Get Mystery Box with random crypto!

ጸሎት ከውስጥ የሚመነጭ የልብ መቃተት ስለሆነ ቃላት ብቻ ሊገልጹት አቅም የላቸውም። በተመሰጠ ልብ | ✞ትንሽ ዝምታ ✞

ጸሎት ከውስጥ የሚመነጭ የልብ መቃተት ስለሆነ ቃላት ብቻ ሊገልጹት አቅም የላቸውም። በተመሰጠ ልብ ፣ በመንፈሳዊ ሀሳብ ፣ በተሰቀለ ኅሊና ወደ አምላካችን የምንነጠቅበትና ከፈጣሪያችን ጋር የምንነጋገርበት ስለሆነ ጸሎት ከቃላት በላይ ነው። በዝምታ እያለን በኅሌናችን ልንመሰጥ እንችላለን።

ጸሎት እግዚአብሔርን የናፈቀ ልብ ሲቃ ነውና ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ይለካበታል። ሰውና እግዚአብሔር መገናኘት የሚችለው በዚህ ዓይነት ከልብ ተፈንቅሎ የሚወጣ ጸሎት ስለሆነ ከዚህ መንፈሳዊ ሕብረት ውጪ ሆነው የሚጮኹት ጩኸት ረብ የለሽ የቃላት ጋጋታ ነው። እግዚአብሔር አምላክን የምትወድ ፣ የምታፈቅር ከሆነ ትጸልያለህ ፤ ከጸለይህ ደግሞ ፍቅረ እግዚአብሔር በውስጥህ ያድጋል። እስኪ በዚሁ ፍቅር የተቀጣጠለና ልብ የሚነካውን የዳዊትን ጸሎት አስተውል "አምላኬ አምላኬ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ ነፍሴ አንተን ተጠማች ፤ ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች። መቼ እደርሳለሁ ? የአምላኬንስ ፊት መቼ አያለሁ።...." (መዝ. ፷፪፥፩)። ደረቅ መሬት በእውነት ዝናምን እንደምትናፍቅ እግዚአብሔርን መናፈቅና መጠማት ይህ አይለይም? እውነት ነው ፍጹም ይህ ነውና።

ብጹእ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