ዋ ምኞቴ ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ ምኞቶች ⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ تُرَٰبًۢا﴾ " ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ " [ሱረቱ ነበእ 40] ⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى قَدَّمْتُ لِحَيَاتِى﴾ " ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ " [ሱረቱል ፈጅር 24] ⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى لَمْ أُوتَ كِتَٰبِيَهْ﴾ " ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ " [ሱረቱል ሃቀህ 25] ⇦ ﴿يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًۭا﴾ " ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ " [ሱረቱል ፉርቃን 28] ⇦ ﴿يَٰلَيْتَنَآ أَطَعْنَا ٱللَّهَ وَأَطَعْنَا ٱلرَّسُولَا۠﴾ " ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ " [ሱረቱል አህዛብ 66] ⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى ٱتَّخَذْتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلًۭا﴾ " ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ " [ሱረቱል ፉርቃን 27] ⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًۭا﴾ " ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ " [ሱረቱ ኒሳእ 73] ☞ ሁሉም የሟቾች ምኞት ናቸው ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው ... ☞ ቀብር ገብተህ አንተም ይህን ከምትመኝ ነፍስህ አካልህ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም። አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን ያረብ SHARE&JOIN t.me/umumahi1 t.me/umumahi1 418 views🅂🅈🄷, 11:17