Get Mystery Box with random crypto!

Hasen Injamo

የቴሌግራም ቻናል አርማ haseniye — Hasen Injamo H
የቴሌግራም ቻናል አርማ haseniye — Hasen Injamo
የሰርጥ አድራሻ: @haseniye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.26K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2022-07-02 20:44:03 ሙስሊም ሁሉ አማኝ አይደለም
======== =========
ሙስሊምነት ያለ አድሎ በነጻ የሚገኝ የተፈጥሮ መብት ነው:: ሁሉም ሰው ሲወለድ ሙስሊም ሆኖ ነው:: ወላጆቹ ወይም አካባቢው ይቀይረዋል:: የተወሰኑት ብቻ ናቸው አምነው የሚዘልቁቱ::
በነፃ የተገኘ ኢስላም በልብ ገብቶ ሲጸና ሙእሚን (አማኝ) ይባላል:: በልብ ጸንቶ ሩሕ ሲጸዳ ሙሕሲን (ሱፊይ) ይባላል::

قَالَتِ الۡاَعۡرَابُ اٰمَنَّا‌ ؕ قُلْ لَّمۡ تُؤۡمِنُوۡا وَلٰـكِنۡ قُوۡلُوۡۤا اَسۡلَمۡنَا وَلَمَّا يَدۡخُلِ الۡاِيۡمَانُ فِىۡ قُلُوۡبِكُمۡ‌ ۚ وَاِنۡ تُطِيۡعُوا اللّٰهَ وَرَسُوۡلَهٗ لَا يَلِتۡكُمۡ مِّنۡ اَعۡمَالِكُمۡ شَيۡـًٔــا‌ ؕ اِنَّ اللّٰهَ غَفُوۡرٌ رَّحِيۡمٌ

የዐረብ ዘላኖች «አምነናል» አሉ፡፡ «አላመናችሁም፤ ግን ሰልመናል በሉ፡፡ «እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና (ጠልቆ) አልገባም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ብትታዘዙ ከሥራዎቻችሁ ምንንም አያጎድልባችሁም፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡ (ቁርአን 49:10)

የእስልምና ሀሁ እንኳ የማያውቅ ነው እኮ ሙስሊም በሉኝ ሌላ ስም አልፈልም የሚለው:: ወንድሜ ሙሕሲንነት (ሱፊይነት) ቀርቶ ሙእሚንነት ደረጃ መች ተደርሶ?

ለምሳሌ:-
ሶላት ጎንበስ ቀና እያሉ መስገድ ሙስሊም ያስብላል::
አላህን ፈርቶ ልብ ሳይወሰወስ መስገድ ሙእሚን ያስብላል::
ያንተንም የቤተሰብህንም ሪዝቅህን (ሲሳይህን) በሙሉ በሶላት ማግኘት ሙሕሲን ያስብላል::

ሱፊያ መባልማ ሲያምረን ይቅር:: ሱፊያነት ሲሟላ እስልምና ይሟላል:: እስልምና ሲሟላ ሱፊያነት ይገኛል::
1.4K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 20:05:56
ዛሬ ጁን 29/2022 ጨረቃ ከመግሪብ በሗላ 19:14 (ከምሽቱ 1:14) በመግባቷ ነገ ሀሙስ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ገብቷል ማለት ነው::
የሀጅ ውቁፍ አረፋ ከተነገ ወዲያ ሳምንት ዐርብ ሲውል ዒደል አድሃ ደግሞ ከነገ ወዲያ ሳምንት ቅዳሜ ይውላል::
ኢንሻአላህ!
2.3K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:34:28 የቤተሰብ አወቃቀር
[ዓብዱልቃዲር ኑረዲን]
=============
ፍቅር + እንክብካቤ = እናት
ፍቅር + ፍርሃት = አባት
ፍቅር + እገዛ = እህት
ፍቅር + ድብድብ = ወንድም
ፍቅር + ስስት = አያት
ፍቅር + ስር መግባት = ልጅ

ፍቅር + እንክብካቤ + ፍርሃት + እገዛ + ድብድብ + ስስስት + ስር መግባት = ሚስት
========

አካውንቲንግን የመረጥኩበት
ምክንያት ይህንን ስሌት በመሥራቴ ነበር
1.6K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 17:55:18 አላህን የምታመሰግንበት ቃላት ያጥርሃል
[ዓብዱልቃዲር ኑረዲን]
ድሮ እጅግ በጣም ብመኘውም ፕሮፌሰሮችን ማሰልጠን ይሳካልኛል ብዬ አልገመትኩም ነበር:: አልሃምዱሊላህ:: የገረመኝ ፓወርፖይንት አልበቃ ብሏቸው ማስታወሻ ይዘው ሲከታተሉ ነው::

