Get Mystery Box with random crypto!

Hakim @ሐኪም

የቴሌግራም ቻናል አርማ hakim_doctors_ethio_health_tena — Hakim @ሐኪም H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hakim_doctors_ethio_health_tena — Hakim @ሐኪም
የሰርጥ አድራሻ: @hakim_doctors_ethio_health_tena
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.06K
የሰርጥ መግለጫ

Hakim @ሐኪም
@Hakim365bot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 15:42:01
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
294 views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:00:40 የጆሮ ማሳከክ ምክንያቶች በጥቂቱ

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም )

ጆሮ ለመስማት የሚያገለግለን የሰውነታችን ክፍል ነው ከዚህም ባለፈ ጆሮ ሚዛንን ለመጠበቅም ጠቀሜታ አለው። ጆሮ በተለያየ ምክንያት ሲጎዳ ከሚከሰቱ ምልክቶች አንዱ የማሳአክ ስሜት ነው።

የጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችን ማወቅ በቶሎ መፍሄዎቻቸውን እንድንፈልግ ይረዳናል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለጆሮ ማሳከክ መንስኤዎችም ናቸው።

* የጆሮ ኩክ መከማቸት

የጆሮ ኩክ (Earwax) የምንለው ሰውነታችን የሞቱ ሴሎችንና ቆሻሻዎችን የሚያጸዳበት መንገድ ሲሆን በብዛት በሚገኝበት ወቅት ግን የማሳከክ ስሜትን ይፈጥራል።

ጆሮን ለማጽዳት መሞከር ኩክ ይበልጥ ወደ ውስጥ እንዲገባ ስለሚያደርግ ይህን ከማድረግ ይቆጠቡ። ወደ ሀኪም በመሄድ ከታዪና ትክክለኛ ምክንያቱ የኩክ መጠራቀም ሆኖ ከተገኘ በጠብታ መድሀኒት ወይንም በህክምና ባለሞያ እርዳታ እንዲወጣ ይደረጋል።

*ኢንፌክሽን

የጆሮ ማሳከክ አንዳንዴ ደግሞ የ ኢንፌክሽን መኖር ምልክት ይሆናል። ጉንፋንን ወይንም ቶንሲልን የሚያስከትሉ ባክቴርያና ቫይረስ በደም ተዘዋውረው ወደ ጆሮ በመሄድ ኢንፌክሽን እንዲፈጠር ያደርጋሉ።

ውሀ ዋና የሚዋኙ ሰዎችም ውሃው በጆሮ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስለሚቆይ እና ተፈጥሮአዊ የሆነውን ጀርሞችን የመከላከል አቅም በእርጥበት ምክንያት እንዲያጣ ስለሚያድርግ ሌላው የ ኢንፌክሽን መንስኤ ተደርጎ ይወሰዳል።

የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ ወደ ሀኪም በመሄድ ጸረ ባክቴርያ የሆኑ የጆሮ መድሀኒቶችን መጠቀም ተገቢ ነው።

*የቆዳ አለርጂ

በጆሮዎ ውጨኛው ክፍል የሚገኘው ቆዳዎ በአለርጂ ምክንያት የማሳከክ ስሜትን ሊያመጣ ይችላል።

የመዋቢያ ቅባቶች ወይንም ቁሳቁሶች አለርጂን ሊይስከትሉ ይችላሉ። የማሳከክ ስሜቱ እንዲጠፋ አለርጂው የተከሰተበትን ምክንያት ተከታትሎ ማወቅ ያስፈልጋል። ከዛም መጠቀም ማቆም ተገቢ ነው።

*ጆሮን በሹል እና ጎጂ ሊሆኑ በሚችሉ እንደ ጸጉር ሻጤ፣ አግራፍ፣ የክብሪት እንጨት በመሳሰሉት ማጽዳት የጆሮ ቆዳን ለመሰንጠቅ ስለሚችል ለኢንፌክሽን ይዳርጋል ከዚህም ባለፈ የጆሮን ውስጣዊ ክፍል በመጉዳት የመስማት ችሎታችንን ሊያሳጣን ይችላል።

