Get Mystery Box with random crypto!

የኔታ ነህ ለኔ ያ ሸንጋይ ምላስህ ቅቤ የሚያቀልጠው ፎርጅድ ማንነትህ ከላይ የሚታየው መታ | ግጥም ከገጣሚያን

የኔታ ነህ ለኔ


ያ ሸንጋይ ምላስህ ቅቤ የሚያቀልጠው
ፎርጅድ ማንነትህ ከላይ የሚታየው

መታወቂያው ሌላ ማሞው ሌላ ሆነህ
ያንቺ ነኝ ስትለኝ ልብህን ሸሽገህ

ሰው አማኙ ልቤ ለፍቅርህ ሲሸነፍ
ምስኪን ማንነቴ አንተን አምኖ ሲከንፍ

የታሻለ ስታይ አቁስለኸው ልቤን
ትተኸኝ ስትሄድ ንቀኸው መውደዴን

እጅጉን ብጎዳም ባንተ ምክንያት ያኔ
አመሰግናለሁ የኔታ ነህ ለኔ
ስለሰው ማንነት ያዘረፍከኝ ቅኔ

ፅዮን

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39