ችግሩ ግን ምን መሰላችሁ:- እስካሁን የተማሩትንና ያስተማሩትን ካሪኩለም ወይም የቆሙበትን አፍርሶ አዲስ ፓራዳይም መገንባት ላይ ነው:: በእርግጥ በሪሰርች ላይ ስለቆዩ ቶሎ መፍትሔ ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::

ዕውነታ:- እኛ በተለይ አፍሪካውያን በድህነት ብዙ ምዕታት ኖረን የለ? እየባሰ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም:: ይህ ሁላችንም እየኖርነው ያለ ዕውነታ ነው:: >60% የዓለም የሚታረስ መሬት አፍሪካ ውስጥ አለ:: ከአፍሪካ 70% ተራራና ውሃ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው:: ድፍን ኢትዮጵያ ላይ በአማካይ ከ3 ሜትር እስከ 20 ሜትር ጥልቀት ጀምሮ ውሃ አለ:: ሆኖም ግን በረሃብና ጥማት እንማቅቃለን:: በዚህ አያያዝ ድህነቱና ሗላ ቀርነቱ ይቀጥላል:: ምዕራባውያን እራሳችን እና አምላካችንን እየወቀስንና እነርሱን እያደነቅን እንድንኖር ያስያዙን ሀዲድ አለ:: ግን በጣም ቀላል ትሪክ ነው:: ያንን ትሪክ በትምህርቱ ዓለም ለኖረ ሰው ስትነግረው የኮረኮሩት ያህል ይስቃል::

- የዓለም ቢሊዮን ሕዝብ:- የገንዘብ ሥርዓት አያውቅም
- መቶዎች ሚሊዮኖች:- ወርቅ እየተቀመጠ ወረቀት የሚታተም ይመስለዋል::
- አስር ሚሊዮኖች:- ገንዘብ ፈጣሪ ብሔራዊ ባንክ ይመስላቸዋል::
- ሚሊዮኖች ብቻ ንግድ ባንኮች .. ከብሔራዊ ባንክ 9 እጥፍ ገንዘብ እንደሚያመርቱ ያውቃሉ::
- ሺዎች ብቻ ይህንን ሥርዓት የዘረጋው የካፒታሊዝም ክሬዲት ሲስተም መሆኑን ያውቃሉ::
- መቶዎች ብቻ ናቸው ተግባራዊ መፍትሔ ያላቸው::
=====
ከዚህ ጀርባ ግን አንድ ምስጉን ሰው አለ::
1.4K viewsedited  14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 14:19:53
ትናንት ዕሁድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስኩል ኦፍ ኮሜርስ ለመምህራን እና ለተወሰኑ (Small circle) ጥሪ ... ስለ ገንዘብ እና የገንዘብ ሥርዓት እንዲሁም ክሪፕቶከረንሲ ፕሮግራም ነበረን:: ዩኒቨርስቲ ያስተማረህን አስተማሪ እንደማስተማር የሚከብድም ግን የሚያስደስትም ነገር አይኖርም::
- ዛሬ የዓለም የፋይናንስና የኢኮኖሚ ፒራሚድን ደብድበነዋል::
- ክሪፕቶግራፊ, ብሎክቼይና ቢትኮንይ ምንነት በቀላሉ በማስረዳት እንግዳ እንዳይሆንበት ጥረናል::
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወሰደውን እርምጃ አግባብነት ወይም (Rationale) አውስተናል::
- ፕሮግራሙ beyond crypto ስለነበር ጠቅላላ የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት ስላስረዳን የብዙ ሰው አስተሳሰብም ሲቀየር አስተውለናል:: (From feedback)
-> ብዙ ሪሰርቾችን ከመምሕራኑና ተማሪዎች እንጠብቃለን::
=========
የዓለም የፋይናንስና ኢኮኖሚ ፒራሚድ-> 666, ኢሉሚናቲ ደጃል ወይም ኮንስፓይሬሲ አይደለም:: ግልጽ ፍጥጥ ያለና መቀየር የሚቻል ሎጂካል አደራደር ነው ያለው::

እስከመጨረሻው ስለተከታተላችሁ እናመሰግናለን::
በተለይ አዲስ አበባ ንግድ ሥራ ኮሌጅ (ኮሜርስን) ከልብ እናመሰግናለን::

ብዙ ማስታወቂያ ያልሠራነው ጥቂት ሰው ብቻ እንዲገኝ ስለተፈለገ ነውና ሌሎቻችሁን በሌላ ፕሮግራም::
1.6K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 22:31:38 ይህንን ጉድ ስሙ

በ " FIAS 777 " በሚል የሚንቀሳቀሱ አካላት አጭበረበሩን ካሉት መካከል እጅግ በጣም በጥቂቱ ፦

" 40000 ብር ተበልቻለሁ "

" በFIAS እኔም 30 ሺህ ብር ተብልቻለሁ "

" እኔም ገንዘቤን ተበልቻለሁ ፤ ተበድሬ ነበር የገባሁት በሰዎች ጉትጎታ ኤጀንቶቹም አድራሻቸውን አጥፍተዋል "

" በFIAS 777 የተዘረፉ በሚያውቋቸው ኤጀንቶች ላይ ክስ ለመስረት እያተዘጋጁ ነው "

" ዘንድሮ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ የምመረቅ ዘንድሮ ነበር ነገርግን ከቤተሰብ ለመመረቂያ ልብስ ብር አስልኬ fias777 ለተባለ አጭበርባሪ platform ልኬ ምንም ብር ሳይገባልኝ በሉት። ከተቻለ እርምጃ እንዲወሰድበት አሳስባለሁ። በተጨማሪ ሌሎች የማጭበርበሪያ መንገዶችን ለምሳሌ ፦ HDU, DH አና የመሳሰሉ platform እየተጠቀሙ ስለሆነ ማንም እንዳይጭበረበር "

" የመንግስት ያለህ እኛ የFIAS ተጠቃሚወች ድርጅቱ ሀገረ መንግስቱ እውቅና የሰጠው ነው ተብለን ነው የገባንበት ሊንኩ ከተዘጋ ጀምሮ ገንዘብ ገቢና ወጭ እሚያደርጉልን ኤጀንቶች ቴሌግራም አካውንታቸውን ድሌት አርገው ከኛ ጋ የተጻጻፋትን አጥፍተው ነው ውሀ ሽታ የሆኑት በመቶ ሽወች የሚቆጠር ገንዘብ vIP Upgrade ያደረጉ ልጆች እያበዱ ነው። "

" እዚህ ኢትዮጵያ ሲያስተባብሩ የነበሩት ይታወቃሉ ፤ ልብስ ለብሰው በአደባባይ ሲታዩም ነበር ፤ እንዴት እና ገንዘቡን የት እንዳደረሱት ይጠየቁ "

" 30 ሽህ ብር አንድ ብር ሳላወጣ ተበልቻለው ባንክ የከፈልኩበትን ደረሰኝ ማቅረብ እችላለሁ "

" በሰው በሰው ገብቼ 30 ሺህ ብር ተበልቻለሁ ፤ ስለድርጅቱ አንዳች ነገር አላውቅም "

" እሄ website በ internet ነው እሚሰራው ግባ ብሎ በማላቀዉ ነገር fias 777 lay ኣስገብተዉ አሁን ላይ እስከ100 ሺህ ሚገመት ብር ከሰዉ ኣስበድረው ኣስበልተውኛል:: የ bank full መረጃ አለኝ "

" ህጋዊ በመምሰል በጦርነት እና በዚህ በኑሮ ውድነት የሚሠቃየውን ሚስኪኑን ማህበረሰባችንን ዘርፎ ስለጠፋው fias777 ስለሚባል ድርጅት መናገር ፈልጋለሁ። አብዛኛው ሰው ትርፋ አገኛለሁ በሚል መንፈስ ከሰው በመበዴር፣ መሬት በመሸጥ፣ ቋሚ ንብረቶቹን ሳይቀር በመሸጥ ለዚህ ድርጂት መጀመሪያ አካባቢ ከ1000 እስከ 30,000 ብር ገቢ ያዴረጉ ሲሆን አሁን በቅርቡ ሊዘጉት አካባቢ ዴግሞ እስከ 180,000 ብር ድረስ ለዚህ ድርጅት ገንዘባቸውን ገቢ በማድረግ ገንዘባቸው የውሀ ሽታ ሁንዋል "

ይህ ከብዙ በጥቂቱ ከተላኩት ውስጥ የቀረበ ሲሆን አብዛኛው ሰው በሰው በሰው መግባቱን እና አሁን ስራውን እንሰራለን የሚሉ አካላት መጥፋታቸውን የሚጠቁም ነው ፤ ተበላ የተባለው ገንዘብም እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። የሚመለከተው አካል ገንዘብ ገቢ በተደረገባቸው አካውንቶች መሰረት ሰዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ከዚህ በፊት በኦንላይን በሚሰራ ስራ በርካታ ትርፍ እናስገኛለን እያሉ ስለሚንቀሳቀሱ አከላት ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት መተላለፉ የሚዘነጋ አይደለም ፤ አሁንም በሌላ ስም የሚንቀሳቀሱ አሉ ጥንቃቄ ይደረግ።

