Get Mystery Box with random crypto!

ነገር ሁሉ ያልፋል ዛሬ ደስ ቢልህ ደስታህ ከእቅልፍ ነቅቶ እንዳትዘናጋ ሀዘንም ይነቃል አይ | ግጥም ከገጣሚያን

ነገር ሁሉ ያልፋል


ዛሬ ደስ ቢልህ ደስታህ ከእቅልፍ ነቅቶ
እንዳትዘናጋ ሀዘንም ይነቃል አይቀርም ተኝቶ
ወይም ከጨነቀህ ሀዘንህ ሲነቃ
ለልብህ ንገረው ደስታህም ይነቃል ሲደርሰው ፈረቃ
የልብህ ውስጥ አልጋ ጠባብ ነው መደቡ
እኩል አያስነቃም እኩል አያስተኛም ልዩ ነው ጥበቡ
ምን ይደረግ?..........ሀዘንህ ከነቃ ደስታህ ያንቀላፋል!
በእንዲህ አይነት ጥበብ፤ በመፈራረቁ፤ ነገር ሁሉ ያልፋል!!!

Some of you say, "Joy is greater than sorrow," and others say, "Nay, sorrow is the greater."
But I say unto you, they are inseparable.
Together they come, and when one sits, alone with you at your board, remember that the other is asleep upon your bed."- Khalil Gibran

ከልቤ የምወደው አባባል "ነገር ሁሉ ያልፋል" የሚለውን ነው። እስኳሁን ከብዶን ያላለፈ ነገር የለም። የሚነጋ ያልመሰለን ወቅት እንኳን ከመንጋት አልፎ ዘመን አስቆጥሯል። ጂብራን እንዳለው ደስታና ሃዘን ተፈራራቂ ናቸው፤ ሁለቱም ያልፋሉ፤ ተመልሰው ይመጣሉ፤ እንደገና ተመልሰው ያልፋሉ። ሀዘን ሲያንቀላፋ ደስታ ይነቃል፤ ደስታ ሲያንቀላፋ ደግሞ ሀዘን ይነቃል። ሁለቱም ሃላፊዎች ናቸው፤ ግን በነቁ ቁጥር የሚሰጡን ትዝታ እና ስሜት ልዩ ነው። "ሁሉም ያልፋል" የተስፋ ቃል ብቻ አይመስለኝም፤ የማስታወሻም ጭምር እንጂ፤ ምክንያቱም ሀዘን ብቻ ያልፋል አይደለም የተባለው፤ ደስታም ጭምር እንጂ። ለማንኛውም ተስፋ ከቤታችን አይጥፋ ሌላ ከዚህ የበለጥ ምን ምኞት አለ?

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join
.. @habtamu39
@habtamu39
@habtamu39