Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔር አለ! በዝምታ እግዚአብሔር አለ!በቀና ልብ እግዚአብሔር አለ!በስቃይ፣በደስታ እግዚአ | ✞ትንሽ ዝምታ ✞

እግዚአብሔር አለ! በዝምታ
እግዚአብሔር አለ!በቀና ልብ
እግዚአብሔር አለ!በስቃይ፣በደስታ

እግዚአብሔር አለ!ሁሌም አለ።ማየት የሚቻለው ማነው??ማነው እግዚአብሔርን በዝምታ ውስጥ ማየት የሚችለው??ማነው እሱ እስከሚናገር በፅናት የሚቆይ??ማነው ያ ፃድቅ ሰው እግዚአብሔር አምላኩን በትንሽ ዝምታ፣በሰፊው የሚያየው?

ትንሽ ዝምም እንበል።ቅዳሴውን በአርምሞ፣ፀሎቱን በርጋታ፣እንባችን በዝግታ፥ልመናችን በጥሞና፣ልግስናችን፣በድብቅ፣

ዝምም እንበል፣ፍቅራችን በልባችን፣
በደላችን፣ችግራችን፣ሀዘናችን፣ሁሉ በዝምታ ውስጥ እናሳልፈው።

እግዚአብሔር አለ በዝምታ
ውስጥ!!


ሱራፌል/