ከTikvahethiopia ገፅ የተወሰደ
2.3K views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:50:54 (ከላይ የቀጠለ)

ባንኮች ደግሞ ከዚህም በላይ ወንጀል ሊሠሩ ይችላሉ:: ምክንያቱም በተቀማጭ ገንዘብ ሱስ አብደዋል:: መቶ ሚሊዮን ብር የሚበደር መቶ ደንበኛ ካላቸው ለአንዱ ተበዳሪ ለማሟላት ስብከት አይሉት ስለት ይወጣሉ:: በየመንገዱ አካውንት ያስከፍታሉ:: ከመቃብር ሐውልት ላይ ሳይቀር ፎቶ በሞባይል ስካን እያደረጉና ስም እየወሰዱ ከኪሳቸው 50 እየከፈሉ አካውንት ይከፍታሉ:: በ50 ብር የሺህ ብር ነጥብ ለራሳቸው ቅርንጫፍ ባንክ ይጨምራሉ:: በጥናት ባላረጋግጠውም ከባንክ ኃላፊዎች እንደሰማሁት 80% የባንክ አካውንት "Dormant” ነው:: እዚያም እዚህም ያስከፍቱህና ትረሳዋለህ:: ባንኮች በቀላሉ ሊታለሉ ይችላሉ:: ምእመኑ እንኳ መታለልና መሳደብ ልማዱ ነውና ይበለው:: ይብሉት::
1.4K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:50:34
ፊያስ/FIAS ሿሿ
===========
ሲተነተን (Foreign Investment Advisory Service) ነው ይሉታል ግን ማረጋገጫ የለም:: ምክንያቱም በሀገራችን ምንም ዓይነት የተመዘገበ ፈቃድ የሌለውና ስግብግቦች ሿሿ የተሠሩበት ፒራሚዳዊ ሥርዓት ነው:: ከዚህ በፊት በኩዌስትና በቲየንስ የተበሉ ሰዎች ያውቁታል:: አሁን የተበላው በዚያ ወቅት ለመረጃ ሩቅ የነበረ በአብዛኛው ወጣቱን ነው::

ፒራሚዳዊ አሠራር ዘመድ ዘመዱን ጓደኛ ጓደኛውን የሚያሞኝበት ነው:: አንድ ሰው 1,000 ብር ከፍሎ ከገባ ትርፍ ለማግኘት ከስሩ ለምሳሌ 13 ሰው አስገባ ሊባል ይችላል:: ከ13ቱ ሰው 13 ሺህ ብር ለፊያስ ገቢ አድርጎ 4,000 ብር ሊሠጡት ይችላሉ:: እርሱ ያስገባቸው ዘመዶች እያንዳንዳቸው ሌላ 13 ዘመድ መመልመል አለባቸው:: እርስበእርስ መበላላት ይባላል::

ይህንን በነፃ ስንነግረው ብዙ ሰው "ምቀኛ, ፋራ, ሗላቀር, ደሃ" እያለ ይሳደብ ነበር:: ማን ፋራና ሗላቀር እንደሆነ ሰሞኑ ታየ:: የእኔን ጽሑፍ ሙክታሮቪችና ሱሌማን አብደላ ሼር አድርገውት ምእመኑ የስድብ መዓት ሲያወርድባቸው ነበር:: አሁን ደግሞ "ተበ(ላ)ሁ" እያሉ ሙሾ ማውረድ ጀምረዋል::
(ከስር ይቀጥላል)
1.4K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 13:38:21
እነሆ ለረጅም ጊዜ ስጽፈት የነበረው ሌላኛው የማክሮ ኢኮኖሚ ፍልስፍናዬ በይፋ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ሆኖ መጣ! ምን ያህል እንደሚያስደስት! ይህኛው LCY ይባላል:: Liberty of Currency እንደማለት ነው (እናንተ ስትፈልጉ በምታውቁት Local Currency በሉት):: ግን መልሰው ሁሉንም በፊያት (ዶላር) ከሸጡት ኪሳራ ነው:: አሠራሩን በ<<ፊያት ገንዘብና ወለድ>> መጽሐፍ ውስጥ ተብራርቷል::

