሰስ ዮርዳኖስ የተገኘን ያህል እስኪሰማን ድረስ ታከብረዋለች፡፡ ምእመናኑም ዳግም ለመጠመቅ ሳይሆን ከበረከተ ጥምቀቱ ለመሳተፍ ማየ ጸሎቱን ተረጭተው ሥጋውን ደሙን ተቀብለው በደስታ፣ በሆታ፣ በእልልታ ያከብሩታል፡፡
92 views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 17:14:11

187 views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 23:17:23

85 views20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 03:06:41

162 views00:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 03:00:53

167 views00:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-27 00:33:36
223 views21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