ጤና ይስጥልኝ

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
450 views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:00:13
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
334 views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:18:23 "ልጄን ፀሀይ ለማሞቅ ሳወጣው በቅቤ ወይም በቫዝሊን አሸዋለሁ"

እስኪ ስለ ፀሐይ ብርሃን ለህፃናት ያለው ፋይዳ እና በማህረሰባችን ወስጥ የሚፈፀሙ የተለመዱ የተሳሳቱ ልማዶችን ጀባ ልበላችሁ

አስራ ሁለት ወራት ፀሐይ እስከ ቤታችን ደጃፍ በምትወጣበት ሀገር : በፀሐይ እጥረት አጥንታቸው ተጣሞ የሚመጡ ልጆች ቀላል አይባሉም። ይህን ከማየት በላይ ምን ልብ የሚሰብር ነገር አለ?

እድሜ ልክ የሚከተል አካል ጉዳት ከሚያስከትሉት የህፃናት ህመሞች መካከል አንዱ ሪኬትስ መሆኑን በቅጡ ያውቃሉን?

ሪኬትስ በቫይታሚን D እጥረት የሚከሰት ሲሆን አጥንቶቻችን እንዲሰሩ የሚያደርጉት ካልሲየም እና ፎስፈረስ ሰውነታችን ከምግብ መጦ መጠቀም እንዳይችል ያደርገዋል። የዚህ ቫይታሚን እጥረት ከብዙ ምክኒያቶች ሊመጣ ቢችልም ባብዛኛው የሚታየውና ዋንኛው ከፀሀይ ብርሃን እጥረት የሚከሰተው ነው! የፀሀይ ብርሃን በቆዳችን አልፎ የማይሰራውን ቫይታሚን D አይነት ወደሚሰራው አይነት ስለሚቀይረው ዋንኛ የቫይታሚኑ ምንጭ ነው።

በማህረሰባችን ወስጥ በፀሀይ ማሞቅ ዙሪያ የሚፈፀሙ የተለመዱ የተሳሳቱ ልማዶችን ጀባ ልበላችሁ

1. ሳወጣው በቅቤ ወይም በቫዝሊን አሻዋለሁ
2. አውጥቼው አላውቅም ለረዥም ጊዜ ምከንያት የሰው አይን ይበላዋል ብዬ / መች እንደሚወጣ ስለማላውቅ
3. የቤት መስኮት አጠገብ በመስታወት አሞቀዋለሁ
4. ግቢው ወይም ሰፈሩ ስለሚቀዘቅዝ እቤት ዉስጥ በእሳት አሞቀዋለሁ ወዘተ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።

የፀሐይ ብርሃን ፋይዳው ለህፃናት ምንድነው ?ህፃናት ከመች ጀምረው ነውና ፀሐይ መወጣት ያለባቸው? የትኛው የፀሐይ ብርሃን ነው ተመራጩ የጥዋት ወይም የከሰኃት? ህፃናት ፀሃይ በሚሞቁበት ጊዜ ቅባት ወይም ቅቤ በቂዳቸው መቀባት ጠቃሚ ወይስ ጎጂ ልምድ ነው? ይኸው

የፀሐይ ብርሀን ከቆዳችን ሲያርፍ ቫይታሚን ዲ የተባለውን ንጥረ ነገር እንዲመረት ያደርጋል::

ህፃናት ከተወለዱ ከ14ኛው ቀን ጀምረው በቀን ከ10 እስከ 15 ደቂቃ የጠዋት ፀሀይ ብርሃንን ማሞቆ ይህን በሽታ ይከላከላል።

ታዲያ ልብ ይበሉ ቫዝሊን ወይም ሌላ ቅባት ከመሞቁ በፊት ወይም እየሞቀ አይቀባም! የፀሀይ ብርሃኗን ስለሚሸፍንባቸው ከሞቁ በኋላ ብቻ ነው ሚመከረው! በሚወጡበት ጊዜ በተቻለ መጠን ያለ ልብስ ቢሞቁ ይመከራል።

የፀሐይ ብርሃን ፋይዳው ለህፃናት ?

ከአንጀት ውስጥ ካልሲየም የተባለውን ንጥረ ነገር ወደ ሰውነት እንዲገባ ያደርጋል ። ይሄ ንጥረ ነገር ለአጥንት እና ለጥርስ እድገት በጣም አስፈላጊ ነዉ። የዚህ ንጥረ ነገር እጥረት ያላቸው ልጆች የአጥንት ጥማት ፣ የጥርስ እድገት መዘግየት ወይም በሚጠበቀው ወቅት አለማብቀል።

ሌላው የቫይታሚን ዲ ጠቀሜታ የሰውነታችንን የበሽታ የመከላከያ አቅም እንዲጨምር ያደርጋል። ሪኬትስ ያለው ልጅ ለተደጋጋሚ የሳንባ ኢንፌክሽን ለቲቢ ወዘተ ኢንፌክሽን የተጋለጠ ይሆናል ማለት ነው።

ህፃናት እስከ መቼ ነው ፀሃይ መውጣት ያለባቸው ?

ፀኃይ ሁሌም ስለሚያስፈልጋቸዉ ህፃናቱ በራሳቸዉ ወደ ፀኃይ መዉጣት እስኪ ጀምሩ ድረስ በቤተሰብ እርዳታ ፀኃይ ማግኘት አለባቸዉ ።

የፀሐይ ብርሀን በማይኖርበት ወቅት ለምሳሌ በክረምት ወረት የተዘጋጁ ቫይታሚን ዲ መድሃኒቶች በመጠናቸው ልክ በባለመያ ትዛዝ መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ዶ/ር መሐመድ በሽር የህፃናት ሐኪም
መልካም ጤንነት ተመኘሁ
ለብዙሃን እንዲደርስ ሼር በማድረግ ይተባበሩን

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
159 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:17:07
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
141 views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:26:19 እርሶ ፣ ቤተሰቦ ወይንም ደግሞ እሚያቁት ወዳጅ ዘመዶ የአይን ህክምና ቦታ ሄደዉ የአይን መድረቅ አለብዎ ፤ ይህንና ያንን ያድርጉ ተብለዉ ይሆናል።

ለመሆኑ የአይን መድረቅ ምንድነው? በምንስ ይመጣል? መከላከያዉና ህክምናዉስ ምንድነዉ? ስለሚሉት ነገሮች በትንሹ ጀባ እንበላችሁ።

ከሳይንሳዊ ትርጓሜዉ ስንነሳ የአይን መደረቅ ማለት እንባችን በተገቢው መጠንና ስሪት አለመመንጨት ወይንም ደግሞ ከመነጨ በኋላ የዉጨኛው የአይን ክፍላችንን አረስርሶ ተረጋግቶ አለመቆይትና እነዚህን ተከትሎ እሚፈጠር የአይን ምቾት ማጣት ፣ የእይታ መረበሽና የዉጨኛዉ የአይን ሽፋን መቁሰልን ያካተተ የአይን ህመም ነዉ።

ስንት አይነት የአይን መደረቅ አለ?
በአጠቃላይ ስንመለከት ሁለት አይነቶች ሲኖሩን

1. ዉሀማዉ የእንባችን ክፍል በተገቢዉ መጠን አለመመንጨት እና
2. እንባችን ከሚገባው መጠን በላይ መትነን
3. ከላይ ያሉት የሁለቱን ያጣመረ**

ምልክቶቹ ምንድን ናቸዉ?
አይናችን
* ምቾት ማጣት፣ የመቆጥቆጥና የማቃጠል ስሜት
* መቅላት
* መቆርቆር
* ብርሀን መፍራት
* የእይታ መደብዘዝና መዳከም
* ከተገቢዉ በላይ ቶሎ ቶሎ መጨፈንና ማልቀስ
* Mucus ያዘለ ፍሳሽ የአይናችን ጥግ ላይ መኖር

ምክንያቶቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

* በተለያዩ ምክንያቶች የእንባ እጢ ላይ በሚደረስ ጉዳት ሳቢያ የሚመነጭ የእንባ መጠን መቀነስ
* የእንባ እጢዎች እንባ ማስተላለፊያ ትቧዎች መዘጋት
* Sjogren syndrome

* የነርቯች በተገቢዉ ሁናቴ አለመስራት (refex block due to contact lens wear, laser eye surgery or trauma to the nerve itself)

* ለተለያዩ ህመሞች እመንወስዳቸዉ መድሀኒቶች (systemic medication) (antihistamines, decongestant, hormon replacement therapy, antidepressant....)

* ለእንባችን መሸፈኛ እሚያገለግለውን ዘይታማ ክፍል እሚያመነጩ እጢዎች መዘጋትና እሚያመነጩት መጠን መቀነስ
* የአይን ቆብ ችግሮችና ዝቅተኛ የሆነ የመጨፈን መጠን

* የVitamin A እጥረት
* ለረጅም ገዜ ማቆያ ኬሚካል(preservative) ያላቸዉ ጠብታዎች
* Contact lens ማድረግ

ከነዚህ ምክንያቶች በተጨማሪነት የአካባቢዎ ሁኔታ እሚያደርሰዉ ተፅዕኖም አለ። እንደምሳሌ
* ለረጅም ሰዓት ማንበብ እና መኪና ማሽከርከር
* ንፋሳማና ዝቅተኛ እርጥበት አዘል የአይር ሁኔታ
* እርጅና
* ሲጃራ ማጤስ ወይንም እሚያጤስ ሰው አካባቢዮ ላይ መኖር... እንደምክንያት ይጠቀሳሉ።

መቼ ሀኪሞትን ያማክሩ?

ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ካለዎት አቅራቢያዎ ወዳለ የአይን ህክምና አገልግሎት ሰጪ ክፍል በመሄድ አይንዎን ቢታዩ ይመከራል።

ህክምናው ምንድን ነዉ?

የአይን መድረቅ ህክምና ታካሚዎች እንዳሉበት የበሽታዉ ደረጃ እሚወሰን ሲሆን በአጣቃላይ ግን ህክምናው ቀጥሎ ያሉትን ነገሮች ያጠቃልላል

1. ታካሚዎችን ስለበሽታዉ ባህሪ ፣ ዘላቂነት (chronic) ና ማድረግ ስለሚገበቸዉ ጥንቃቄ ማስተማር

2. የእንባ እጢዎች እንባ እንዲመነጩ ማበረታታት፣ መተካትና ማቆየት

3. የአይን መቁሰልን መቆጣጠርና ማከም
4. የአይን ቆብ ችግሮችን ተገቢዉን ህክምና መስጠት

ታካሚዎች ማድረግ ያለባቸዉ ጥንቃቄ

* እየወሰዱ ያሉትን ማንኛዉንም መድሀኒቶች ለአይን ሀኪሞ ያሳዩ
* ሲጃራ እሚያጤሱ ከሆነ ያቁሙ
* ኮምፒውተር ና ስልክ ሲጠቀሙ የብርሀን መጠኑን ይቀንሱ
* በሚያነቡበት ጊዜ በየመሀሉ እረፍት ይውሰዱ
* ሲያነቡ ፣ ኮምፒውተር ና ስልክ ሲጠቀሙ ቶሎ ቶሎ መጨፈኖን አይዘንጉ
* አካባቢዎት ደረቅ እና ንፋሳማ ከሆን መቀየርን ያስቡ።

ከሚያባብሱ ነገሮች ለምሳሌ ceiling fan ካለ ያስወግዱ።
* ከቤት ዉጪ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መነፀር መጠቀምን ይልመዱ
* የአይኖትን ንፁህና መጠበቅ ፈፅሞ አይዘንጉ።

ዶ/ር በእምነት ተረዳ ፤ የአይን ህክምና ስፔሻሊስት

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
190 views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:25:59
@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena
170 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