Get Mystery Box with random crypto!

የሰው ልጅ የክብር ጉዞ የኔና ያንተ ክብር ነው፤ የሰው ልጅ የውርደት እሽቁልቁሊት የኔና ያንተ ውር | BEEKI OR እወቅ

የሰው ልጅ የክብር ጉዞ የኔና ያንተ ክብር ነው፤ የሰው ልጅ የውርደት እሽቁልቁሊት የኔና ያንተ ውርደት ነው። ከመኪና እያወረዱ የረሸኑን እኔና አንተን ነው፤ ረሻኞችም እኛው ነን።
በወለጋ የተጨፈጨፍነው እኔና አንተ ነን፤ ጨፍጫፊዎቹም እኛው ነን።

የትም ቦታ የሚደርስ ኢሰብአዊነት ከሰውነት ተርታ የሚያስወጣን እኛኑ ነው። ከሰውነት ክብር መውረድ ማለት ወደ እንስሳነት ደረጃ ዝቅ ማለት ነው። እንስሳነት ሲያይል በንፁሃን ደም የሚፎክርና ነውሩ ክብሩ የሆነ ሰው በማህበረሰብ ውስጥ ይበቅላል።

ወንድሜ፣
"ማን ተገደለ?" ብለህ አትጠይቅ፤ የሞትነው እኔና አንተ ነን። "ማን ገደለ?" ብለህም አትጠይቅ፤ የጨፈጨፍነው እኔና አንተ ነን። "ማን ያስቁመው?" ካልከኝ ራሱን "ሰው" ብሎ የሚጠራ ማንኛውም ሰው ሁሉ እልሃለሁ። ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች...

አላህ ሆይ! በቃ በለን! የእውነት "ሰው" እንሆን ዘንድ እርዳን።