Get Mystery Box with random crypto!

ለእኛ ብሎ ቢሰቀል ራሱ ሊመለክ አይገባውም የዒሳ (የእየሱስ) አምላኪ ነን | ሐምዱ<=>ቋንጤ

ለእኛ ብሎ ቢሰቀል ራሱ
ሊመለክ አይገባውም



የዒሳ (የእየሱስ) አምላኪ ነን ብለው
“እየሱስ ያድናል፣ እየሱስ ጌታ ነው” እያሉ የሚሰብኩ ፔንጤዎችና ይህንኑ አመለካከት የሚያምኑ ኦርቶዶክሶች ለዚህ ባጢል ለሆነው እምነታቸው መረጃ አድርገው ከሚያቀርቧቸው ነጥቦች አንዱ…
“እየሱስ እኛን ለማዳን ሲል ተሰቅሏል” የሚል ነው።

ይህ አባባል በሎጂካልም ይሁን በእምነታዊ መነፅር ቢታይ በብዙ ዓይነት መልኮች ሙሉ ለሙሉ ውድቅ የሚሆን ሲሆን እኔም በዚህ ዳሰሳዬ ውድቅ ከሚሆንባቸው መንገዶች አንዱን ለማየት ወደድኩኝ።


«ለእኛ ብሎ ቢሰቀል ራሱ ሊመለክ አይገባውም።»
እንዴት

“ለእኛ ሲል ተሰቀለ” የሚለው ዓረፍተ ነገር ሲተረጎም፦
እኛ (የሰው ልጆች) አመፃችን በዝቶ የሆነ አካል (አምላካችን) አስቆጣነው። አምላካችንም እኛን በወንጀላችን ብዛት ሊያጠፋን ተቃረበ። በዚህ ጊዜ የሆነ አካል (ዒሳ (እየሱስ)) መጣና እኛ እንማር ዘንዳ እሱ ተሰቀለና በእሱ መሰቀል (መቁሰል) እኛ ተፈወስን (ተማርን)። ስለዚህ “እኛን ያዳነን እየሱስ ነውና እናመልከዋለን”
ማለት ነው።
ይህ ነው እምነታቸው።


አሁን ተከታተሉኝ…
1ኛ,በወንጀላችን ምክንያት የተቆጣ አካል (አምላክ) አለ ማለት ያንን አምላክ ዋነኛው (የሐቅ) አምላካችን እሱ ነው።

2ኛ,አምላካችን በወንጀላችን ብዛት ተቆጥቶ እኛን ከጥፋት ለመታደግ ራሱን ሰውቶ የተሰቀለ አካል ቢኖር ራሱ ያ አካል እኛን ከአምላካችን ቁጣ ሊታደገን አማላጅ የሆነ አካል እንጂ እሱ ራሱ አምላካችን ሊሆን አይችልም።

3ኛ,እኛን ለማዳን አማላጅ ሆኖ የተሰቀለ አካል አለ ማለት፦
3.1, እሱ አምላካችን እንዲምረን አማላጅ የሆነ አካል እንጂ እሱ ራሱ የሚምር (የሚያድን) አካል አይደለም።
3.2, ይህ ተሰቀለ የተባለው አካል እውነተኛው (ሐቁ) አምላካችን እንዲምረን የሚለምንና የሚማፀን እንጂ እሱ ራሱ መማርም ይሁን ማዳን የማይችል አካል እንደ ሆነ ያሳየናል።

በራሳቸው አንደበት……
“አምላካችን እንዳይቀጣን እየሱስ ለእኛ ሲል ተሰቀለ” እያሉ
በሌላኛው ምላሳቸው
“እየሱስ ጌታ ነው፣ እየሱስ ያድናል” እያሉ ይሰብካሉ።

ወገን!
አንድ ሽንቱን የመቆጣጠር ያህል እንኳ አእምሮው ጤነኛ የሆነ ሰው……
እየሱስ ጌታ ከሆነ፣ እየሱስ የሚያድን ከሆነ
ለምን ተሰቀለ ሳይሰቀል ለምን አላዳነንም ብሎ አይጠይቅም

እውነታው ግን……
ዒሳ (እየሱስ)
አልተሰቀለም አልተገደለም።
ማዳንም መማርም አይችልም።


የአላህ ትእዛዝና ክልከላ ወደ ባሮች እንዲያስተላልፍ አላህ በትልቅ ተኣምር ላይ አድርጎ የላከው ባሪያውና መልእክተኛው ነው። ጠላቶቹ ጥቃት ሊፈፅሙበት ባሴሩ ጊዜ አላህ ወደ ሰማይ ከፍ አደረገው
ይህንን እውነታ የተቃረነ የትኛውም እምነት ውድቅ (ባጢል) ነው።


ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር
https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB