Get Mystery Box with random crypto!

የዓሹራ ቀን ትሩፋት! --------------- ዓሹራ ቀን ከአሏህ ወር ከሆነው ከሙሐረም በረከቶች | 🌹Islamic_deawa 🌹

የዓሹራ ቀን ትሩፋት!
---------------
ዓሹራ ቀን ከአሏህ ወር ከሆነው ከሙሐረም በረከቶች አንዱ ነው። እሱም ከሙሐረም 10ኛው ቀን ነው። ወሩን ወደ አሏህ ማስጠጋት ትልቅ ደረጃና ትሩፋት ስላለው ነው። ምክንያቱም አሏህ ምንንም ነገር ወደሱ አያስጠጋውም ልዩ ፍጡሮቹን በስተቀር። ( ስለሆነም ነው ሙሐረም ወር የአሏህ ወር የተባለው፤ ከሌሎቹ በተለየ መልኩ)።

የአሏህ መልክተኛ – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – እንዳሉትም፦ [ ከረመዷን ቀጥሎ በላጩ ፆም የአሏህ ወር ሙሐረም ወር ነው።] ሙስሊም። አስረኛው ቀን (ዓሹራ) ክብር ሲሰጠው የነበረው ከቀምት ጀምሮ ነው። የዚህ ቀን ትሩፋት ደግሞ ትልቅ ነው። ነቢዩሏሂ ሙሳንና – ዐለይሂ አስ–ሰላም – ህዝቦቹን ነጃ ያወጣበት፤ ፊርዓውንን ከነ ሰራዊት በባህር ያሰመጠበት ቀን ነው። ሙሳ – ዐለይሂ አስ–ሰላም – ለአሏህ ምስጋና ብለው ፁመውታል። ቁረይሾች በጃሂሊያ ዘመን ይፆሙት ነበር። አይሁዶችም እንደዛው። ረሱልም – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – [ ከእናንተ ይልቅ እኛ ለሙሳ ተገቢና ቅርብ ነን።] አሏቸው። ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት። ነቢዩም ፆመውታል። እንዲፆምም አዘዋል። መጀመሪያ ጊዜ ግዳጅ ነበር፤ የረመዳን ፆም ግዴታ ከመጣ በኋላ ወደ ሱናነት ዞሮዋል።

በመሆኑም 9ኛውንም ቀን ጨምሮ ከ10ኛው ( ዓሹራ) ጋር መፆም ይወደዳል። አይሁዶች 10ኛውን ብቻ ስለሚፆሙ፤ እነሱን ለመቃረን ተብሎ።

ትልቁ ትሩፋቱ ያለፈውን የአንድ አመት ወንጀል ያሰርዛል። ይህ ነው ንፁህ በሆነው ሱና የፀደቀው።

በዚህ ቀን ከፆም ውጪ የተደነገገ አንድም ነገር የለም!
-
ከሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ ፈርኩስ ከፈትዋ ቁ ፡ 592 የተቀነጨበ።
-
ሁሉም በፆሙ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ሼር አድርጉላቸው! አሏህ ተጠቃሚ ያድርገን!