የዓሹራእ ፆም ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን – ረሒመሁሏህ – እንዲህ ይላሉ፦ የዓሹራእ ፆም ④ ደረጃዎች አሉት፦ ①ኛው ደረጃ፦ 9፣10ና 11ኛውን መፆም። ይህ ትልቁ ደረጃ ነው። ምክንያቱም ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው እንደዘገቡት፦ [ (ከዓሹራእ) ከፊቱ አንድ ቀን እና ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ። አይሁዳውያንን ተቃረኑዋቸው።] አንድ ሰው ሶስት ቀን በመፆሙ ተጨማሪ በአንድ ወር የሶስት ቀንን ፆም ደረጃ ያገኛል። ②ኛው ደረጃ፦ 9ኛውና 10ኛውን መፆም። ነቢዩ – ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም – “ አይሁዶች አስረኛውን ቀን ይፆሙ ነበር ” ተብሎ ሲነገራቸው [ ወደ ቀጣዩ አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም ቀን እፆማለው።] ማለታቸው። አይሁዶችን መቃረን ይወዱ ነበር። እንዲሁም ከሃዲያንን በሙሉ። ③ኛው ደረጃ፦ 10ኛውን ከ11ኛው ጋር መፆም። ④ኛው ደረጃ፦ 10ኛውን ብቻ መፆም። ከፊል ዑለማዎች ይህንን “ይፈቀዳል” ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ “ብቻውን ነጥሎ መፆም ይጠላል” ብለዋል። "ይፈቀዳል" ያሉ ዑለሞች መረጃቸው፤ ነቢዩ – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – ስለ ዓሹራእ ፆም በተጠየቁ ጊዜ “ የበፊቷን አንድ አመት ወንጀል ያሰርዛል ” ብለዋል። እዚህ ጋ ዘጠነኛውን ቀን አልጠቀሱም የሚለውን ንግግር በመያዝ ነው። አስረኛውን ነጥሎ መፆም "ይጠላል" ያሉ ዑለሞች መረጃቸው፤ ነቢዩ – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – [(ከዓሹራእ) ከፊቱ አንድ ቀን እና ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ። አይሁዳውያንን ተቃረኑዋቸው።] ማለታቸውን ሲሆን፤ ይህ ሐዲስ አይሁዳውያንን ለመቃረን አንድ ቀን መጨረም ግዴታ መሆኑን ያስገነዝባል። ወይም ነጥሎ መፆም መጠላቱን ያስረዳል። ይላሉ። #መነጠሉ_ይጠላል_የሚለው_እንደ_መረጃ_ጠንካራ_ነው! ስለዚህ አንድ ሰው ከኺላፉ ለመውጣት ከበስተፊቱ 9ኛውን ወይም ከበስተኋላው 11ኛውን ቢፆም የሚለውን እንደግፋለን።” ሊቃኣቱ አልባቢል መፍቱሕ 95 84 views🅂🅈🄷, 05:30