Get Mystery Box with random crypto!

በል ጎራው በል ጎራው በል ፎክር ይለኛል፣ ሰው በሰው ሲገፋ ሲጠቃ ያመኛል። ዘንድሮስ ይሄ ቀን ላን | ግጥም ከገጣሚያን

በል ጎራው በል ጎራው በል ፎክር ይለኛል፣
ሰው በሰው ሲገፋ ሲጠቃ ያመኛል።
ዘንድሮስ ይሄ ቀን ላንተ ሲል ባልመሼ፣
እንዳትጠራጠር እጥፍ ነው ምላሼ።
ጠጥተህ ጠጥተህ እንደበርበሬ ፍል፣
ወዴት ትሸሻለህ እዳህን ሳትከፍል።
ስሙን አልጠራውም ያውቀዋል ስናገር፣
ተማምለን ነበር አብረን ልንሻገር።
ገና በቁልቁለት ቀረ ወደኋላ ፣
ኤያየሁ ዝም አልኩት ቃሉን እንደበላ።
አሁንስ ቸገረኝ ዝም ብለው ባሰ
በእጁ ግፍ አበዛ ደም እያፈሰሰ።
የያዕቆብን መሬት በጉልበቱ አረሰ
ላያድር ነው መሠል በቀን ገሰገሰ።
ተወልዷል ይሉኛል በጉ ቀንድ አውጥቶ
ምኑን ተወለደ እናቱን ተዋግቶ።
ከወንዱ ጀግናው ቦታላይ ፈሪ ተኝቶበት
ሲባንን አደረ በህልሙ እየመጣበት።

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39