በቀጣይ ደግሞ Buss’y’ness (ማባተል) የሚለው ፍልስፍና ነው:: ይህም ተጀምሯል:: የሰራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ, የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር, ግብርና ሚኒስቴርና ገቢዎች ሚኒስቴርን የተመለከተ ነው:: እናንተ ስትፈልጉ Business በሉት::
1.4K viewsedited  10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:42:52 ሕዝብን ማባተል
============
ብዙ ሕዝብ ባለበት ሀገር መንግሥት ጨካኝ ብቻ ሳይሆን ማዕከላዊ አዛዥ መሆን አለበት:: የጎንዮሽ አዛዥ ታዛዥ አያስፈልግም:: መዋቅሩን እየጠበቀ ይውረድ:: በሚያለምጥ ላይ መቀልጠም:: ሦስት ዓይነት የሊደርሺፕ ዓይነቶች አሉ:: እኛ ክላሲካል ዕድሜ ላይ ስለሆንን እነርሱ ፍቱን ናቸው::

1) አዛዥ - የጉልበት ሠራተኛ, መሀይምና ቦዘኔ የበዛበት ቦታ የምትጠቀመው ነው:: ትእዛዝ እንጂ ምክክር አያዋጣም:: Do/Don’t ብቻ!

2) ዲሞክራቲክ - ማመዛዘን የሚችል ምሁር ያለበት ቦታ

3) ሌይዜፌሬ - ልቅ አመራር ሲሆን ጥቅም ላይ የሚውለው ሁሉም ኤክስፐርት የሆነበት ቦታ ላይ ነው:: ትለቃቸውና ውጤት ይዘው ይመጣሉ:: የሕክምና ቀዶ ጥገና ክፍል, የጥናትና ምርምርም ተቋም ሌይዜፌሬ ነው::

በትምህርት ብንሄድ
- እስከ ማትሪክ: አውቶክራቲክ (አዛዥ),
- ዲግሪ ላይ ዲሞክራቲክ ትሆንና
- ማስተርስና ዶክትሬት ደረጃ ሌይዜፌሬ ይሆናል::

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራ ሚኒስትሮችን መጠቅለል አይደል እንዴ? አልጠቀለል ያለውን ቆርጦ መጣል:: ምክንያቱም ብዙዎቹ በውክልና እንጂ በብቃት የመጡ አይደሉም:: ለሚኒስትሮች አውቶክራሲውን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል:: እንደሚታወቀው የፖለቲካ ሥልጣን ጫካ በመግባት እንጂ ዩኒቨርስቲ በመግባት አይገኝም:: ስለዚህ አፍሪካ ላይ Law of the jungle ነው የሚያዋጣው:: በተዋረድ እስከ ወረዳ ማውረድና Loophole እየከፈቱ መሄድ ነው:: ከመስመር የሚወጣው ላይ ለምን የእናት ልጅ አይሆንም ግንባሩ ላይ ማብራት! ጠላት የሚገባው በጣም በቅርብና የሚታመን በሚባል ሰው በኩል ነው::
_____
ሕዝብን ማወቅ
ምሳሌ:- የኤርትራ ሕዝብ ሁሉም ውትድርና ሰልጥኗል:: ጸጥ ማሰኘት የሚቻለው ትጥቅ በማስፈታት ሳይሆን ሁሉንም በማስታጠቅ ነው:: ማን ማን ላይ ይተኩ^ሳል? እየተፈራራ ይኖራል::

የኢትዮጵያ አብዛኛው ወይም ሁሉም ሕዝብ ቦዘኔ ስለሆነ መፍትሔው ማባተል ነው:: ቢዚ ማድረግ! የሥራ ሥርዓቱ ግን በቦዘኔ ላይ ቦዘኔ የሚጨምር እንጂ የሚያሠራ አይደለም:: 10 ሺህ ብር አቅም የሌለው ሰው 100 ሺህ ብር ግብር ክፈል ይባላል:: ለምን? ስለሠራ:: ካልሠራና ፈቃድ ካላወጣ እኮ ማንም ግብር አይጠይቀውም:: ስለዚህ ሥራውን ትቶት ያወናብዳል::

የግብርናው ደግሞ መሬቱ ተኝቶ ይከርማል:: የሚያስገድድ አመራር የለም:: መሬትህ ጦም ካደረ ልጅህ የሕዝብ ልጅ ይሆናል:: ለመንግሥት እርሻ ይዘምታል ብሎ ማስፈራሪያ መስጠትና ማባተል::

ሲጠቃለል:- ቦዘኔነትን የሚያክል ታክስን ማጭበርበር አላየሁም ይላል ዓብዱልቃዲር ኑረዲን
1.3K viewsedited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